የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ካርዲናል ብርሃነየሱስ፣ በመንግሥትና በሕወሓት መካከል የተደረሰውን ስምምነት አስመልክቶ የተናገሩት፡፡ ካርዲናሉ ለኢፕድ እንደገለጹት፣ በሁለቱ አካላት የተከወነው የሰላም ስምምነት እርሳቸውና ሌሎችም የሃይማኖት አባቶች በመልካም የሚመለከቱት ጉዳይ ነውና ተግባራዊ እንዲደረግ በመጸለይ ላይ ናቸው፡፡ ሰላምን ከሕፃን እስከ አዋቂ ሁሉም ሰው ይወዳታልና የሰላም አማራጭ በመወሰዱ ደስተኛ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