Saturday, May 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣው የወባ ሥርጭት

በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣው የወባ ሥርጭት

ቀን:

የወባ በሽታ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሐራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል ዕድሜም ሆነ ፆታ ሳይለይ የሚያጠቃ ዋነኛ የጤናና የማኅበራዊ ዕድገት ችግር ነው፡፡

የሥርጭት መጠኑም በተጠቀሱት አገሮች በተለይም ከጥቅምት ወር እስከ ኅዳር አጋማሽ ድረስ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያይልበት ነው፡፡ ጤና ሚኒስቴር እንደሚለውም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመትና የጥቅምት ወር መረጃ የሥርጭት መጠኑ ሲገመገም ከባለፉት ዓመታት ተመሳሳይ ጊዜያት ጋር ሲነጻጸር በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርትም እ.ኤ.አ. በ2020 በዓለም አቀፍ ደረጃ የወባ ሕሙማን ቁጥር በ14 ሚሊዮን ጨምሯል፡፡

- Advertisement -

ለዚህ ከአየር ፀባይ መቀያየር ጋር ተያይዞ ለወባ ትኝኝ መራባትና ሥርጭት ምቹ ሁኔታዎች መፈጠር፣ ከክረምት ዝናብና ከጎርፍ ጋር ተያይዞ በበርካታ አካባቢዎች ለወባ ትንኝ መራባት ምቹ የሆኑ ውኃ ማቆራቸው፣ የወንዞች መቆራረጥና ሌሎችም አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

በኢትዮጵያ በአንዳንድ አካባቢዎች ከፀጥታ ችግር፣ ከጎርፍና ከድርቅ ጋር ተያይዞ የሰዎች ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች መፈናቀል፣ በባለሙያዎችና በየደረጃው ባለው አመራር ዘንድ ከወባ መከላከልና ቁጥጥር አንጻር የተፈጠረ መዘናጋት መኖርና የወባ በሽታ ስለቀነሰ ‹‹ወባ ጠፍቷል›› የሚል የተሳሳተ አረዳድ መዳበሩ፣ ኅብረተሰቡ የሚቀርቡለትን የወባ መከላከያና ቁጥጥር ዘዴዎች በትክክል አለመጠቀሙ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች በጤና ተቋማት የወባ መድኃኒት አቅርቦት፣ የወባ ግብዓት መቆራረጥ መኖርና አዲስ የወባ አስተላለፊ ትንኝ ዝርያ An. Stephensi በተጨማሪነት መገኘትና መስፋፋት ችግሩ እንዲጎላ ካደረጉ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ፡፡

ጤና ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ፣ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም በአማራ ክልል በልማት ቀጣናዎች አካባቢ፣ በኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች፣ በደቡብና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልሎች የተለያዩ ወረዳዎች በተለያዩ ምክንያቶች ከፍተኛ የወባ ሕሙማን ቁጥር ሪፖርት ተደርጓል፡፡

የ2015 በጀት ዓመት እስከ ጥቅምት መጨረሻ ሪፖርት እንደሚያሳየውም፣ 2,606,094 ለሚሆኑ የወባ ሕሙማን ተጠርጣሪዎች ምርመራ ተደርጎ በወባ በሽታ መያዛቸው ለተረጋገጠ 673,919 ሰዎች የሕክምና አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡ ይህ ከ2014 ዓ.ም. ከተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀረ የህሙማን መጠን መጨመሩን ያሳያል፡፡ ይኼም ትኩሳት ኖሮባቸው ምርመራ ካደረጉ ሰዎች መካከል 26 በመቶ ወባ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት፣ ክልሎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የተለያዩ ወባን የመከላከልና መቆጣጠር ተግባራት ማከናወኑን የገለጹ ሲሆን፣ ከእነዚህም የወባ በሽታን ከመከላከል፣ ቁጥጥርና ማስወገድ አንጻር የኅብረተሰቡን ግንዛቤን ለመጨመር አምስት ዓይነት የሬዲዮና አምስት ዓይነት የቴሌቪዥን ስፖቶች ተዘጋጅተው ለኅብረተሰቡ እየተላለፉ መገኘታቸው፣ ምትክ አጎበር ሊያገኙ ለሚገባቸው ወረዳዎች የሚሠራጭ 19,753,405 አጎበር ተገዝቶ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ክትትል ተደርጎ የመጀመሪያው 2,599,650 አጎበር ከክልሎች ጋር በጋራ በተዘጋጀው ፕሮግራም መሠረት ሥርጭቱ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በዕቅድ የተያዙ 1,207,897 ቤቶችን ለመርጨት ታቅዶ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 96 በመቶ ቤቶች መረጨታቸውና የምርምርና ጥናት ሥራዎችን በመተግበርና በመደገፍ በግብዓትነት መጠቀም ላይ እየተሠራ እንደሚገኝም አክሏል፡፡

የወባ አስተላለፊ ትንኝ አዲስ ዝርያ “An. Stephensi” በተገኘባቸው በድሬዳዋ፣ ሶማሌ፣ ኦሮሚያና አፋር ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ስምንት ከተሞች ላይ እየተሠራ መሆኑንና ሕሙማንን ማከም የሚያስችል ኮአርተም፣ “Artesunate injection” እና ሕሙማንን መመርመር የሚያስችል መመርመርያ ኪት ግዥ ተፈጽሞ ለጤና ተቋማት እየተሠራጨ እንደሚገኝም ጠቁሟል፡፡

የወባ ሥርጭትን ለመግታትም በጤና ድርጀት በየደረጃው የተጠናከረ ምላሽ ከማድረግ በተጨማሪም፣ ኅብረተሰቡ የወባ ሥርጭት ከሌለባቸው አካባቢዎች ወባ ወደ ሚገኝባቸው ሥፍራዎች የሚደረግ እንቅስቃሴና ቆይታ አስፈላጊውን የመከላከልና ጥንቃቄ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ፣ የወባ ሕመም ስሜትና ምልክት ካለ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራና ሕክምና እንዲያደርግ፣ የአጎበር አጠቃቀምና የአካባቢ ቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የመኝታ አጎበሮችን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ጤና ሚኒስቴር ጥሪ አስተላልፏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...