Tuesday, February 20, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከዩክሬን ወደ ኢትዮጵያ ሊላክ በነበረ 40 ሺሕ ቶን ስንዴ ላይ ዕግድ ተጣለ

ተዛማጅ ፅሁፎች

12 መርከቦች ‹‹ብላክ ›› ማለፍ አይችሉም ተብሏል

  • በሩሲያና በዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት በድጋሚ በማገርሸቱ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ የነበረ 40 ሺሕ ቶን ስንዴ የያዘ መርከብ ‹‹ብላክ ሲ›› ተብሎ የሚጠራውን ባህር ማለፍ ባለመቻሉ፣ እህሉን ወደ ጂቡቲ ማጓጓዝ አለመቻሉ ተገለጸ፡፡

በ‹‹ብላክ ሲ›› ታግተው የሚገኙት መርከቦቹ ብዛታቸው 12 የሚጠጉ ሲሆን፣ 54,500 ቶን እህል ጭነው እንደነበር ተነግሯል፡፡ ወደ ኢትዮጵያና ሌሎች ታዳጊና አፍሪካ አገሮች በዕርዳታ ሊከፋፈል የነበረው ስንዴ በዓለም አቀፍ የምግብ ፕሮግራምና ሌሎች አጋር ድርጅቶች የተገዛ ነው፡፡

የዩክሬን መሠረተ ልማት ሚኒስትር አሌክሳንደር ኩባራኮቭ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የሚዲያ አውታሮች ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፣ ሩሲያ ከአገራቸው ጋር የነበራትን ስምምነት በማፍረስ በ‹‹ብላክ ሲ›› በኩል የሚደረጉ የመርከብ ትራንስፖርት አገልግሎቶችን ማገዷንና እህሉን ወደ መዳረሻቸው መውሰድ አለመቻሉን ገልጸዋል፡፡ ይህም በኢትዮጵያ ለረሃብ የተጋለጡ ሰዎችን ለበለጠ ችግር እንደሚያጋልጥ ተናግረዋል፡፡

ለኢትዮጵያና ለሌሎች አፍሪካ አገሮች ስንዴ ምርቶችን በመላክ የምትታወቀው ዩክሬን፣ ወደ እነዚህ አገሮች ምርቶችን ለመላክ በ‹‹ብላክ ሲ›› ግዴታ ማለፍ ይኖርበታል፡፡ በሩሲያና በዩክሬን መካከል ጦርነቱ መከሰቱን ተከትሎ በቭላድሚር ፑቲን ትዕዛዝ ከዩክሬን የሚነሱ መርከቦች እንዳያልፉ ዕግድ ተጥሎ የነበረ ቢሆንም፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግፊት ሁለቱ አገሮች ‹‹ብላክ ሲ ግሬን ኢንሼቲቭ›› የተባለ ስምምነት በመፈራረም፣ ዩክሬን የተመረቱ የግብርና ምርቶች ወደ አፍሪካ አገሮች እንዲላኩ ስምምነት ተደርሶ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ በዩክሬንና በእንግሊዝ ስፔሻሊስቶች፣ የእህል ኮሪደሩን ደኅንነት ለመጠበቅ ተሰማርተው በነበሩ መርከቦች ላይ የሽብር ተግባር ተፈጽሟል ያለችው ሩሲያ፣ ስምምነቱን ማቋረጧን በመከላከያ ሚኒስትሯ በኩል ያወጣችው መረጃ ያመላክታል፡፡ ይህንንም ተከተሎ ከዩክሬን የሚመጡ የግብርና ምርቶች የያዙ መርከቦች እንዳያልፉ መታገዳቸውን ሚኒስትሩ ይፋ አድርጓል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ የስምምነቱ መፍረስ እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል፡፡ ዋና ጸሐፊው እንደተናገሩት ያልተረጋጋውን የስንዴና የማዳበሪያ ገበያ ይበልጡኑ ችግር ውስጥ እንደሚከተው አክለዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና ልማት ጉባዔ ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመላክተው፣ ባለፉት አምስት ወራት የሁለቱ ምርቶች ዋጋ መቀነስ ያሳየ ሲሆን፣ ጦርነቱ ሲጀምር አካባቢ ከታየው ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የ14 በመቶ ቅናሽ ታይቷል፡፡

ከወር በፊት ዩክሬን ለኢትዮጵያና ሶማሊያ ለሚከናውኑ የሰብዓዊ መብት ዕርዳታዎችን ለማገዝ 50 ሺሕ ቶን ስንዴ ለመለገስ ቃል መግባቷ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች