Monday, November 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወየሳ (1961 - 2015)

  ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወየሳ (1961 – 2015)

  ቀን:

  የ1983ቱ የመንግሥት ለውጥ ካስገኛቸው አንዱ የነፃ ፕሬስ ኅትመቶችን ነበር። በወቅቱ ከነበሩት መጽሔቶችና ጋዜጦች መካከል በሩሕ፣ በፈለግ፣ በሞገድ፣ በመብረቅ፣ በማዕበል በዘጋቢነትም ሆነ በዓምድ አዘጋጅነት የሚታወቀው ዳዊት ከበደ ወየሳ ነው።

  ገጸ ታሪኩ እንደሚያሳየው፣ በሴቶች ጉዳይ ላይ የምታተኩር ‹‹ታደለች›› መጽሔት ዋና አዘጋጅም ነበር። ‹‹ፊያሜታ›› የተባለች ጋዜጣ መሥራችና ዋና አዘጋጅ የነበረው ዳዊት፣ የሚዲያ ሰው አለባበሱ ሥርዓቱን የጠበቀ መሆን አለበት ብሎ ያምን እንደነበረ ይነገርለታል።

  በኅትመት ሚዲያ ላይ ከመሰማራቱ በፊት የትምህርት መገናኛ ተቋም ሥር በነበረው የለገዳዲ ሬዲዮ ጣቢያ፣ በቅዳሜ ከእኛ ጋርና በእሑድ ላንዳፍታ ዝግጅቶች በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መጣጥፎችን፣ ግጥሞችንና አጫጭር ድራማዎች ያቀርብ እንደነበረ ይወሳል።

  ዳዊት በተመረቀበት የኤሌክትሪክ ዘርፍ በመብራት ኃይል ተቀጥሮ ያገለገለ ሲሆን፣ በድርጅቱ ይታተም በነበረው ‹‹ፈለገ ብርሃን›› መጽሔት ይጽፍ እንደነበረ ዜና ሕይወቱ ያሳያል።

  የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማኅበርን በሕዝብ ግንኙነት ኃላፊነት የሠራው ዳዊት፣ በ1992 ዓ.ም. በስደት  በኬንያ፣ በካናዳና አሜሪካ መኖር ከጀመረ በኋላ በጋዜጠኝነት በመቀጠል በተለያዩ ሚዲያዎች ሠርቷል።

  በኅብረት ድምፅ መጽሔት፣ በአድማስ ሬዲዮና በትንሳዔ ሬዲዮ በአዘጋጅነትና በኃላፊነት መሥራቱ ይወሳል።

  ስለእሱ ታሪክ በተዘጋጀ አንድ ጽሑፍ ላይ እንደተጠቀሰው፣‹‹በስደት የሚገኙ የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞችን ፎረም መሥርቷል፡፡ ዕለታዊ ችግሮችን ከመፍታት ጀምሮ ጋዜጠኞች ከሙያቸው እንዳይርቁ በርካታ ሙያዊና ሰብዓዊ ሥራዎችን ሠርቷል››፡፡

  በአዲስ አበባ ከተማ ቄራ አካባቢ ታኅሣሥ 19 ቀን 1961 ዓ.ም. የተወለደው ዳዊት፣   የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በዳግማዊ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከዚያም የቴክኒክና ሙያን በምሥራቅ አጠቃላይ ትምህርት ቤት ተከታትሎ በ1979 ዓ.ም. በኤሌክትሪክ ሙያ ተመርቋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ክፍል ውስጥ የሥነ ጽሑፍ ትምህርትን መከታተል ችሏል፡፡ በካናዳ ሜሞርያል ኒው ፋውንድላንድ ዩኒቨርሲቲ  በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የመጀመርያ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡

  ከሁለት አሠርታት በላይ ከኖረበት ባህር ማዶ አሜሪካ ለዕረፍት ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በድንገተኛ ሕመም ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በ53 ዓመቱ አርፏል፡፡ በ53 ዓመቱ አርፏል። ሥርዓተ ቀብሩም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ኅዳር 3 ቀን ተፈጽሟል። ዳዊት ከበደ ወየሳ ባለትዳርና የአንድ ወንድና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበር፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...