Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትቀነኒሳ በቀለ የግራንድ አፍሪካ ኢምፓክት ሽልማትን አሸነፈ

ቀነኒሳ በቀለ የግራንድ አፍሪካ ኢምፓክት ሽልማትን አሸነፈ

ቀን:

የአሜሪካዋ ኒው ኮሮልተን ከተማ ኦክቶበር 16ን በቀነኒሳ ስም ሰይማለች

በየዓመቱ በአሜሪካ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚያሳትፈው፣ በዋሽንግተን ዲሲ የሚከናወነው የታላቅ አፍሪካ የጎዳና ሩጫ ዘንድሮም ለአራተኛ ጊዜ ተከናውኗል፡፡ በዚያው የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት በዚህ የጎዳና ውድድር አንጋፋ አትሌቶች የተካፈሉ ሲሆን፣ የምንጊዜም የረዥም ርቀት ኮከብ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል፡፡

ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. በኖቫ ኮኔክሽን አማካይነት በተሰናዳው የጎዳና ውድድር ላይ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተካፈሉ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ ፋጡማ ሮባ፣ ሚሊዮን ወልዴ፣ ቁጥሬ ዱለቻ እንዲሁም ቀነኒሳ በቀለ የተገኙ ሲሆን፣ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በውድድሩ ተገኝተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በማግስቱ በተከናወነው የአፍሪካ ኢምፓክት የዕውቅና መርሐ ግብር ቀነኒሳ በቀለ በስፖርት ዓለም በተለይ ለአትሌቲክስ ላበረከተው አስተዋጽኦ፣ የዓመቱን የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ሽልማት ተጎናጽፏል፡፡

ከዚህም ባሻገር የአሜሪካዋ ኒው ኮሮልተን ከተማ አስተዳደር በየዓመቱ ኦክቶበር (ጥቅምት) 16ን በቀነኒሳ ስም እንዲሰየም ወስኗል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ በዳያስፖራው ማኅበረሰብ እየተለመደ የመጣው የታላቅ አፍሪካ ሩጫ ላይ የእረኛዬ የቴሌቪዥን ድራማ ደራሲዎችና ተዋንያኖች የተጋበዙ ሲሆን በፊልሙ ዘርፍ ላበርከቱት አስተዋጾም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

እንደ አዘጋጁ ጋሻው አበዝ (ዶ/ር) አስተያየት ከሆነ የሽልማቱ ዋና ዓላማ፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን በማክበር፣ ሌሎች እንዲነሳሱ ለማበረታታት ነው፡፡ ተሸላሚዎቹም የተሰጣቸውን ሽልማት በቀጣይ የበለጠ ለሕዝብና አገር የሚበጅ አበርከቶ እንዲኖራቸው ስንቅ ይሆናቸዋል በማለትም አስረድተዋል፡፡

ከዝግጅቱ ባሻገር የበጎ ሥራ ማከናወን ግቡ ያደረገው ታላቅ የአፍሪካ የሩጫ ዝግጅት ከኅብረት ለበጎ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር እንደሚሠራ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም የዳያስፖራውን ማኅበረሰብ ያሰባሰበውን በአራተኛው ታላቅ አፍሪካ ሩጫ መድረክን በመጠቀም አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ለሚመራው ኅብረት ለበጎ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለሚያስገነባው ሆስፒታል የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቡን አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ተመዝጋቢዎች ያሻቸውን የገንዘብ መጠን በትኬት ሽያጩ ላይ ጨምረው እንዲገዙ የቀረበላቸው ሲሆን፣ ለበጎ አድራጎት የሚውለው ገንዘብም መሰብሰቡ ተጠቅሷል፡፡

በ5 ኪሎ ሜትር ውድድሩ በአዋቂ ወንዶች አብርሃም ስሜ፣ አሸናፊ ከተማና ግርማ ኢላላ ተከታትለው በመግባት ባለድል ሲሆኑ፤ በአዋቂ ሴቶች ጋዲሴ ደሪባ፣ ገዛኸኝ ገመዳና አንጋፋዋ አትሌት ቁጥሬ ዱለቻ ከአንድ እስከ ሦስት ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አሸንፈዋል፡፡

በሕፃናት ዘርፍ ወንዶች ዮናታን ዳዊት ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ፣ ዮናታን ንጉሤና ናትናኤል ቢኒያም ሁለተኛና ሦስተኛ ይዘው አጠናቀዋል፡፡ በሴቶች አርሴማ ፀጋዬ፣ እንዲሁም የቀነኒሳ በቀለ ልጆች ኤልናታ ቀነኒሳና ኤልሳም ቀነኒሳ ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ፈጽመዋል፡፡

በአራተኛው የታላቅ ሩጫ የ2022 ቶዮታ መኪና ዕጣ ለዕድለኛ ተሰናድቶ የነበረ ሲሆን፣ ዕጣው የደረሰው ተሳታፊ ሽልማቱን መረከቡ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...