Saturday, December 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአዲስ አበባ ከተማን የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን በ‹‹አዲስ እሳቤ ቱሪዝም››

የአዲስ አበባ ከተማን የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን በ‹‹አዲስ እሳቤ ቱሪዝም››

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶችን፣ ታሪካዊ ቅርሶችን እንዲሁም የማይዳሰሱ ትውፊቶችን በአግባቡ ለመጠቀምና በዘርፉ ላይ የሚታዩትን ችግሮች ፈትቶ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ እንዲቻል እንደ አገር ‹‹አዲስ ዕሳቤ ለቱሪዝም›› የተሰኘ አሠራር ተዘርግቶ እየተሠራ መሆኑን የባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው ‹‹አዲስ ዕሳቤ ቱሪዝም›› በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 10 እስከ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ በመስቀል አደባባይ በሚያከብረው የዓለም የቱሪዝም ቀን ላይ የተለያዩ ኩነቶች የሚቀርቡበት መሆኑን፣ ሰኞ ጥቅምት 7 ቀን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

የቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ደስታ ሎሬንሶ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን በተገቢው መንገድ ለመጠቀም ቢሮው የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

‹‹ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፉ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን ማሳደግ ያስፈልጋል፤›› የሚሉት ኃላፊው፣ ‹‹ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ እንደ አገር ወጥ የሆነ አሠራር መዘርጋት ይገባል፤›› ብለዋል፡፡  

በአዲስ አበባ ከተማ እየተሠሩ ያሉትም ሆነ ወደፊት የሚሠሩ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ ለቱሪዝም ዘርፍ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል በማለትም ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን ከመጠቀም አኳያ እዚህ ግባ የሚባል ሥራ አለመሥራቱን፣ ይሁን እንጂ ለመፍትሔው መንግሥትም ሆነ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

ከተለያዩ አገሮች የሚመጡ ቱሪስቶች የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን እንዲጎበኙ፣ ቢሮው የተለያዩ መስህቦችን እንደ አዲስ በመሥራት የቱሪዝም ዘርፉን እያሳደገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በአዲስ አበባ ለሦስት ቀናት በሚካሄደው የዓለም ቱሪዝም ቀን ላይ በፌስቲቫሉ ከሚኖሩት ዝግጅቶች መካከል የሙዚቃ፣ የሰርከስ፣ የማርሽ ባንድ ትርዒት ይገኙበታል፡፡ እንዲሁም የተለያዩ የቱሪዝም ባለድርሻ አካላትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት መድረክም እንደሚሆን አብራርተዋል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን ቢሮ የራሱን ሎጎ በክብረ በዓሉ ላይ የሚያስተዋውቅ መሆኑን፣ ሎጎውም ሲተዋወቅ አዲስ አበባ የቱሪዝም ዕይታ ውስጥ እንድትገባ ትልቅ አማራጭ ይሆናል ብለዋል፡፡

በቅርቡም ኮልፌ በሚገኘው የፖሊሲ ማሠልጠኛ ማዕከል ውስጥ የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ የነፃነት ታጋይ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ ሥልጠና የወሰዱበትን ማዕከል በማልማት የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን እየተሠራ መሆኑን ደስታ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡      

የዓለም የቱሪዝም ቀን መስከረም 17 ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ43ኛ ጊዜ ‹‹አዲስ ዕሳቤ ለቱሪዝም›› በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች መከበሩ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...