Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የሚያነብ ሰው እና የማያነብ ሰው!

ትኩስ ፅሁፎች

የሚያነብ ሰው እና የማያነብ ሰው አእምሮ ልክ ደጋ ላይ በእንክብካቤ እንዳደገ ትልቅ የዋርካ ዛፍ እና በረሃ ላይ እንደበቀለ የቀነጨረ ዛፍ ይመስላሉ። ስለመኖር ካነሳን ሁለቱም ዛፎች ይኖራሉ። የደጋው ዋርካ ዛፍ በቂ እርጥበት እና ለም አፈር ስለሚያገኝ አድጎ ይንሰራፋል። ለአእዋፋት ጎጆ መስሪያ መጠለያ፣ ለእንስሳት ከፀሐይ መጠለያ፣ ለደከመው ሰው ማረፊያ ይሆናል። የሚያነብ ሰው አእምሮም እንደዚሁ ነው። ለሰዎች በችግራቸው ጊዜ መፍትሔ ይዞ የሚገኝ የለፉበትን ያህል የሚክስ ሰዎች የሚተማመኑበት እና ራሱን የሚጠቅም ይሆናል።

ለዛፉ ሁሉንም ፈሳሽ ብንደፋበት ሊያደርቁት የሚችሉትን ፈሳሽ ኬሚካሎችን ልንደፋ ስለምንችል መጠንቀቅ እንዳለብን ሁሉ ለአእምሮአችንም የሚጠቅመውን ነገር መመገብ አለብን መምረጥም አለብን።

በሌላ በኩል ምንም ለም አፈር እና እርጥበት በሌለበት በረሃ ላይ የበቀለች ዛፍ  ትቀነጭራለች እንጅ አታድግም። የግድ እንድታድግ እና እንድትንሰራፋ የምትመገበው ነገር ያስፈልጋታል። የምትመገበው ከሌላት ለራሷም የምትጠቅም አትሆንም ብዙም ሳትቆይ ልትደርቅ ትችላለች ወይም ጨርሳ እስከምትጠፋ እንደ ቀነጨረች ትቀራለች።

የማያነብ ሰውም ራሱን አይጠቅምም ለሌሎችም መፍትሔ መሆን አይችልም አእምሮው እንደቀጨጨ ሳይጠቀም ሰው ሳይጠቅም ሕይወቱ ያልፋል።

  • ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል- ዋልያ መጻሕፍት መደብር እና ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ባዘጋጁት መርሐ ግብር ላይ ስለ ንባብ ከተናገሩት (ቡክ ፎር ኦል)
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች