Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአብላጫው ሥራ በመንግሥት የሚከናወነው የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት

አብላጫው ሥራ በመንግሥት የሚከናወነው የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት

ቀን:

የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆነውን የእናቶችና አሥር በመቶ ያህሉን የሕፃናት ሞት የመከላከልና የመቀነስ አቅም አለው፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ አገልግሎቱን የሚጠቀሙ ጥንዶች ያልታቀደ እርግዝና እንዳይገጥማቸው የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ጤና ሚኒስቴር ይገልጻል፡፡

በሚኒስቴሩ የእናቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጤናና የሥርዓተ ምግብ ዳይሬክተር መሠረት ዘለዓለም (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት የኢትዮጵያን ዕድገት ለማረጋገጥ የሚያስችል መርህ ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

እንደ ዘለዓለም (ዶ/ር) በኢትዮጵያ በ1992 ዓ.ም. የተካሄደው የሥን ሕዝብ ጤና ዳሰሳ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ይጠቀሙ የነበሩ ሴቶችና ልጃገረዶች ስምንት በመቶ ብቻ እንደነበሩ ሲያሳይ፣ በ2011 ዓ.ም. የተከናወው ተመሳሳይ ጥናት ደግሞ የተጠቃሚዎቹ ቁጥር 41 በመቶ መድረሱን ያሳያል፡፡

ሚኒስቴሩ ባስቀመጠው የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ መሠረት የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ብዛት ወደ 50 በመቶ፣ በአሥር ዓመቱ ዕቅድ ደግሞ ወደ 54 በመቶ ለማሳደግ ታልሞም እየተሠራ ይገኛል፡፡

ሆኖም ከአምስት ሴቶች አንዷ ወይም 20 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት መረጃ እያላቸውና መጠቀም እየፈለጉ የማይጠቀሙ መሆናቸውን ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል፡፡

ይህም ባሎቻቸው ስላልተስማሙ፣ ጓደኞቻቸውና በቅርብ የሚያውቋቸው ዘመዶቻቸው በአገልግሎቱ ስለማይተማመኑ፣ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስተጓጉላት ነገር መኖሩና እንደምክንያት ሊጠቀስ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ከአፋርና ከትግራይ ክልሎች ውጪ በተከናወነ ላይ የመንግሥትና የግል ጤና ተቋማት የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የዳሰሰው ጥናት ሰሞኑን ይፋ ሲሆን ዳይሬክተሯ መሠረት (ዶ/ር) እንዳብራሩት፣ 89 በመቶ የሚሆነው የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት በመንግሥት ጤና ተቋማት እየተሰጠ ነው፡፡

ጥቅምት 2011 ዓ.ም. የተከናወነው መለስተኛ የሥነ ተዋልዶ ጤና ዳሰሳ ጠቅሰው እንዳሉትም፣ 12 በመቶ ሴቶች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት የሚጠቀሙት በግል ጤና ተቋማት ነበር፡፡

አገልግሎቱን በግል ጤና ተቋም እንዲያገኙ ያደረጋቸው ፍላጎትም የግል ፍላጎታቸው ተጠብቆ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎትና ማግኘታቸውና ከአገልግሎት ሰጪዎች ጋር መልካም መግባባት መፍጠር መቻላቸው ከምክንያቶቹ እንደሚገኙበት አስረድተዋል፡፡

እንደ መሠረት (ዶ/ር)በግል ጤና ተቋማት የሚገለገሉትም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ወጣትና የተማሩ ሴቶች  እንዲሁም የጋምቤላ፣ የሶማሌ፣ የአፋርና የሐረሪ ክልሎች ነዋሪዎች የሆኑ ሴቶችና ልጃገረዶች ናቸው፡፡

የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን በኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ በዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎችም የትምህርትና የሥራ ተቋማት ለሚገኙ ሴቶች ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በጤና ሚኒስቴርና ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት ከተካሄደውና በጥቅምት መገባደጃ ይፋ ከሆነው የጥናት ውጤት ለመረዳት እንደተቻለው፣ ከግል ጤና ተቋማት መካከል 89 ከመቶ ያህሉ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡

ተቋማቱ የሚሰጡት የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት የኮንዶም፣ በአፍ የሚወሰድ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብልና በመርፌ የሚሰጥ መሆኑን ጥናቱ ያሳያል፡፡ በ2000 እና በ2005 የተካሄደው የሥነ ሕዝብ የጤና ዳሰሳ፣ መንግሥታዊ ባልሆኑና የእምነት ተቋማት በሆኑ ድርጅቶች ሥር የሚገኙ ክሊኒኮችና የግል መድኃኒት ቤቶች የወሊድ መከላከያ ዋና ምንጮች መሆናቸውን ጥናቱ ያሳያል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...