Monday, November 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  [ክቡር ሚኒስትሩ መንግሥት ሰሞኑን ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ የጣለውን ክልከላ ማኅበረሰቡ እንዴት እንደተቀበለው ከአማካሪያቸው ጋር እያወሩ ነው]

  • እሺ ተቃውሞ ሰማሁ ነው ያልከኝ?
  • አዎ ክቡር ሚኒስትር። እንዳይገቡ ከተከለከሉት ምርቶች በተወሰኑት ላይ ተቃውሞ ሰምቻለሁ።
  • በየትኞቹ ምርቶች ላይ?
  • በተለይ አርቴፊሻል ፀጉር በመከልከሉ በርካታ ተቃውሞና ትችት በማኅበራዊ ድረገጾች ሲዘዋወር ነበር። 
  • የኡጋንዳዋ ምክትል ፕሬዚዳንት የተናገሩትን ሰምተው ቢሆን ይቃወሙም ነበር።
  • የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት? 
  • አዎ። ሰሞኑን በባህርዳር በተካሄደው የጣና ፎረም ላይ ንግግር አድርገው ነበር። 
  • አዎ። እርስዎም እዚያ ነበሩ። እና ሴትየዋ ምን አሉ? 
  • የኡጋንዳ ወጣት ሴቶች በፀጉራቸው ማጠር ደስተኛ አለመሆናቸውን በቀልድ መልክ ይናገራሉ አሉ።
  • ምን ብለው ይናገራሉ አሉ?
  • ማነው ከአቢሲኒያ ያመጣን! ወደ ኡጋንዳ ባያመጡን ኖሮ እንደ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ፀጉራችን ያምር ነበር እንደሚሉ ተናግረው ነበር።
  • [ሳቅ] የሚገርመው ግን አርቴፊሻል ፀጉር እንዳይገባ መከልከሉን የተቃወሙት ሴቶቻችን አይደሉም ክቡር ሚኒስትር።
  • እንዴ! እና ማነው የተቃወመው?
  • ሸኔ፡፡ 
  • [እየሳቁ] አንተ ደግሞ ቀልድና ቁምነገርህ አይለይም። 
  • ምን ላድርግ ብለው ነው ክቡር ሚኒስትር።
  • ልክ ነህ እንደዚህ ቁምነገር ያዘሉ ቀልዶች ያዝናናሉ። 
  • ልክ ነው ክቡር ሚኒስትር። 
  • ሌላ የሰማኸው ተቃውሞ ነገር የለም? 
  • ልሂቃኑን ጨምሮ አብዛኛው የማኅበረሰብ ክፍል ውሳኔያችንን በከፍተኛ ደረጃ ነው የደገፈው። ግን ደግሞ…
  • ግን ምን?
  • ያው ተቃውሞ ጨርሶ አይጠፋም። በተለይ ተቃውሞው ከራሳችን መዋቅር መመንጨቱ በጣም ያበሳጫ።
  • ከራሳችን ስትል? ከሕዝብ ክንፍ ነው?
  • አይደለም። በየደረጃው ከሚገኙ የፓርቲና የመንግሥት መዋቅሮቻችን ማለቴ ነው።
  • አትለኝም? 
  • እውነቴን ነው ክቡር ሚኒስትር። 
  • እንዴት?
  • በተለይ ውስኪ እንዳይገባ መከልከል የለበትም የሚሉት መብዛታቸው አስገራሚ ነው። 
  • ይህ አስገራሚ አይደለም!
  • እ…
  • አሳፋሪ ነው!
  • አዎ፣ ያበሳጫል ክቡር ሚኒስትር።
  • ግን ውስኪ እንዳይገባ በመከልከሉ ብቻ ሲሉ ነው የተቃወሙት? 
  • ውስኪ ይበሉ እንጂ ምክንያታቸው እሱ እንዳልሆነ ይታወቃል።
  • ምንድነው ምክንያታቸው?
  • ጊዜ ነው 
  • የምን ጊዜ?
  • በእኛ ጊዜ እንዴት ይከለከላል ነው የሚሉት ክቡር ሚኒስትር
  • እነዚህን ነው በጊዜ ማለት!
  • በጊዜ ማለት ሲሉ?
  • በጊዜ መሸኘት!

  [የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ መንግሥት የሰሜኑ ጦርነትን በተመለከተ መረጃ መስጠት ከጀመረ እኔም አንዳንድ ጉዳዮችን ልረዳ ብሎ በጠዋት ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ገብቶ እየጠየቀ ነው]

