Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹አይሁዶች ወደ ሞት ጎዳና እየሄዱ እንኳ ያነብባሉ››

ትኩስ ፅሁፎች

ዶክተር ሚራዥ ኒክሎል የኦሽዋትዊዝ ሚስጥር በሚለው መጽሐፋቸው ‹‹እኛ አይሁዶች ጥሩ የንባብ ባህል አለን፡፡ በናዚ የማጎሪያ ካምፖች ውስጥ ሆነን ሞትን እየተጠባበቅን በሚስጥር መጽሐፍ እያዞርን እናነብ ነበር፤›› ሲሉ ከትበዋል። ይህንም አስመልክቶ ዘነበ ወላ የስብሐት ማስታወሻ ላይ፣ በእያንዳንዱ የአውሮጳና የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በየዩኒቨርስቲው ከሰባት ያላነሱ የአይሁድ ፕሮፌሰሮች ይገኛሉ ይለናል። ቀጥሎም አይሁዶች አንባቢዎች በመሆናቸው ህልውናቸውንና ሀገራቸውን ታድገዋል፡፡

የአይሁዶች የንባብ ፍቅር ከፍ የሚያደርገው ደግሞ ቪክቶር ፍራንክል የተባለው እውቁ የስነ ልቦና ባለሙያና የሎጎ ቴራፒ የስነ ልቦና ህክምና መስራች በናዚ ካምፕ ሶስት ዓመት በቆየበት ጊዜ  የአይሁድ ወጣቶች መጻፍ ሰርቀው ያነቡ እንደነበር  ይገልጻል፡፡ ‹‹ቴሪዚን ሽታት ከተባለው የማጎሪያ ካፕ ወደ ኦሽዋትዊዝ ማጎሪያ ካምፕ እንዲሄዱ ሲነገራቸው፣  ከ1000 የማያንሱ ወጣቶች በቴሪዝን ሽታት ውስጥ የሚገኘውን ቤተ መጻፍ በመሉ ሰርቀው ሁሉም በሻንጣቸው ይዘው እንደሄዱ ይነግረናል። ልብ አደርጉ ወጣቶቹ ወደሞት እንደሚሄዱ እያወቁ እንኳ በንባብ ውስጥ ትርጉም ያለው ህይወት መኖር ችለዋል። 

የእኛው ንጉስ ዘርዓ ያዕቆብም የንባብ ባህል እንዲዳብር በየቤተክርስትያኑ ያሉ መጻፍት ለንባብ ክፍት እንዲሆኑና ምዕመኑ እንዲያነብ ያደርጉ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ። በደርግ ጊዜም ከ70ሺ በላይ የንባብ ቤቶች እንደነበሩ ደራሲ  እንዳለ ጌታ ከበደ ከትቧል። አሁን ግን  ቤተ መጻሕፍት የአንድ ለአምስትና የልማት ቡድን መወያያ እንደሆኑ የሚጽፈው ደራሲው የንባብ ባህልም ደካማ አንደሆነ ይናገራል። አዎ የንባብ ባህላችን ደክሟል ፣ ለድክመቱ ደግሞ የመንግስት ፖሊሲዎችና የግላችን ተነሳሽነት በምክንያትነት ይሸከማሉ የሚል እምነት አለኝ። የመንግስት ፖሊሲዎች የትውልዱን የንባብ ባህል ሊያሳድግ የሚችል  ፖሊሲ ማውጣትና መተግበር እንዲሁም ወላጆች እንዲሁም ግለሰባዊ ተነሳሽነት ተጨምሮበት የንባብ ባህላችን እንዲያድግ ቢደረግ መልካም ነው።

  • አቡ ኬክሃኒ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ የጻፈው
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች