Wednesday, April 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምበመቶዎች የገደለው ከሚሊዮን በላይ ያፈናቀለው የናይጄሪያ የጎርፍ አደጋ

በመቶዎች የገደለው ከሚሊዮን በላይ ያፈናቀለው የናይጄሪያ የጎርፍ አደጋ

ቀን:

ናይጄሪያ በአሥር ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ በተባለ የጎርፍ አደጋ እየተጠቃች ነው፡፡ የሰውን ሕይወት ከማጥፋቱ ባለፈ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች፣ የመሠረተ ልማት አውታሮችና ሁለት መቶ ሺሕ ቤቶች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ እንዳወደሙባት እየተዘገበ ነው፡፡

መሰንበቻውን በአገሪቱ ከሚገኙት 36 ግዛቶች በ33ቱ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 603 ሰዎች መሞታቸውን፣ ከ2,400 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን፣ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ደግሞ መፈናቀላቸውን የአገሪቱ የሰብዓዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡በመቶዎች የገደለው ከሚሊዮን በላይ ያፈናቀለው የናይጄሪያ የጎርፍ አደጋ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

 

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ዘ ኒውዮርክ ታይምስ እንደዘገበው፣ በጎርፉ የተጠቁ አካባቢዎች ነዋሪዎች ንብረታቸውን ተሸክመው በውኃ በተጥለቀለቁ መንገዶች ላይ በታንኳ ይጓዛሉ። ምግብና ነዳጅ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መንገዶችን አጨናንቀዋል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች የውኃ መጠን ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ቤቶቹ የተንሳፈፉ ይመስላሉ፡፡ በሌሎች ቦታዎች መኪኖቹ በጎርፍ ተውጠዋል፡፡

በመቶዎች የገደለው ከሚሊዮን በላይ ያፈናቀለው የናይጄሪያ የጎርፍ አደጋ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
በናይጄሪያ የደረሰው አስከፊው የጎርፍ አደጋና ያስከተለው ጥፋት ገጽታ

የናይጄሪያ የሰብዓዊ ጉዳዮችና የአደጋ መከላከል ሚኒስትር ሳዲያ ኡመር ፋሩክ፣ በአስከፊ የጎርፍ አደጋዎች 603 ሰዎች መሞታቸውን ባለፈው እሑድ በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸውን ዶቼቬሌ ዘግቧል።ወደ 82,000 የሚጠጉ ቤቶችና 110,000 ሔክታር የእርሻ መሬቶች በውኃ በመጥለቅለቃቸው ሰብሉ መውደሙን ፋሩክ አክለዋል።በእርሻ መሬቶች ላይ እየደረሰ ያለው ውድመት የናይጄሪያ የምግብ አቅርቦትን አሳሳቢ አድርጎታል፡፡ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ መናርንም አስከትሏል፡፡ በአገሪቱ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በተከሰተው ጎርፍ መጥለቅለቅ ለተጎዱ ሐዘናቸውን በትዊተር ገጻቸው የገለጹት ፋሩክ፣ በባህር ዳርቻ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን የአስተዳደር አካላት እንዲያስወጡ አሳስበዋል። ምንም እንኳን ትንበያ ቢደረግም በርካታ ክልሎች ለጎርፉ ሥጋት በቂ ዝግጅት እንዳላደረጉ ያስታወሱት ፋሩክ አክለውም የየአካባቢው ማኅበረሰቦች የአየር ንብረት ትንበያን በቁም ነገር ሊመለከቱት ይገባልም ብለዋል፡፡ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ባለፈው ሳምንት በጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ማኅበረሰቦች 12,000 ሜትሪክ ቶን ምግብ ከናይጄሪያ ስትራቴጅካዊ ክምችት ወጥቶ እንዲከፋፈል አዘዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ቡሃሪ ባለፈው ሰኞ በጎርፉ ምክንያት የደረሰው ውድመት አሳዛኝ መሆኑን ገልጸው፣ በደቡብ የአገሪቱ ክፍል በባዬልሳ ግዛት ብቻ 700,000 ሰዎች ተፈናቅለዋል ብለዋል።የናይጄሪያ የሰብዓዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ወደ 1.4 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው መፈናቀላቸውን አስታውቋል።በናይጄሪያ ከሚገኙት 36 ግዛቶች ጎርፉ በ33ቱ ላይ ጉዳት በማድረሱ ሁሉም የፌዴራል ኤጀንሲዎች የነፍስ አድንና የአደጋ መከላከል ሥራቸውን እንዲያሳድጉ ቡሃሪ  አሳስበዋል፡፡ የሰብዓዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ሳዲያ ኡመር ፋሩክ ባለፈው እሑድ ዕለት ለጎርፉ በቂ ዝግጅት አላደረጉም ባሏቸው የክልል መንግሥታት ላይ ለደረሰው ሞት በተወሰነ መልኩ ተጠያቂ አድርገዋል።በአፍሪካ የዝናብ ወቅት የሚጀምረው በሰኔ ወር ቢሆንም በተለይ በነሐሴ ወር ላይ ከባድ ዝናብ ማስከተሉን የብሔራዊ ድንገተኛ አደጋ አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል።ናይጄሪያ በተደጋጋሚ በአስከፊ ጎርፍ ተጎድታለችየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ በናይጄሪያ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና አገሪቱ በተደጋጋሚ በከባድ የጎርፍ አደጋ ሥጋት ላይ እንደምትወድቅ ገልጿል።ዘገባዎች እንደሚያሳዩት እ.ኤ.አ. በ2012 በ30 ግዛቶች ውስጥ በደረሱት የጎርፍ አደጋዎች ከ400 በላይ ሰዎችን ሲሞቱ 1.3 ሚሊዮን ተፈናቅለዋል።እንደ ተመድ መግለጫ እ.ኤ.አ. በ2019 ከሁለት መቶ ሺሕ በላይ ሰዎች በጎርፍ የተጎዱ ሲሆን 158 ሰዎች ሞተዋል።

በናይጄሪያ በተለይም በባህር ዳርቻዎች አካባቢ በየዓመቱ የጎርፍ መጥለቅለቅ ያጋጥማል፡፡ ነገር ግን የዘንድሮው ጎርፍ ግን ካለፉት አሥር ዓመታት በላይ የከፋ ነው፡፡ ባለሥልጣናቱ ለአደጋው ምክንያት የሚያደርጉት በጎረቤት አገሯ ካሜሩን ከሚገኘው ከላግዶ ግድብ የተትረፈረፈ ውኃ መለቀቁና ባልተለመደ ዝናብ ምክንያት ነው፡፡

አልጀዚራ በደቡባዊ ናይጄሪያ የባይልሳ ግዛት ዋና ከተማ ከሆነችው ዬናጎዋ እንደዘገበው ሰዎች ከባለሥልጣናት ዕርዳታ ለማግኘት ተስፋ በማድረግ ወደ ከተማዋ እየገቡ ናቸው፡፡ ኅብረተሰቡ አሁንም ከሥጋት ያልተላቀቀው ዝናቡ በሚቀጥሉት ቀናትም እንደሚቀጥል መገለጹ ነው፡፡

የውኃው መጠን በአሳሳቢ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱ የውኃ ፍሰቱም አስከፊነቱም መባባሱ ጎርፉም በዚሁ መንገድ መቀጠሉን የአልጀዚራ ዘገባ ያመለክታል፡፡

የጎርፍ አደጋው በናይጄሪያ የሰብዓዊ ቀውስ እንዲባባስ አድርጎታል፡፡ በተለይም በችግር በተሞላው ሰሜናዊ ክልል የተነሳው ብጥብጥ ከሦስት ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ማፈናቀሉን የአገር ውስጥ መፈናቀልን የሚከታተለው ማዕከል አስታውቋል።

እስከ ኅዳር መጨረሻ ድረስ አምስት ክልሎች በጎርፍ አደጋ ሥጋት ላይ መሆናቸውን የሰብዓዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ሳዲያ ኡመር ፋሩክ አስጠንቅቀዋል።

የሚመለከታቸው የክልል መንግሥታት፣ የአካባቢ መስተዳድር ምክር ቤቶችና ማኅበረሰቦች ለጎርፍ በሚጋለጡ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎችን ወደ ከፍተኛ ቦታዎች በማዘዋወር አደጋን እንዲቋቋሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...