Monday, November 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴን የዘከረው ዓውደ ርዕይ

  ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴን የዘከረው ዓውደ ርዕይ

  ቀን:

  በኢትዮጵያ የዘመናዊ መንግሥት ታሪክ በተለይ በ20ኛው ምታመት የመጀመርያ ሩብ ሁነኛ ሥፍራ ነበራቸው፡፡ ከአዲስ አበባ ከንቲባነት እስከ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት፡፡ መሳ ለመሳም ከጥንታዊው አገራዊ ትምህርት ከሚቀዳው ዕውቀታቸው በሰረፀውና ብሂልን ከባህል ባዛመዱ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻቸውም ይታወቃሉ፡፡ ከሃያ በላይ ድርሰቶችን የታሪክ መጻሕፍት፣ የባህር ማዶ የጉዞ ማስታወሻዎችንም አፍርተዋል፡፡ ማን ቢሉ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ (1870 -1931) ነው መልሱ፡፡

  ከብላቴን ጌታ ኅሩይ የታሪክና የሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻቸው መካከል ‹‹ኢትዮጵያና መተማ (የአፄ ዮሐንስ ታሪክ ባጭሩ)፣ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ ከንግሥተ ሳባ እስከ ታላቁ የዓድዋ ድል፣ ‹‹ወዳጄ ልቤ፤ የሰውን ጠባይና ኑሮ በምሳሌ የሚገልጽ፣ ‹‹የልዕልት ወይዘሮ መነን መንገድ በኢየሩሳሌምና በምስር፣ ‹‹በኢትዮጵያ የሚገኙ በግዕዝና በአማርኛ ቋንቋ የተጻፉ የመጻሕፍት ካታሎግ፣ ‹‹ማኅደረ ብርሃን ሀገረ ጃፓን፣ ‹‹ለልጅ ምክር ለአባት መታሰቢያ፣ ‹‹የልብ አሳብ፤ የብርሃኔና የጽዮን ሞገስ ጋብቻ፣ ‹‹ጎሀ ጽባሕ፣ ‹‹አዲስ ዓለም፤ የቅኖችና የደግ አድራጊዎች መኖሪያ ይገኙበታል፡፡

  ባሕሩ ዘውዴ (ፕሮፌሰር) አሰናድተውት በ2009 ዓ.ም. የታተመው ‹‹የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በአውሮፓና መካከለኛው ምሥራቅ›› ብላቴን ጌታ ኅሩይ በ1903 ዓ.ም. ያዘጋጁትና በረቂቅ ደረጃ የነበረ የጉዞ ማስታወሻም ተጠቃሽ ሥራቸው ነበር፡፡

  እኚህን ታላቅ ኢትዮጵያዊ የሚዘክር ልዩ መርሐ ግብር የጥንት መኖሪያ ቤታቸውን ጽሕፈት ቤቱ ባደረገው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ ሲከናወን ሰንብቷል፡፡ በአካዴሚው ሥር በሚገኘው የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ሥነ ጥበባት ማዕከል አማካይነት የሕይወት ታሪካቸው ከታሰበበት የውይይት መድረክ ባለፈም የፎቶ ዓውደ ርዕይም ቀርቧል፡፡ 

  በመስከረም 9 ቀን 1931 ዓ.ም. ያረፉበት 84ኛ ዓመትን አስታክኮ በተዘጋጀው ዓውደ ርዕይ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴን የሕይወትና የሥራ ጉዞዎችን የሚያሳዩ አርባ ታሪካዊ ፎቶዎች ቀርበውበታል፡፡ 

  በፋሺስት ጣልያን የወረራ ዘመን (1928 – 1933) ከንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ጋር በእንግሊዝ በስደት ሳሉ በ1931 ዓ.ም. ያረፉት ብላቴን ጌታ ኅሩይ፣ ቀብራቸው በባዝ ከተማ ሉግዘምበርግ የተፈጸመ ሲሆን፣ ጣሊያን ከተወገደ በኋላ በ1940 ዓ.ም. አፅማቸው ፈልሶ በአዲስ አበባ መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በክብር እንዲያርፍ ተደርጓል፡፡

  በመጀመርያው የባዝ ሥርዓተ ቀብር ላይ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባሰሙት ዲስኩር እንዲህ ብለው ነበር፡-

  ‹‹ታላቅ ነህ ሳልልህ ብቀር ሥራዎችህ ቀድመውኝ ይናገራሉ፡፡ ይህ የአዳም ልጆችን ወግ ሲቀበል የምታዩት ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ በሀገራችን ሥርዓት በመልካም አያያዝ ያደገ፣ ከኢትዮጵያም ከፍ ከአሉት ሊቃውንት የሚቆጠር ነው፡፡ ብልኃቱንና ትጋቱንም ለመልካም ሥራ የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ስላደረጋቸው በመንግሥታችን ሥራ ለመመረጥና ወደ ታላቁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ለመድረስ ችሏል፡፡ በጊዜውም የጻፋቸው መጻሕፍት ከፍተኛ ባህሪውን የሚገልጹ ይልቁንም በቤተ ክህነትና በታሪክ ዕውቀት በዓለም ሊቃውንት ዘንድ የታወቀና የተከበረ አደረጉት፡፡ ለምታውቁት ሰው ከታሪኩ ከዚህ የበለጠ ልነግራችሁ የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡››

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...