  • እንደምን አደሩ ክቡር ሚኒስትር?
  • ሰላም። 
  • እንኳን ደስ አልዎት። 
  • ለምኑ?
  • የሰሜኑ ጉዳይ ወደ መደምደሚያው እየተጠጋ ይመስላል።
  • በዚህ ጉዳይ ላይ አትጠይቀኝ አላልኩህም?
  • መንግሥት ዝምታውን ሰብሯል ብዬ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • መንግሥት የተናገረው ነገር አለ እንዴ? 
  • አዎ። ትላንት መግለጫ አውጥቶ ሦስት ከተሞችን መቆጣጠሩን ይፋ አድርጓል። ከዚያ በፊትም የአየር ማረፊያዎችን እንደሚቆጣጠር ገልጿል። 
  • ለነገሩ ከዚህ በኋላ ዝም ማለት ጠቀሜታ የለውም። 
  • አዎ፣ ትክክል ነው። የውጭ አጋሮቻቸው ዝምታውን ተጠቅመው ጫና ለመፍጠር እየሞከሩ ነው። 
  • እኮ። እዚህ ደረጃ ሲደርስ መናገር ተገቢ ነው። ለዚያም ነው መንግሥት የተናገረው። 
  • ቢሆንም ያልገባኝ ነገር አለ ክቡር ሚኒስትር?
  • ምንድነው?
  • መንግሥት በይፋ አየር ማረፊያዎችን እቆጣጠራለሁ ማለቱ ትክልል ነው? የውጭ አጋሮቻቸውን አያስቆጣም?
  • ለምን ያስቆጣል? አየር ማረፊያዎቹ እኮ የፌዴራል መንግሥት ንብረቶች ናቸው። 
  • እሱስ ልክ ነው። 
  • በተጨማሪም የውጭ ኃይሎች አየር ማረፊያዎቹን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ በምዕራባዊያኑ ጭምር የተረጋገጠ ተጨባጭ ማስረጃ በመኖሩ ነው። 
  • በራሳቸው የተረጋገጠ መረጃ አለ? 
  • አዎ። ራሳቸው ያረጋገጡትና በይፋም የተናገሩት ነው።
  • እንደው ግን ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ከአየር ማረፊያዎቹ ውጪ ወደ ዋና ከተማዋ አይገባም?
  • በዋና ከተማ አየር ማረፊያ የለም እንዴ? 
  • አለ? 
  • ስለዚህ ይገባል። በዚያ ላይ አየር ማረፊያዎችን ብቻ አይደለም መንግሥት ለመቆጣጠር የወሰነው።
  • ሌላ ምን አለ?
  • የፌዴራል መንግሥት መሠረተ ልማቶችንም ይቆጣጠራል።
  • የትኞቹን ማለት ነው? 
  • ለምሳሌ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን፣ የኃይል ማመንጫና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን፣ አገር አቋራጭ የትራንስፖርት መንገዶችን ይቆጣጠራል።
  • ዩኒቨርሲቲዎችም አሉ። 
  • እዎ። የመከላከያ ሠራዊቱ ይጠቀምባቸው የነበሩ የማዘዣ ማዕከላትንም ይቆጣጠራል። 
  • አሁን የገለጿቸው በሙሉ እኮ በዋና ከተማዋ ይገኛሉ።
  • ስለዚህ ይቆጣጠራቸዋል። 
  • እነዚህን ሁሉ ተቋማት ከሚቆጣጠር ሌላ ነገር ቢያደርግ አይሻለውም?
  • ምን?
  • ከተማዋን መቆጣጠር!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  አነስተኛ ካፒታል ያላቸው ባንኮች በመዋሃድ አቅም እንዲፈጥሩ ጉምቱው የፋይናንስ ባለሙያ መከሩ

  የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ እንዳይገቡ የሚከለክለውን ሕግ የማሻሻል...

  በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ብሔራዊ አገልግሎት የተካተተበት አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

  የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ወይም የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ወጣቶች በፈቃደኝነት...

  ነባር ‹‹ላዳ›› ታክሲዎችን መሸጥና መለወጥን ጨምሮ ለሌላ ማስተላለፍ ተከለከለ

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለምዶ ‹‹ላዳ ታክሲ›› ተብለው የሚታወቁትን...

  የምግብ ዘይት አምራቾች ምርቶቻቸው ለገበያ ባለመቅረባቸው ተጨማሪ ለማምረት ተቸግረናል አሉ

  ፌቤላ ፋብሪካ ማምረት አቁሟል ሸሙ ፋብሪካ 5.6 ሚሊዮን ሊትር ተከማችቶበታል ፋብሪካዎች...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...

  ከመሬት ለአራሹ ወደ ደላላ የዞረው የመሬት ፖለቲካ

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ለመጀመርያ ጊዜ...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [የተቃዋሚ ፓርቲው ትይዩ ሚኒስትር ክቡር ሚኒስትሩ ጋ ደውለው መንግሥት በሙሰኞች ላይ ለመውሰድ ስላሰበው የሕግ ዕርምጃ ሐሳብ እየተለዋወጡ ነው]

  ሄሎ… ማን ልበል? ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስጥልኝ… ማን ልበል? የእርስዎ ትይዩ ነኝ፡፡  አቤት? ያው ፓርቲዬን ወክዬ የፍትሕ ሚኒስትሩ ትይዩ ነኝ ማለቴ ነው፡፡ ኦ... ገባኝ… ገባኝ...  ትንሽ ግራ አገባሁዎት አይደል? ትይዩ...

   [ክቡር ሚኒስትሩ እራት እየበሉ መንግሥትን በሚተቹ ጋዜጠኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን ዕርምጃ የተመለከተ መረጃ እየቀረበላቸው ነው]

  ለጋዜጠኞቹ መንግሥትን እንዲተቹ መረጃ የሚሰጧቸው ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ እነሱ አይደሉም፡፡ እና የትኞቹ ናቸው? እዚሁ ከተማችን የሚገኙ ምዕራባውያን ናቸው። እንዴት ነው መረጃውን የሚያቀብሏቸው? እራት እያበሉ ነው። ምን? አዎ፣ እራት ግብዣ ይጠሯቸውና መተቸት...

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከፕሮፓጋንዳ ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢው ጋር ስለ ሰሜኑ የሰላም ስምምነት ትግበራ መረጃ እየተለዋወጡ ነው]

  እኔ ምልህ፡፡ አቤት ክቡር ሚኒስትር? የሰሜኑ ተዋጊዎች ከሠራዊታችን ጋር መቀራረብ ጀመሩ የሚባለው እውነት ነው?  አዎ። እውነት ነው ክቡር ሚኒስትር።  ከማንም ትዕዛዝ ሳይጠብቁ ነው ከእኛ ሠራዊት ጋር መቀላቀል ጀመሩ...