Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበበጀት እጥረት ከ16 ፌዴሬሽኖች ስድስቱ ብቻ ጉባዔያቸውን ማከናወናቸው ተገለጸ

በበጀት እጥረት ከ16 ፌዴሬሽኖች ስድስቱ ብቻ ጉባዔያቸውን ማከናወናቸው ተገለጸ

ቀን:

የተለያዩ ስፖርቶችን ከሚመሩት 16 ፌዴሬሽኖች መካከል በ2015 ዓ.ም. ሩብ ዓመት ስድስት ስፖርት ፌዴሬሽኖች ብቻ ጠቅላላ ጉባዔያቸውን ማድረጋቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የአገር አቀፍ ስፖርት ማኅበራት ዕውቅና ድጋፍ አስፈጻሚ፣ የሩብ ዓመት አፈጻጻም ግምገማን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርት ሲያቀርብ እንደገለጸው፣ ከ31 ፌዴሬሽኖች መካከል 16 ፌዴሬሽኖች በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ጉባዔያቸውን እንደሚያደርጉ ቢጠበቅም ስድስቱ ብቻ አድርገዋል፡፡

በዚህም መሠረት በሩብ ዓመቱ ጠቅላላ ጉባዔያቸውን ያከናወኑት ፌዴሬሽኖች የኢትዮጵያ መረብ ኳስ፣ የቴኒስ፣ የእግር ኳስ፣ የውሹ፣ የቦውሊንግና የሞተር አሶሴሽን ናቸው፡፡

ቀሪዎቹ 15 ፌዴሬሽኖች በሁለተኛው ሩብ ዓመት ጉባዔያቸውን እንደሚያደርጉ በሪፖርቱ ላይ የተገለጸ ሲሆን፣ የማኅበሮቹ አቅም በመንግሥት ድጋፍ ላይ የተንጠለጠለ መሆኑ ተወስቷል፡፡

ሚኒስትሮቹ አቶ ቀጀላ መርዳሳና አቶ መስፍን ቸርነት በተገኙበት ከቋሚ ኮሚቴ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የስፖርት ማኅበራት ምዝገባ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘሪሁን ታገሰ ናቸው፡፡ ጉባዔ ለመጥራት አቅም የሌላቸው በርካታ ፌዴሬሽኖች የመንግሥትን የገንዘብ ድጋፍ የሚጠባበቁ በመሆናቸው ጉባዔያቸውን ሳያከናውኑ የቀሩ መኖራቸው ጠቅሰዋል፡፡

አቅም ኖሯቸው ጉባዔያቸውን ካደረጉት መካከል፣ በአገር አቀፍ ስፖርት መመርያና ማቋቋሚያ መሠረት የራሳቸውን ደንብና መመርያ አውጥተው ያፀደቁ መኖራቸውን አቶ ዘሪሁን አክለዋል፡፡

በሌላ በኩል በስፖርት ዘርፍ አደረጃጀት በሩብ ዓመቱ ለመሰብሰብ ከታቀደው ፌዴሬሽኖቹ ራሳቸው የገንዘብ ገቢ ፈጥረው የመጓዝ ሒደት በሩብ ዓመቱ አዝጋሚ መሆኑ ተነስቷል፡፡ በዚህም ምክንያት የክልል የስፖርት አደረጃጀቶች፣ የተለያዩ የክለብ አደረጃጀቶች እንዲሁም በተለያዩ የክልል ከተሞች ላይ የሚገኙ ክለቦች አብዛኞቹ የመንግሥት የበጀት ድጋፍ የሚጠባበቁ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

እንደ አቶ ዘሪሁን ማብራሪያ፣ የስፖርት ማኅበራት የገንዘብ አቅም ለማሳደግ ከተመልካች፣ ከስፖንሰር፣ ከግል ባለሀብትና ከዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖች በሚገኙ ድጋፎች ገቢን ማሳደግ ቢቻልም፣ ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች አለመኖራቸው ለችግሩ መሠረታዊ ችግር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...