Saturday, June 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ‹‹ኢትዮጵያ ምን አጥታ ተቸገረች?››

‹‹ኢትዮጵያ ምን አጥታ ተቸገረች?››

ቀን:

‹‹ኢትዮጵያ ምን አጥታ ተቸገረች?›› በሚል ርዕስ በአቶ አሰፋ አደፍርስ ለሕትመት የበቃው ታሪክ ቀመስ መጽሐፍ ጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ተመርቆ ገበያ ላይ ውሏል፡፡

ደራሲው እንደተናገሩት፣ መጽሐፉ ከአፄ ቴዎድሮስ እስከ አፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ ከዚያም እስካሁን ያለውን ታሪካዊ እውነታ የዳሰሰ ቢሆንም፣ ቁጭትና ንዴት የተሞላበት እውነታ አለበት፡፡

ኢትዮጵያ በቀንድ ሀብት ከዓለም አምስተኛ፣ ከአፍሪካ አንደኛ ብትሆንም ሥጋ ከውጭ የምታስገባ አገር መሆኗ ቁጭት የሚያጭር መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በቀን 66,000 ሊትር ወተትና የወተት ተዋጽኦ መቅረብ ሲገባው፣ እየቀረበ ያለው ግን 60,000 ሊትር እንኳን ያልሞላ፣ ለዚያም ውኃ የታከለበትና ሕፃናቱም ይህን መሰል ወተት ለመጠጣት መገደዳቸው ሌላው ቁጭት መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ይህንንም ችግር በመገንዝብ 66 የወተት ላሞች አዳቅለው ቦሌ አካባቢ ወተትና የወተት ተዋጽኦ ለማቅረብ የሚያስችል ፕሮጀክት እንደቀረጹ፣ ለፕሮጀክቱም ዕውን መሆን ሁለት ሚሊዮን ዶላር እንዳገኙ፣ ነገር ግን ጉዳዩ በሚመለከተው አካል ፕሮጀክቱ ተቀባይነት እንዳጣና ዶላሩንም እንደመለሱ በመጽሐፉ ውስጥ ጠቅሰዋል፡፡

በተለምዶ ‹‹ቆሼ›› የተባለውን ቦታ ለማልማት ተንቀሳቅሰው የነበሩ ቢሆንም፣ ጉዳዩ የሚመለከተው መንግሥታዊ አካል መንግሥት ያለማዋል በሚል ምክንያት እንቅስቃሴያቸውን እንዲያቆሙ መዳረጋቸውን መጽሐፉ ይተርካል፡፡

እንደ ደራሲው እምነት ኢትዮጵያ ያጣችው ነገር ቢኖር የአሠራር ሥርዓት፣ የአመራሩ ድክመት መሆኑን ገልጸው፣ መጽሐፉንም ያዘጋጁት ከዚህ መሠረት ሐሳብና እውነታ ተነስተው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የዘጠና ስድስት ዓመት ዕድሜ ባለፀጋው ደጃዝማች ወልደሰማዕት ገብረወልድ መጽሐፉን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፣ ‹‹መጽሐፉ እርስ በርስ ከመገዳደልና ከመዘራረፍ ተላቀንና ቆም ብለን ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ ገናንነቷ እንድንመልሳት የሚል እምነት አሳድሮብኛል፤›› ብለዋል፡፡

በቴክኖሎጂ የታገዘ ዕድገት ከማስመዝገብ ይልቅ አገርን በታትኖ ወደ ትንሽ አገር ለማውረድ መሞከረ እኩይ ተግባር ነው ያሉት ደግሞ ብርጋዲየር ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ ናቸው፡፡

አያይዘውም መጽሐፉ በአሁኑ ጊዜ እየተፈጸመ ያለው እኩይ ተግባር ከእንግዲህ እንዳይደገም፣ አገርን በልማት እያሳደጉ እርስ በርስ ተባብሮ፣ ተቃቅፎና ተረዳድቶ ከመኖር የተሻለ ነገር እንደሌለ ያመላክታልም ብለዋል፡፡

መጽሐፉ የታሪክ ሰነድ መሆኑን የገለጹት አቶ ጥበቡ በለጠ እንዳመለከቱት፣ እስከ 1966 ዓ.ም. ድረስ ለትምህርት አሜሪካን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የአውሮፓ አገሮች የሄዱ ወጣቶች ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላ በየተማሩበት አገር ጥገኝነት ጠይቀው በዚያው የቀሩ አልነበሩም፡፡ ይህ የሚያሳየው በዘመኑ በኢትዮጵያዊነት ላይ ምን ያህል እንደተሠራ፣ ሥራውም ምን ያህል እንደሠረፀና ተቀባይነትም እንዳገኘ ነው፡፡

ደራሲው ግን በስደት ከሚኖሩበት አሜሪካ ይዘው ያመጡትን ሀብት አገርና ወገንን ለመጥቀም ያደረጉት ሙከራና ጥረት ኃላፊነት በማይሰማቸው አንዳንድ ሰዎች ምክንያት ሥራ ላይ እንዳይውል መደረጉ፣ በአንፃሩ ደግሞ በሥራ አጥነት የተነሳ በየቤቱ ያለው ችግር ሲታይ ከዓለም ምን ያህል ወደ ኋላ እንደቀረንና ከድህነት ወለል በታች እንደወረድን ያሳያል ብለዋል፡፡

‹‹‘ኢትዮጵያ ምን አጥታ ተቸገረች?’ ሦስት ጉዳዮችን እንዳስታውስና በአፅንኦት እንድቆዝምባቸው አድርጎኛል፤ (1) የኤድዋርድ ጊበንን ‹ኢትዮጵያ ዓለምን ረስታ ዓለሙም ረስቷት ለሺሕ ዓመታት አንቀላፋች፤ (2) የደቂቀ እስጢፋኖስ ‹የድህነት ሥሩ ግጭት ነው› እና (3) የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስን ‹የአገሬ ሰው ሥርዓት ግባ ብዬ ብለው እምቢ ብሎ ተጣላኝ› ይህ መጽሐፍ ትውልድ ሰክኖ እንዲያስብና ድርሻውን እንዲወጣ የሚጋብዝ ድንቅ አበርክቶ ነው፤›› በማለት በመጽሐፉ የጀርባ ሽፋን ላይ አስተያየት የሰጡት የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አበባው አያሌው ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...