Sunday, May 26, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ከቀረጥና ከታክስ ነፃ የሆኑት የእንስሳት መኖ ግብዓቶች ዝርዝር ታወቀ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከባለፈው ዓመት 2014 ዓ.ም. ሰኔ ወር ጀምሮ ከቀረጥና ከታክስ ነፃ የሆኑት የእንስሳት መኖ ግብዓቶች ላይ በተፈጠረው፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ አከፋፈል አለመግባባት ምክንያት የእንስሳት መኖ ግብዓቶች ዝርዝር ወጣ፡፡

ሪፖርተር ከግብርና ሚኒስቴር ባገኘው መረጃ መሠረት አገር ውስጥ የሚመረቱ፣ እንዲሁም የፋብሪካ ተረፈ ምርቶችና ከውጭ የሚገቡ የእንስሳት መኖ ዓይነቶችን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የገቢዎች ሚኒስቴር ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ለቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ጽፏል፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ገቢዎች ሚኒስቴር ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. በጻፈለት ደብዳቤ እንዳሳወቀው፣ ምርቶቹን በ13 ዘርፎች የመደበ ሲሆን፣ ከተለያዩ እንደ ዱቄት፣ የምግብ ዘይት፣ ስኳርና ቢራ ዓይነት ፋብሪካዎች የሚወጡ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ተረፈ ምርት ዓይነቶችን ያካተተ ነው፡፡ በተጨማሪም ሰባት ዓይነት ከዕርድ እንስሳት የሚገኙ ተረፈ ምርቶችንና ከውጭ የሚገቡ ቫይታሚንና አልሚ ምግብ ዓይነቶችን ያካተተ የመኖ ግብዓቶችን ዝርዝር ነው ግብርና ሚኒስቴር ለገቢዎች ሚኒስቴር ያስተላለፈው፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በደብዳቤው እንዳሳወቀው፣ ባለፈው ሰኔ ወር ውስጥ ውሳኔን ካሳለፈ በኋላ ለታክስ አስተዳደር እንዲመች ሲባል፣ በአገር ውስጥ ግብይቱ በሚፈጸምበት ወቅት ታክሱን ተገበያዮች እንዲከፋፈሉና፣ የተገበያዩበት ምርትም ለእንስሳት መኖ ግብዓትነት መዋሉን ግብርና ሚኒስቴር ሲያረጋግጥ ከታክስ ተመላሽ እንዲሆን በሐምሌ ወር 2014 ዓ.ም. መወሰኑን አስታውሷል፡፡ ሆኖም ግን የተወሰኑ ዱቄትና የዱቄት ውጤቶች አምራቾች ግብይቱ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ነው በሚል፣ ታክሱ እንደማይመለከታቸው መከራከሪያ ያቀርቡ እንደነበር ገልጿል፡፡ ይህንንም ክፍተት ለመሙላትና ለታክስ ተመላሽ ሥርዓቱ እንዲያመች የግብርና ሚኒስቴር አስቀድሞ እንዲታወቅ የመኖ ግብዓት ዓይነቶችን ለገቢዎች ሚኒስቴር አሳውቆ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ዱቄት አምራቾች ማኅበር በበኩሉ፣ መጀመርያ ላይ ከገንዘብ ሚኒስቴር ባገኘው ከታክስ ነፃ ትዕዛዝ መሠረት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሳይቆርጥ ይሸጡ እንደነበረ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉነህ ለማ ለሪፖርተር የገለጹ ሲሆን፣ ቆይቶ ውዝግብ መምጣቱንና ገቢዎችም ተረፈ ምርቱን ለመኖ ግብዓትነት እንደሚመጠቀሙ ካረጋገጠ እንደሚመልስላቸው ሲያስረዳቸው መቁረጥ እንደጀመሩ አክለው ተናግረዋል፡፡

ተረፈ ምርቱን ከፋብሪካዎች ከወሰዱ በኃላ መኖ አምራቾም ሆኑ ሌሎች ተጠቃሚዎች እሴት ጨምረውም ሆነ ሳይጨምሩ፣ ሊጠቀሙ የሚችሉ ሲሆን፣ ለመኖ ምርትም ሆነ በቀጥታ ለሚሰጡት ፋብካዎች ሲሰጡ መለየት እንደማይችሉ አቶ ሙሉነህ ይገልጻሉ፡፡ ‹‹እኛ እየለየን ለግማሹ ቫት መቁረጥ ወይም ለግማሹ አለመቁረጥ አንችልም፡፡ መጀመርያም ታክስ ይነሳ የሚል የገንዘብ ሚኒስቴር ደብዳቤ ስላሳወቀን ነው መቁረጥ አቁመን የነበረው፤›› ሲሉ አክለው ገልጸዋል፡፡

የእንስሳ መኖ ላይ የሚሠራ (ትሮው ኒውትሬሽን) የተባለ የኔዘርላድ ድርጅት ቴክኒካል ሽያጭ ኃላፊ የሆኑት ደመቀ ወንድምአገኝ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ሙያዊ አስተያየታቸውን ሲሰጡ፣ እስከዛሬ በታሰበለት ሥርዓት አለመሠራቱን የገለጹ ሲሆን፣ አሁን የመኖ ግብዓቶቹ ዝርዝር መውጣቱ በጎ ድርጊት እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ እሳቸው የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎች ማኅበር ቦርድ ጸሐፊ ሆነው ከዚህ በፊት ለበርካታ ዓመታት አገልግለው የነበረ ሲሆን፣ እሳቸውም ይገጥማቸው እንደነበር የገለጹት አንደኛው ችግር የግንኙነት ሥርዓቶች በተገቢው አለመሠራታቸውን ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች