Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመከላከያ በትግራይ ክልል ለሚያካሂዳቸው ሥራዎች የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

መከላከያ በትግራይ ክልል ለሚያካሂዳቸው ሥራዎች የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ቀን:

  • ሠራዊቱ በትግራይ ክልል 402 ሔክታር መሬት ላይ የሚገኝ ሰብል ሰብስቧል

በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል በቅርቡ ሰሞኑን በተደረገው የሰላም ስምምነት መሠረት በቅርቡ ለሚካሄዱት ታጣቂዎችን መለየት፣ ትጥቅ ማስፍታት፣ ተሃድሶና ሌሎች የቅንጅት ሥራዎችን ለማከናወን የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. የአገር መከላከያ ሠራዊት ኃላፊዎች በአዲስ አበባ መቀመጫቸውን ላደረጉ የተለያዩ አገሮች ኤምባሲዎች የመከላከያ አታሼዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡ አታሼዎቹና ሌሎች የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ አባላት የሥልጠና፣ የቴክኒክና አቅም ግንባታ ድጋፎች በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ለዲፕሎማቶች ገለጻ ተደርጓል፡፡

በገለጻው የመከላከያ ሠራዊት የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ፣ አታሼዎቹ የአገራቸውን የመከላከያ ሠራዊት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር የግንኙነት ድልድ እንዲኖራቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹የመከላከያ ሠራዊትን በመወከል ለአታሼው ማኅበረሰብ የማስተላልፈው ጥሪ ቢኖር፣ ቀጣይነት ያለው ምክርና ድጋፍ የመስጠት ጥረት እንዲቀጥል ነው፤›› ሲሉ ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ተናግረዋል፡፡

በተያያዘም መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል በቅርቡ ሲያደርገው የነበረውን ክንውን ለአታሼዎቹ ገለጻ ተደርጎ የነበረ ሲሆን፣ በዚህም ሕዝባዊ አገልግሎት ላይ በስፋት ተሰማርቶ እንደነበር በዝርዝር ተገልጿል፡፡ ካለፈው ነሐሴ አጋማሽ ወዲህ በድጋሚ አገርሽቶ በነበረው ጦርነትና የመከላከያ ሠራዊት ባደረገው የመከላከል ሥራ ወደ ትግራይ ክልል ከዘለቀበት ጊዜ ወዲህ፣ 402 ሔክታር መሬት ላይ የደረሰ ሰብል 3,211 ለሚሆኑ አርሶ አደሮች እንዳጨደ ተነግሯል፡፡

እነዚህን ማኅበራዊ አገልግሎቶች በዝርዝር ያስረዱት የመከላከያ ሠራዊት የውጭ ግንኙነት ክፍል ከፍተኛ አማካሪ መኮንን አበበ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የመከላከያ ሠራዊት ለማኅበረሰቡ ድጋፍ ለማድረግ የሰላም ስምምነቱን እንዳልጠበቀ፣ ቀድሞውኑ ወደ ትግራይ ክልል መግባት ሲጀምር እነዚህን ሥራዎች ሲያከናውን እንደነበር ተናግረዋል፡፡ 11,136 የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ማጓጓዝን፣ እንዲሁም 14 እርጉዝ ሴቶችን ጨምሮ ለ3,833 ሕሙማን በትግራይ ክልል በራሱ ወጪ እንዳሳከመ ገልጸዋል፡፡ በትግራይ ክልል የሚገኙ የሠራዊቱ አባላት ከደመወዛቸው በማዋጣትም ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ እንደለገሱ መኮንን (ዶ/ር) ጠቁመዋል፡፡

አታሼዎቹና የመከላከያ ሠራዊት ኃላፊዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት የጦርነት ጊዜያት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመናጋገር ተገናኝተው እንደነበር የገለጹት ሜጀር ጄኔራል ተሾመ፣ የአሁኑ ግንኙነት በተለየ ምዕራፍ እንደሆነና ይህም በአዲስ የልማትና የሰላም ተስፋ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፕሪቶሪያ መጀመርያ የተደረገውና በናይሮቢ የቀጠለው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት ላይ የተወሰኑ አገሮች አታሼዎች ጥያቄ በማንሳት ሥጋትም እንዳለባቸው ገልጸው የነበረ ሲሆን፣ በርካታ አታሼዎች በስምምነቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ነበር፡፡ ለዚህም ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሜጀር ጄኔራሉ ሲሰጡ ሥጋት ያለባቸው አገሮች እንዲህ ዓይነት ችግሮች ገጥመዋቸው የነበሩ የአፍሪካ አገሮችን እንደ ምሳሌ ከመውሰድ የመነጨ እንደሆነ፣ አብዛኞቹ አገሮች ተወካዮች ግን በአድናቆት የመንግሥትን ዕርምጃ እንዳዩት ነው የገለጹት፡፡

‹‹የአንዳንዶቹ ጥርጣሬ በተለያዩ አገሮች የተከሰተውን ምሳሌ በማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የአንዱ አገር ሁኔታ ለኢትዮጵያ ምሳሌ ሊሆን አይችልም፡፡ ኢትዮጵያ የተለየች አገር ነች፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡  

የአውስትራሊያ ኤምባሲ ምክትል ወታደራዊ አታሼ አንቶኒ ሲሊሲች በሰጡት አስተያየት፣ አውስትራሊያ ጠንካራ የሰብዓዊ ድጋፍ ዕቅድ እንዳላትና ለኢትዮጵያ መንግሥትም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነች፣ እንዲሁም መሠረት የያዘ ፕሮግራም እንዳላት ተናግረዋል፡፡ በተለይም በምግብ ደኅንነት ለኢትዮጵያና በአጠቃላይ ለምሥራቅ አፍሪካ የድጋፍ ፕሮግራም እንዳላትም አክለዋል፡፡ በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር የተደረገውም ስምምነት ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ ትልቅ ምሳሌ እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...