እንነሳ ይሆን፤ እኛም ከንቅልፋችን፤ ሁሉን ነገር ረስተን፡፡
እጅህ ውስጥ ያለችው ኧረ ነፍሴስ ብትሆን
ምንም አታስታውስ፤ ነፋስ እንዳሸዋ
ዘምባባውን ረስቶ ወደ ሚሸሹበት ረጃጅሞችና ሰማያዊ ጥላ
ወጨፎ ሲጠርገው የጨላለመውን ያንን ምድረበዳ?
አሁን እንደፊት ታስታውስ ይሆን፤ ምንም እንኳን ቢያልፉ
አንድ ሺ ጠፈሮች፤ፕላኔቶችንም እዚያ ሲያናፍሱ
ያን ባዶ ሕዋህው በጎረና ልሳን?
የነፍሴ ነፍስ ሆይ፤ ፈጽሞ አይረሳም አንዲት ቃልም ብትሆን፤
ፍቅሬ ወለላዬ፤ አንጋፈጠውም ለየብቻችን
የጠፉት ፀሐዮች ምድረበዳውን፡፡
የምትዞርበት የኛለም ብትሆንም ሕዋህውን ጭምር ከቶ አንፈራውም፤
አብረን እንሄዳለን አንለያይም
ለየብቻ ሆነን አንጋፈጠውም ያንን ዘላለም፡፡
- ከሳራ ቲስዴል (1884 – 1930) ስድ ትርጉም በዳዊት ዘኪሮስ (1925 – 2007)