Wednesday, April 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊመንግሥት በሴቶች ላይ የሚደርስን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

መንግሥት በሴቶች ላይ የሚደርስን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚደርስ ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃትን እንዲያስቆም መንግሥትን ጠየቀ፡፡

ኢሰመጉ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ የሴቶች ጥቃት ከጊዜ ወደጊዜ እጨመረ መምጣቱንና በዚህም ተቋሙ በተለያዩ ጊዜዎች ባወጣቸው መግለጫዎች፣ መንግሥት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት ሰጥቶ ጥቃቱን እንዲያቆም ሲወተውት የቆየ ቢሆንም፣ አሁንም ጥቃቱ መልኩንና ባህሪውን እየቀያየረ ራሳቸውን እንኳን መከላከል በማይችሉ ሕፃናት ሴቶች ላይ ሳይቀር ድርጊቱ በዘግናኝ ሁኔታ እየተፈጸመ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ለአብነት ከሰሞኑም የ17 ዓመት ታዳጊና 12ኛ ክፍል ተማሪ በነበረቸው አዶናይት ይሔይስ በተባለች ተማሪ ላይ በተደጋጋሚ የአስገድዶ መድፈር ድርጊት ሲፈጸምባት ቆይቶ መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወቷ አልፎ መገኘቱን አስረድቷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በተጨማሪም አልማዝ እሸቱ የተባለች ግለሰብ በተደጋጋሚ ድብደባ ሲፈጸምባት ቆይቶ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ በመኖሪያ ቤቷ መታጠቢያ ውስጥ መገኘቷን እንዲሁም ወ/ት ባህር ሼህ የተባለች ግለሰብ መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡45 ሰዓት በዲስ አባባ በተለምዶ መሳለሚያ በሚባለው አካባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ የተለያዩ ቦታዎች ሰውነቷ ተወግቶ ሕይወቷ አልፎ መገኘቱን ጠቅሷል፡፡

ኢሰመጉ እነዚህን ለማሳያነት አቀረብኩ ይበል እንጂ በሴቶች ላይ መሰል ጥቃቶች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ውስጥ በተደጋጋሚ እየተፈጸሙ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች የደረሱት መሆኑን አስታውቋል፡፡ በመሆኑም ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ከጊዜወደ ጊዜ እየተባባሱ መምጣታቸው ለጉዳዩ በመንግሥት ሆነ ሌሎች በሚመለከታቸው አካላት በቂ የሆነ ትኩረት እየተሰጠው አለመሆኑን ማሳያ እንደሆነ በመግለጫው አቅርቧል፡፡ በሴቶች ላይ በሚደርስ ጥቃት ምክንያት የሴቶች መብቶች አከባበር በተለይም ለሴቶች መብቶች ጥበቃ ከማድረግ አንፃር አሁን ላይ ያለው ሁኔታ በየጊዜው እየቀረቡ ካሉት አቤቱታዎች መጨመር አንፃር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቋል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት በሴቶች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ላይ መንግሥት በቂ ጥኩረት በመስጠት ሴቶችን በተመለከተ ያሉ ሕጎችን በማሻሻል፣ ለሴቶች ተገቢውን ከላላ የሚሰጥ የሕግ ማዕቀፍ እንዲዘረጋ ኢሰመጉ ጠይቋል፡፡

በመሆኑም መንግሥት በአፍሪካ ቻርተር የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ፕሮቶኮል የሆነው የአፍሪካ ሴቶች (Maputo Protocol) ላያ ያደረጋቸው አንዳንድ ተአቅቦዎች፣ ሴቶች ሊኖራቸው የሚገባቸውን መብቶች የሚገድብ በመሆኑ፣ ተአቅቦዎቹን እንዲያነሳ እንዲሁም በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ማንኛውንም ዓይነት አድልዎ ለማስወገድ የወጣው ስምምነት (CEDAW) የአማራጭ ፕሮቶኮል (Optional Protocol) ለሴቶች ተጨማሪ መብቶችን የሚያጎናጽፍ በመሆኑ ይህንን የአማራጭ ፕሮቶኮል አንዲያፀድቅ ጠይቋል፡፡

በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተለይም መንግሥት፣ የሃይማኖት አባቶች የማኅበረሰብ አንቂዎች፣ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ሲቪል ማኅበራት እንዲሁም ግለሰቦች፣ በሴቶች ላይ የሚደርስን ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ለመከላከል በጋራ እንዲቆሙና የሴቶች መብቶችን መንግሥት እንዲያከብር፣ እንዲያስከብርና የሕግ እንዲሁም የሥነ ሥርዓት ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ የተጠናከረና የተቀናጀ የውትወታ ሥራን እንዲሠሩ ኢሰመጉ ጥሪ አቅርቧልል፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...