Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

አንደበትን አትለጉሚ

ትኩስ ፅሁፎች

አንደበት፣ ነፍስ ዓለምን ለመድረስ እጇን እምትዘረጋበት መንገድ ነው፡፡ ይህ ቃል ይሆን ይሆናል፤ ዝምታም ይሆን ይሆናል፡፡ በልብሽም በነፍስሽም መናገር አቁሚና አድምጪ፡፡

ምስባክ መድረኩን በቁጥጥርሽ ስር ለማድረግ አትሞክሪ፡፡ ድምፅ የተነፈጉቱ እንዲናገሩ ፍቀጂ፡፡

ነፍሶች ሁሉ እኩል ናቸው፡፡ እኩልነት ማለት፣ ሰዎችን በጠረጴዛ ዙሪያ አስቀምጦ የልባቸውን እንዲናገሩ ማድረግ ብቻ እንዳይደለ ግን እውቂ፡፡

ይልቅ፣ ልበ-ንፁሃን የሚናገሩ፣ በአዋቂነት ማን-አለብኝነት ጉድፍ ተሸፍኖ በልብሽ ጥልቀት ውስጥ የተደበቀውን የዛ ራስሽን እውነት እንዲሁ በመረዳት፣ እነሱ እልብሽ ውስጥ እንዲቀመጡ መፍቀድ ነው፡፡ አዎን፣ የነሱ አንደበት ያንቺም አንደበት ነው፡፡ ከዚያ ሁሉም ነፍሳት በጋራ ከሚዋኙበት ውቂያኖስ የፈለቀ አንድ ጠብታ፡፡ የራስሽን እውነት የምትይዢውን ያህል ያንንም እንዱያ አጥብቀሽ ያዢው፡፡

ይህ፣ እጅግ ጥልቅ በሆነ ደረጃ ሌሎችን መድረስ፣ ሌሎችም እንዲደርሱሽ መፍቀድ፣ ውሳኔ ሆኖ ሲወለድ፣ በልብሽም በነፍስሽም አክብሪው፡፡ ያ ውሳኔ ያንቺም ውሳኔ ነውና፡፡ የገዛ ልብሽ እንዲናገር ስትፈቅጂም እንዲሁ አድርጊ፣ አዕምሮሽን ዝም አስብዩና አድምጪ፡፡ የሚናወጠውን ባህር ለመግታት ከሞከርሽ፣ በውስጡ አትዋኚበትም፡፡ ትሰጥሚያለሽ፡፡

  • ኦታም ፑልቶ ‹‹የፈላሱ መንገድ›› (2006 ዓ.ም.)
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች