Wednesday, April 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበመካከለኛና በረዥም ርቀት ደምቀው የነበሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ማራቶንን በድል ጀምረውታል

በመካከለኛና በረዥም ርቀት ደምቀው የነበሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ማራቶንን በድል ጀምረውታል

ቀን:

በሳምንቱ በተለያዩ አገሮች በተከናወኑ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደምቀው አሳልፈዋል፡፡ በአምስተርዳም በተደረገው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ድል ማድረግ ችለዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2016 የሪዮ ኦሊምፒክ ውድድሯ በኋላ በጉዳት እንዲሁም በወሊድ ምክንያት ከአትሌቲክስ ውድድር ጠፍታ የነበረችው የቀድሞ 10 ሺሕ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቷ አልማዝ አያና በመጀመሪያዋ የማራቶን ተሳትፎዋን በድል ተወጥታለች፡፡

አልማዝ ርቀቱን 2፡17፡20 በሆነ ሰዓት ያጠናቀቀች ሲሆን፣ የቦታውን ሰዓት ከማሻሻል ባሻገር፣ በመጀመርያ የማራቶን ተሳትፎ ፈጣን ሰዓት ያጠናቀቀች አትሌት መሆን ችላለች፡፡ አልማዝ ከሪዮ ኦሊምፒክ የ10 ሺሕ ሜትር ክብረ ወሰን ካሳካች በኋላ፣ በወሊድና በከባድ የጉልበት ጉዳት ቀዶ ሕክምና ከውድድር ርቃ መቆየቷ ይታወሳል፡፡

ለዓመታት ደብዛዋ ጠፍቶ የከረመችው አልማዝ፣ ከዚህ ቀደም በኬንያዋ አንጄላ ታኑይ ተይዞ የነበረውን 2፡17፡57 ክብረ ወሰን ጭምር ማሻሻል የቻለችው፣ 37 ሰከንዶችን በማሻሻል የቦታው ሰባተኛ ምርጥ ሰዓት ተደርጎ ተመዝግቦላታል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከወራት በፊት በሀምቡርግ የመጀመሪያ ማራቶን ውድድሯን አድርጋ፣ በመጀመሪያ ተሳትፎዋ የቦታውን ምርጥ ሰዓት መያዝ የቻለችው የዓለም ዘርፍ የኋላው የነበረች ሲሆን፣ በወራት ልዩነት ውስጥ በአልማዝ መያዙ በርካቶችን አስገርሟል፡፡ 

‹‹ለዚህ ቃላት የሉኝም፡፡ ይህ ውጤት ለእኔ በጣም ልዩ ነው፡፡ በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ፤›› በማለት አልማዝ አስተያየቷን ለጋዜጠኞች ሰጥታለች፡፡

የመጀመሪያውን አጋማሽ 69፡26 በሆነ ጊዜ ያጋመሰችው አልማዝ፣ 38ኛ ኪሎ ሜትር ቆርጣ በመሄድ ማሸነፍ ችላለች፡፡ አልማዝ ከሪዮ ኦሊምፒክ ተሳትፎዋ በኋላ በጉዳት ክፉ ጊዜ ማሳለፏን ገልጻ ለድሉ ቤተሰቧን፣ አሠልጣኞቿን እንዲሁም ማናጀሮቿን አመስግናለች፡፡ አትሌቷ ባለፈው ወር በእንግሊዝ ኒውካስትል ከተማ በተሳተፈችበት የመጀመሪያ የግማሽ ማራቶን ውድድር፣ 1፡07፡10 በመግባት ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

አትሌቷ የኤንኤን አትሌቲክስ ቡድንን የተቀላቀለች ሲሆን፣ በቀጣይ በርካታ የጎዳና ውድድሮች ላይ ትካፈላለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አምስተርዳም ከአልማዝ ባሻገር፣ በመካከለኛ ርቀት የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቷን ገንዘቤ ዲባባን ማስመልከት ችሏል፡፡ በ1,500፣ 3,000 ሜትር እንዲሁም 5,000 ሜትር ርቀቶች ላይ ብቻ በመካፈል የምትታወቀው ገንዘቤ፣ በማራቶን 2፡18፡05 በሆነ ጊዜ ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ፀሐይ ገመቹ 2፡18፡59 ሦስተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡

የዓለም 1,500 ሜትር ክብር ወሰን ባለቤቷ ገንዘቤ፣ ለረዥም ጊዜ ከውድድር ርቃ ለማራቶን ዝግጅት ስታደርግ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በ2020 የመጀመርያውን ግማሽ ማራቶን በቫሌንሽያ አድርጋ 65፡18 በሆነ ሰዓት አጠናቃ፣ የምንጊዜም የግማሽ ማራቶን የመጀመሪያ ተሳትፎ ምርጥ ሰዓት ማስመዝገብ መቻሏ ይታወሳል፡፡

በበርካታ የቤት ውስጥና በዳይመንድ ሊግ ድል ማድረግ የቻለችው ገንዘቤ፣ የማራቶን ተሳትፎዋንም በስኬት ተቀላቅላለች፡፡ በቀጣይ በበርካታ የጎዳና ውድድሮች ላይ ከሚጠበቁ እንስት አትሌቶች መካከል አንዷ እንደምትሆን ይጠበቃል፡፡

በሌላ በኩል በአምስተርዳም ማራቶን የወንዶች ውድድር ፀጋዬ ጌታቸው 2፡04፡49 በሆነ ጊዜ ሲያሸንፍ፣ ሌላው ኢትዮጵያዊ ባዘዘው አሳመረ 2፡04፡57 ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ ጌታቸው የመጀመሪያው ግማሽ ማራቶን 61፡57 በሆነ ሰዓት ማጋመስ የቻለ ሲሆን፣ በታምራት ቶላ ተይዞ የነበረውን 2፡03፡39 ሰዓት ሊያሻሽል ይችላል የሚል ግምት አግኝቶ ነበር፡፡ ኬንያዊው ታይታስ ኪፕሪቶ 2፡04፡54 ሦስተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡

በሳምንቱ ከአምስተርዳም ባሻገር በሌሎች የተለያዩ አገሮች የማራቶን ውድድሮች የተደረጉ ሲሆን በቶሮንቶ ካናዳ፣ በደቡብ አፍሪካና በህንድ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በቶሮንቶ ማራቶን ይሆንልኝ አዳነ 02፡07፡18 አንደኛ፣ በሴቶች ገለቴ ቡርቃ 2፡24፡31 ሁለተኛ ሲሆኑ በደቡብ አፍሪካ በተደረገ የማራቶን ውድድር በሴቶች መሠረት ድንቄ አንደኛ ሆና አጠናቃለች፡፡ በህንድ ኒው ዴልሂ በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር ጫላ ረጋሳ በ60፡30 አንደኛ፣ ሌላው ቦኪ ዲሪባ በ60፡34 ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡.

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...