Tuesday, February 27, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

 [ክቡር ሚኒስትሩ እራት እየበሉ መንግሥትን በሚተቹ ጋዜጠኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን ዕርምጃ የተመለከተ መረጃ እየቀረበላቸው ነው]

 • ለጋዜጠኞቹ መንግሥትን እንዲተቹ መረጃ የሚሰጧቸው ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡
 • እነሱ አይደሉም፡፡
 • እና የትኞቹ ናቸው?
 • እዚሁ ከተማችን የሚገኙ ምዕራባውያን ናቸው።
 • እንዴት ነው መረጃውን የሚያቀብሏቸው?
 • እራት እያበሉ ነው።
 • ምን?
 • አዎ፣ እራት ግብዣ ይጠሯቸውና መተቸት ያለባቸውን ጉዳይ ያስጨብጧቸዋል።
 • ምን ዓይነት እራት ቢሆን ነው መንግሥትን ለመተቸት ያስደፈራቸው?
 • እሱን ማወቅ አልቻልንም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምክንያቱ ይህ ጋዜጠኞቹን ለምን አታቀርቧቸውም?
 • የተወሰኑትን አብልተናል።
 • እራት?
 • አይደለም።
 • ምሣ ነው?
 • አይደለም።
 • እና ምንድነው?
 • አሳራቸውን፡፡
 • እንዴት እንደዛ ታደርጋላችሁ?
 • መፍትሔ ያመጣል ብለን አስበን ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • ጋዜጠኞችን ማሰር መፍትሔ አይደለም ብየ ስንት ጊዜ ነው የተናገርኩት? ትክክል አልሠራችሁም፡፡
 • ስህተት እንደሠራን ዘግይቶ ነው የገባን ክቡር ሚኒስትር።
 • እንዴት?
 • ጋዜጠኞቹ ቢታሰሩም ኤምባሲዎቹ ግን እራት መጋበዛቸውን አጠናክረው ነው የቀጠሉበት።
 • ሌሎች ጋዜጠኞችን መጋበዝ ነው?
 • አይደለም።
 • እና ለማን ነው የእራት ግብዣው?
 • ጋዜጠኞችን ስናስር የሚጋብዙት ዳኞችን ነው።
 • ዳኞችን?
 • አዎ።
 • ዳኞችን መጋበዝ ለምን አስፈለጋቸው?
 • ጋዜጠኞቹን በዋስ እንዲፈቱ፡፡
 • ዳኞቹ?
 • አዎ፡፡
 • በእራት ግብዣ ሊያዳክሙን እየጣሩ ነው?
 • በእራት ግብዣ የአገር ሉዓላዊነት አደጋ ላይ አይወድቅም ብለን እኛም ዕርምጃ ወስደናል፡፡
 • የምን ዕርምጃ ማን ላይ?
 • ጋዜጠኞቹን እንዳበላናቸው ዳኞቹንም…
 • እንዳትጨርሰው እንዳትጨርሰው፡፡
 • ለመቀጣጫ ብለን የተወሰኑትን አብልተናቸዋል።
 • ዳኞቹን?
 • አዎ። ግን እሱም ውግዘት አስከተለብን እንጂ አልሠራም።
 • ማሰር መፍትሔ አይደለም ብዬ የምለፈልፈው ለዚህ እኮ ነው። እናንተ ግን አትሰሙም።
 • ምን እናድርግ ታዲያ ክቡር ሚኒስትር? ዝም እንበል?
 • መፍትሔው እሱ አይደለም፡፡
 • ምንድነው ታዲያ?
 • እራት የሚያበሉትን መከታተልና መሰለል ነው መፍትሔው።
 • እነሱን መከታተል አስቸጋሪ ነው ክቡር ሚኒስትር። የሕግ ከለላ ስላላቸው ልናስራቸውም እንችልም!
 • ማሰር መፍትሔ አይደለም እያልኩህ አስሬ ማሰር ማሰር አትበልብኝ፡፡
 • እንዴት መከታተል እንችላለን ታዲያ?
 • እሱን ሲደርስ ታያለህ፡፡
 • ምን አስበው ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • እያንዳንዷን እንቅስቃሴያቸውን ከላይ ሆነን እንከታተላለን።
 • እንዴት ብለን… ሳተላይት ሳይኖረን?
 • እየገነባን ነው፡፡
 • ሳተላይት? 
 • አዎ፡፡
 • የት?
 • እንጦጦ ላይ!

[ክቡር ሚኒስትሩ ሥራ ደክመው ውለው አመሻሹን ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን የፓርላማ ውሎ ተመስጠው ሲመለከቱ አገኟቸውና በድጋሚ አብረው መከታተል ጀመሩ]

 • እንዴ? ምን ለማለት ፈልገው ነው?
 • ምን አሉ?
 • ስለ ብርጭቆ የሚሉትን አልሰማህም?
 • ሰምቻለሁ።
 • ታዲያ እንደዛ ማለት ነበረባቸው?
 • እንዴት? ትክክል አይደለም የተናገሩት?
 • ተመረመሩ የሚል ዜና ሰሞኑን ተነግሮ አልነበር እንዴ?
 • ስለምንድን እያወራሽ ያለሽው አልገባኝም? ምን ያሉ መስሎሽ ነው?
 • በእጃቸው ስለያዙት ብርጭቆ የተናገሩትን አትሰማም እንዴ አንተ ደግሞ?
 • ይችን ብርጭቆ እዚያ ጋ ሆኖ ማየትና እዚህ ጋር ሆኖ ማየት በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው ያሉትን አይደል የምትይው?
 • አዎ፡፡
 • ታዲያ ምንድነው ችግሩ?
 • ከርቀት ቢያዩትም ብርጭቆ መሆኑን የሚስቱ አይመስለኝም ምክንያቱም…
 • እ… ምክንያቱ?
 • በቅርቡ ተመርምረዋል።
 • ማን ነው የተመረመረው?
 • አባላቱ፡፡
 • ምናቸውን?
 • ዓይናቸውን!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...

ሕወሓት በትግራይ ጦርነት ወቅት በፌዴራል መንግሥት ተይዘው ከነበሩት አባላቱ መካከል ሁለቱን አሰናበተ

በሕወሓት አባላት ላይ የዓቃቤ ሕግ ምስክር የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ...

የኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት ለመፈጸም የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የሚያስችለውን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...

[ክቡር ሚኒስትሩ  የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላትን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እያዞሩ እያስጎበኙ ከአንድ ዲያስፖራ ጋር እየተወያዩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር የዛሬ ሁለት ዓመታት ገደማ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ከተማዋን ጎብኝቼ ነበር። እውነት? አዎ። ታዲያ ልዩነቱን እንዴት አዩት? በጣም ይደንቃል። ሌላ ከተማ እኮ ነው የመሰለችው። አይደል? አዎ። እንዴት ነው...