ቅሬታ የቀረባባቸወን የ2005 ዓ.ም ባለ ሶስት መኝታ የኮንደሚኒየም ቤቶች ጨመሮ የ25,971 ቤቶች ዕጣ ነገ ሊወጣ ነው።
ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በይፋ ዕጣ ከወጣበት በኋል የማጭበርበር ከባድ የሙስና ወንጀል ተፈጽሞበታል ተብሎ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ የተደረገው የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አስፈላጊውንና ከዚህ ቀደም ተፈጥሮ ከነበረው ስህተት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ በተመላበት አዲስ ሲስተም ተዘጋጅቶ በነገው ዕለት እንደሚወጣ የከተማ አስተዳደሩ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በነገው ዕለት ዕጣ ከሚወጣባቸው ቤቶች በ20/80 ፕሮግራም ለተመዘገቡ 3,318 ስቱዲዮ፣7,171 ባለ አንድ መኝታ፣8,159 ባለ ሁለት መኝታ እንዲሁም 300 ባለ ሶስት መኝታ ተመዝጋቢ ነዋሪዎች የሚተላለፉ ናቸው ተብሏል
በ40/60 የቤት ልማት ከተገነቡት 1,870 ባለ አንድ መኝታ፣ 4,220 ባለ ሁለት መኝታ እንዲሁም 753 ባለ ሶስት መኝታ ቤቶች በነገው ዕጣ እንደሚተላለፉ ታውቋል።