ቅርሶችና የቱሪስት መስህብ ስፍራ በሚገኙባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ምልክቶች (ላንድ ማርኮች) እና አቅጣጫ ጠቋሚዎችን እየተሠራላቸው ነው፡፡ ከነዚህም አንዱ በሐረር ከተማ መግቢያ ላይ የተገነባው የሐረር ጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ ምልክት ነው፡፡ ይኸው ምልክት መሰንበቻውን በቱሪዝም ሚኒስቴርና በክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ተመርቋል። የቱሪዝም ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ አቅጣጫ ጠቋሚዎቹም ሆኑ ምልክቶቹ፣ ባህላዊ እሴቶች ታሪካዊ ይዘታቸውን በጠበቀና የየአካባቢውን ቋንቋዎች ታሳቢ ባደረገ መልኩ እየተሠሩ ናቸው፡፡