Monday, January 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊእናቶችና ሕፃናት ጤና ላይ የሚያተኩር የ22 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

እናቶችና ሕፃናት ጤና ላይ የሚያተኩር የ22 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

ቀን:

በስምንት ክልሎች በሚገኙ 44 ወረዳዎች ውስጥ በ22 ሚሊዮን ዶላር ተግባራዊ የሚሆንና በእናቶችና ሕፃናት ጤና ላይ የሚያተኩር የመጀመርያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ፡፡

አርብቶ አደሮች፣ ከፊል አርብቶ አደሮችና አርሶ አደሮች ባሉበት በእነዚሁ ወረዳዎች ፕሮጀክቱ ተግባራዊ የሚሆነው አምሪፍ ሔልዝ እና ጄኤስአይ በተባሉ አጋር ድርጅቶች ቅንጅት ነው፡፡

እንደ ጤና ሚኒስቴር ፕሮጀክቱ በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በተመረጡ 14 ወረዳዎች የሚተገበር ሲሆን፣ ቀጥሎ በሚኖሩት አምስት ዓመታት ውስጥ ደግሞ በ30 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

የአምሪፍ ሔልዝ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ስንታየሁ ፀጋዬ (ዶ/ር) የፕሮጀክቱን ተግባራዊ መሆን አስመልክተው እንዳሉት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ መንግሥት በጤናው ዘርፍ በዋናነትም የመጀመርያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አገልግሎትን ለማሻሻል እያከናወናቸው ላሉት ተግባራት የበኩሉን ዕገዛ ያደርጋል፡፡

የአምሪፍ ሔልዝ አፍሪካ የመጀመርያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ዳይሬክተር አቶ ተመስገን አየሁ በበኩላቸው፣ ፕሮጀክቱ በእናቶችና ሕፃናት ጤና ላይ እንደሚያተኩርና በዚህም የኅብረተሰቡን መደጋገፍ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ይፋ ሲሆን የተገኙት የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ፕሮጀክቱ ከዓመት በፊት ፀድቆ ወደ ሥራ የገባውን የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ እንደሚያግዝ አስረድተዋል፡፡

ፕሮጀክት ይፋ የሆነው በሐዋሳ ከተማ ጥቅምት 10 እና 11 ቀን 2015 ዓ.ም. በተካሄደው 24ኛው ዓመታዊ የጤና ጉባዔ ላይ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...