Thursday, February 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልቅሬታ የቀረበበት አርክውድ ፊልም አዳዲስ መርሐ ግብሮቹን አስተዋወቀ

ቅሬታ የቀረበበት አርክውድ ፊልም አዳዲስ መርሐ ግብሮቹን አስተዋወቀ

ቀን:

በኢትዮጵያ የፊልም ዘርፉን ለማሳደግ፣ የጥበቡንም ባለሙያዎች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የሚገልጸው፣ ‹‹አርክውድ ፊልም›› ሦስት አዳዲስ መርሐ ግብሮችን አስተዋውቋል፡፡

በውጭ አገሮች እንዳሉት እንደ ቦሊውድ ዓይነቶች ተቋማት መሰል አርክውድ ብሎ የሚንቀሳቀሰው ተቋሙ፣ ዓመታዊ የፊልም ሽልማት፣ የቀጥታ የፊልም አገልግሎትና አዲስ የፊልም መንደር ለመገንባት ማቀዱን ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ሆቴል በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ከነዚህ መርሐ ግብሮች በተጨማሪ የፊልም ባለሙያዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በቅርቡ የአክሲዮን ሽያጭ እንደሚጀምር የአርክውድ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ አርሴማ ወርቁ ተናግረዋል፡፡

ሥራ አስኪያጇ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የአርክውድ የፊልም ኢንዱስትሪ የአክሲዮን ሽያጭ በዋናነት ባለሙያዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግና ሙያውን ወደ አንድ ዕርምጃ ከፍ የሚያደርግ ነው፡፡

የአርክውድ ዲጂታል የፊልም ማሰራጫ አዳዲስና የታዩ የፊልሞችን ሰንዶ የሚይዝ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ አርሴማ ፊልሞችን በአንድ የሚያቀርብ ስለሆነ ከብዙ አቅጣጫ ዘላቂ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡

የቀጥታ ማሰራጫው ለኢትዮጵያ ፊልም አፍቃሪያን የፊልም ማሳያ መድረክ ብቻ አለመሆኑን፣ የባለሙያዎችን የቅጂ መብት የማስጠበቅና አርቲስቶች ተገቢውን ክፍያ እንዲያገኙ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የፊልም መንደር ለመገንባት ቦታ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆኑን፣ ሲጠናቀቅም ጥናት ያላቸው ፊልሞችን ለመሥራት የሚያስችሉ ዘመናዊ ግብዓቶችን የሚይዝ ይሆናል ብለዋል፡፡

መንደሩ በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ፊልሞችን ለመሥራት የሚያስችል፣ በሙያው መሥራት ላልቻሉ ወጣቶች የፈጠራ ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ተናግረዋል፡፡ የፊልም መንደሩ ዲዛይኑ መጠናቀቁንና ቀጣዩን ሒደት ለሚዲያ እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡

የሚመሠረተው የአክሲዮን ማኅበር ለኢትዮጵያውያን ክፍት መሆኑን፣ አቅሙ በፈቀደ ልክ ኅብረተሰቡ እንዲገዛ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል አርክውድ ያለ ባለሙያው ዕውቅና በአምስት ግለሰቦች ብቻ የአክሲዮን ማኅበርን ማቋቋሙ ተገቢ አይደለም የሚል አስተያየት የሰጡ አሉ፡፡

‹‹አርክውድ ያለ ባለሙያው  ዕውቅና አክሲዮኑን በአምስት ግለሰቦች  የተመሠረተ ነው፤›› ሲሉ ለሪፖርተር ቅሬታ ያቀረቡት የፊልም ባለሙያ አቶ ነቢል እድሪስና ሌሎች ባለሙያዎች ናቸው፡፡

የአርክውድ ባለቤቶች አቶ ኤርሚያስ ታደሰ፣ አቶ ቢንያም ዓለማየሁ፣  ወ/ሮ አርሴማ ወርቁና ሌሎች ባለሙያዎች ተጨምረው የመሠረቱት መሆኑን አስታውሰዋል። የተመሠረተው አክሲዮንም የሁሉም መባሉ ስህተት መሆኑን አስረድተዋል።

አርክውድ   የሰፊው የፊልም ባለሙያዎች ሳይሆን የተወሰኑ ግለሰቦች በመሆኑና ሌሎችንም የባለቤትነት ጥያቄዎች  ሳይመልስ የተመሠረተ በመሆኑ መስተካከል እንዳለበት ገልጸዋል። ሁሉም የፊልም ባለሙያዎች ያልተስማሙበትና የጥቂት ግለሰቦችን ጥቅም ያስበለጠ በመሆኑ፣ ኢንዱስትሪውን የሚጠቅም አይደለም ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ከሐሳብ ጀምሮ ምሥረታው የሁሉም የፊልም ባለሙያዎች እንዲሆን ከስምምነት እንደደረሱ አስታውሰው፣ ሥራ ለማስፈጸም የተመረጡ ግለሰቦች ግን ወደ ራሳቸው ማዞራቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም የአርክውድ የጥቂት የግለሰቦች እንጂ የሁሉም መባል የለበትም ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

በፊልም ባለሙያዎች የቀረበውን ቅሬታ በተመለከተ ሥራ አስኪያጇ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በቀረበው ቅሬታ (ጥያቄ) ዙሪያ ተቀራርበን ለመነጋገር እንሞክራለን፡፡ ለባለሙያዎች በተለይ ሁኔታ የተዘጋጀ አክሲዮን መኖሩን፣ የቀረበው ቅሬታ በተመለከተ ግን ግልጽ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ለፊልም ተዋናይ፣ ለዳይሬክተር ክፍያ የሚከፍለው ፕሮውዲሰሩ መሆኑን ያስታወሱት ሥራ አስኪያጇ አርክውድ መመሥረቱ ባለሙያዎች የሮያሊቲ ጥቅም እንዲያገኙ የሚያደርግና አባል ከሆኑ ደግሞ ጥቅሙ ከፍ ይላል ብለዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ጥቁር የመልበስ ውዝግብና የእምነት ነፃነት በኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ኅዳር ወር ላይ በፓርላማ...

የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚቆጠጠር ገለልተኛ ተቋም ለመመሥረት እንቅስቃሴ ተጀመረ

ከ70 በላይ አዳዲስ የፋይናንስ ተቋማት ዘርፉን ሊቀላቀሉ ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

እስቲ አንገፋፋ!

እነሆ መንገድ። ጊዜና ሥፍራ ተጋግዘው በውስንነት ይዘውናል። መፍጠን ያቃተው...