Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአስከፊነቱ የጎላው የአከርካሪ አጥንት በሽታ

አስከፊነቱ የጎላው የአከርካሪ አጥንት በሽታ

ቀን:

በዓለም አቀፍ ደረጃ አንድ ቢሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የአከርካሪ አጥንት በሽታ ተጠቂ ሲሆኑ፣ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ሕሙማን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙት ናቸው፡፡ አንድ መረጃ እንደሚሳየው በተለይም በኢትዮጵያ በርካታ ሰዎች በዚህ በሽታ ተጠቂ የሚሆኑት የማኅበረሰብ ክፍሎች አብዛኛዎቹ በገጠራማ ሥፍራ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ በግብርና፣ በኮንስትራክሽን፣ በሸክም በተያያዥ ሥራዎች የሚሳተፉ ሰዎች የዚህ ችግር ገፈት ቀማሽ እየሆኑ ይገኛል፡፡

ኅብረተሰቡን ከዚህ ችግር ለመታደግ ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ከስፓይን ኸልዝ ኢንሺየቲቭ፣ ከጤና፣ ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ እንዲሁም ከትምህርት ሚኒስቴሮች ጋር እየሠራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

‹‹እያንዳንዱ የአከርካሪ አጥንት ዋጋ አለው›› በሚል መሪ ቃል  ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም. የተከበረው ዓለም አቀፍ የአከርካሪ አጥንት ቀን በኢትዮጵያ ለአሥርኛ ጊዜ የታሰበው በአካል ብቃት እንቅስቃሴና በፓናል ውይይት ነው፡፡

የማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ 52 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች እየሞቱ የሚገኙት ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ነው፡፡

ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፣ ተገቢውን የሆነ የሕክምና አገልግሎት አለማግኘት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ ለአከርካሪ አጥንት በሽታ ይዳርጋል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ይኼንን በሽታ ለመግታት መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አለበት ብለዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የአከርካሪ አጥንት በሽታ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን፣ አብዛኛው የማኅበረሰብ ክፍልም ስለበሽታው አስከፊነት በቂ የሆነ ግንዛቤ አለመኖሩ ችግሩን ይበልጥ እንዳጎላው አስረድተዋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የሕክምና አገልግሎት አለመሰጠቱ ችግሩ እንዲባባስ አድርጎታል የሚሉት አቶ ወንዱ፣ ይኼንንም ታሳቢ በማድረግ መንግሥት በተለያዩ የሕክምና ተቋሞች ላይ አገልግሎት መስጠት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

የአከርካሪ አጥንት በሽታ እንደሌሎች በሽታዎች ሁሉ መታየት እንዳለበት ገልጸው፣ የበሽታውን አስከፊነት በመረዳት በየትምህርት ቤቶች፣ በኮንስትራክሽን ሥራ ለተሰማሩ ተቋሞች፣ ለመካኒኮች እንዲሁም ደግሞ በገጠራማ ሥፍራ ለሚገኙ ሰዎች ግንዛቤ መስጠት እንደሚገባ አክለው ገልጸዋል፡፡

የስፓይን ኸልዝ ኢንሺየቲቭ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰላም አክሊሉ (ዶ/ር) እንዳብራሩት፣ ጥናቶቹ እንደሚያሳዩት ከሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአከርካሪ አጥንት በሽታ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ቢሊዮን በላይ ሆኗል፡፡

ለዚህ በሽታ ተጋላጭ የሆኑ አብዛኛዎቹ ሰዎች በበሽታው የተያዙበትን ምክንያት እንኳን በቅጡ የማያውቁ መሆናቸው፣ በተለይም ደግሞ ችግሩ የሚያስከትለው ከባድ ዕቃ በሚሸከሙ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአከርካሪ አጥንት በሽታ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርና ያለው የሕክምና ተቋም አለመመጣጠን አንዱ ተግዳሮት ነው የሚሉት ሥራ አስፈጻሚዋ ይኼንን ችግር ለመግታት መንግሥት የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በአፍሪካ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ሰዎች በበሽታው ተጋላጭ መሆናቸውንና በሽታውን ለመግታት የአመጋገብ ሥርዓትን ማስተካከል እንዲሁም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...