Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመንግሥት ለአየርላንድ መንግሥት የመጨረሻ ማሳሰቢያ አስተላለፈ

መንግሥት ለአየርላንድ መንግሥት የመጨረሻ ማሳሰቢያ አስተላለፈ

ቀን:

ስድስት የአውሮፓ አገሮች የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቆም አሳሰቡ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰሜናዊ ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የአየርላንድ መንግሥት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጻረሩ ድርጊቶችን እየፈጸመ ነው ሲል ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ‹‹ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ›› የሚል ማሳሰቢያ ደብዳቤ ጻፈ።   

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኰንን  ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ለአየርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በጻፉት ደብዳቤ፣ የፌደራል መንግሥት ከሕወሓት ታጣቂዎች ጋር የሚደረገውን ጦርነት በሰላም ለመፍታት በአፍሪካ ኅብረት የቀረበውን ሰላማዊ ድርድር ጥሪ መቀበሉንና ችግሮቹን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በጦርነቱ ተፈጸሙ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በምርመራ በማረጋገጥ፣ ሁሉን አቀፍ የሽግግር ጊዜ ፍትሕ ሥርዓት በመዘርጋት፣ እንዲሁም በብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ሁሉን አቀፍ ምክክር በማድረግ የአገሪቱን የወደፊት ዕጣ ፋንታ ለመወሰን በሚያስችል መልኩ ጠንካራ መሠረት ለመጣል የሚያስችሉ ቁርጠኛ ውሳኔዎችን እየወሰደ መሆኑን አስረድቷል፡፡

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ከአውሮፓ ኅብረት ከመጡ ተወካዮች ጋር በግል አካሄድኩት ባለው ንግግር፣ ኢትዮጵያ ከኅብረቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማስተካካል ከፈለገች ከአየርላንድ ጋር ያለውን ግንኙነት በማስተካከል ወደ ነበረበት መመለስ እንዳለባት መነጋገሩን በደብዳቤው አስታውቋል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ ከአየርላንድ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት ማስተካከል ትልቅ ዓላማ አድርጋ እየሠራች መሆኑ ቢታመንም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማስተካካል እየሄደበት ባለው ልክ፣ የአየርላንድ መንግሥትም ጉዳዩን በዚህ ልክ እንደሚወስደው አላውቅም ብሏል፡፡  በመሆኑም አየርላንድ በኢትዮጵያ ላይ እያካሄደችው ያለውን ጠብ አጫሪ እንቅስቃሴ እንድታቆም አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሁሉም ወዳጅና ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ያለውን ግንኙነት በተሻለ ሁኔታና በአዲስ መንፈስ  ለማስተካከልና ለማቆም እየሠራ ቢሆንም፣ አየርላንድ ኢትዮጵያ ላይ እያደረሰችው ያለው ጫና መቀነስ አለመቻሉን የሚያስረዳው ደብዳቤው፣ ከዚህ ቀደም በሁለቱ አገሮች የነበሩ ስብሰባዎች ውጤታማ አለመሆናቸውን ገልጿል፡፡ በዚህም አየርላንድ ሕወሓትን በማበረታትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባልነቷን ተገን በማድረግ፣ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጥብቅ የሆነ ውሳኔ እንዲተላለፍ እየገፋፋች መሆኑን በደብዳቤው ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የአየርላንድ መንግሥት ያለማቋረጥ እየካሄደው ካለው የበረታ የጠላትነት እንቅስቃሴ እንዲቆጠብ፣ ለአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በላከው የአቤቱታ ደብዳቤ አቅርቧል፡፡

በመሆኑም ሁለቱም አገሮች ገንቢ በሆነና ዓለም አቀፍ ሕጉን በጠበቀ መልኩ ለመነጋገር የሚረዱ ሁኔታዎችን በማመቻቸት፣ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴውን ማስቀጠል እንደሚሻ ጠይቋል፡፡

አቶ ደመቀ ለአየርላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በጻፉት ደብዳቤ ከሚኒስትሩ ጋር ለመነጋጋር ዝግጁ መሆናቸውን እንዲሁም፣ በመከባበርና የአገሪቱን ሉዓላዊ እኩልነት ባከበረ መልኩ በመነጋጋገር በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት ያለበትን ሁኔታ መገምገም እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

 የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር) ዓርብ ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በቲዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጹሑፍ፣ አየርላንድ ላለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያን በማያባራ መልኩ እየከሰሰችና እየጎነተለች ለማዳከም ስትሠራ መቆየቷን የገለጹ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት አሁንም በተደጋጋሚ ቅሬታውን ቢያቀርብም በአገሪቱ ውድቅ የተደረገበት በመሆኑ፣ ለአየርላንድ መንግሥት የመጨረሻ ማሳሰቢያ ለመስጠት መገደዱን አስታውቀዋል፡፡

አክለውም የሁለቱ አገሮች ግንኙነት በሚያሳዝን ደረጃ ዝቅተኛ በሚባል ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በሌላ ዜና አሜሪካን ጨምሮ አምስት የአሮፓ አገሮች በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርት መባባስና የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት መቆራረጥ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል፡፡

ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. አውስትራሊያ፣ አሜሪካ፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ ዴንማርክና ኔዘርላድ ባወጡት የጋራ አቋም መግለጫ የፌደራል መንግሥትና የሕወሓት ታጣቂዎች ግጭቱን በአስቸኳይ አቁመው ያልተቋረጠ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንዲኖር ጠይቀዋል፡፡

የኤርትራ በጦርነቱ መሳተፍን እናወግዛለን የሚለው መግለጫው የኤርትራ ወታደሮች ከሰሜን ኢትዮጵያ ለቀው እዲወጡና የውጭ ኃይሎች ጦርነቱን ሊያባብስ ከሚችል ንግግር እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡ አንደ አዲስ ባገረሸው ጦርት ሌላ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይከሰት ሥጋት እንዳላቸው የገለጹት አገሮቹ፣ በንጹኃን ላይ የሚደረግ የትኛውም ዓይነት ጥቃት እንደሚያወግዙ በመግለጫው አቅርበዋል፡፡

በመሆኑም ሁለቱም አካላት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ ተረድተው በአፍሪካ ኅብረት የተጀመረው ሰላማዊ የድርድር ሒደት ውስጥ በመግባት ለኢትዮጵያውን የመጨረሻ መፍትሄ እንዲያመጡ ጠይቀዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መለስ ዓለም (አምባሳደር) የአገሮቹን የጋራ አቋም አስመልከተው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የቋንቋ አጠቃቀም ካልሆነ በስተቀር መግለጫው ከዚህ በፊት ሲወጡ ከነበሩት መግለጫዎች የተለየ ነገር የለውም ብለዋል፡፡  ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ሁልጊዜም ቢሆን ለሰላም ያለው ዝግጁነትና አቋም ግልጽ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹በየቦታው ምርት እየገዙ የሚያከማቹ ከበርቴ ገበሬዎች ተፈጥረዋል››

አቶ ኡስማን ስሩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር...

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...