Saturday, May 25, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

 • ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ሰላም ሰላም … ተቀመጥ!
 • አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር! ቀድሜ ቀጠሮ እንዲያዝልኝ ስጠይቅ እንደገለጽኩት በተቋሙ ሠራተኛ ተወክዬ ነው የመጣሁት።
 • እንዴ? አንተ የእኛ ተቋም ባልደረባ አይደለህም እንዴ?
 • ነኝ ክቡር ሚኒስትር!
 • ታዲያ በየትኛውን ተቋም ሠራተኛ ነው የተወከልከው?
 • በዚሁ በእኛው ተቋም ሠራተኛ ነው የተወከልኩት ክቡር ሚኒስትር።
 • እንዴት? በቀጥታ ከሠራተኛው ጋር የምገናኝበት መድረክ እያለ አንተን መወከል ለምን አስፈለገ?
 • የሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ የሚመለከት ስለሆነ በዕድሜም በልምድም አንተ ብታነጋግራቸው ይሻላል ብለው ስለወከሉኝ ነው።
 • ምንድነው ጉዳዩ?
 • ክቡር ሚኒስትር ሠራተኛው በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ነው።
 • እሱ የሁላችንም ችግር ነው … በአገር ጭምር የመጣ ነው።
 • ክቡር ሚኒስትር የመንግሥት ሠራተኛው ግን የከፋ ችግር ውስጥ ነው ያለው። በተለይ ተቋማችን …
 • ለተቋማችን ተለይቶ የመጣ ችግር ነው እንዴ?
 • አይለደም። ግን የችግሩን ጥልቀት የሚረዳልን አጥተናል።
 • ምን ማለትህ ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር እኛ ተቋም ውስጥ ያለውን ሁኔታ ቢያዩ የችግሩን ጥልቀት ይረዱታል። በቀን አንዴ ብቻ የሚመገቡ ባልደረቦቻችን እየተበራከቱ ነው።
 • እና ምን ይደረግ ነው የምትለው? ለዚህ ተቋም ብቻ የሚወሰን ነገር እንደማይኖር አታውቅም?
 • እሱን እገነዘባለሁ። በሠራተኛው የተወከልኩትም እርስዎ መፍትሔ እንዲሰጡን አይደለም።
 • እና ለምንድነው?
 • ከፍተኛ የመንግሥት አመራር እንደመሆንዎ መጠን የሚመሩት ተቋም ሠራተኞችን ችግር ለካቢኔ እንዲያቀርቡልን ወይም ጉዳዩ ሲነሳ እንዲያስረዱልን ነው።
 • ጉዳዩ እንዴት ይነሳል? ማን ያነሳዋል?
 • በሁሉም የመንግሥት ተቋማት ያሉ ሠራተኞች ተመሳሳይ ጥያቄ ይኖራቸዋል ወይም የዚህ ተቋም ሠራተኞች እኔን እንደወከሉት ሌሎቹም እንደዚያ ሊያደርጉ ይችላሉ ብዬ ነው።
 • እሺ ተነሳ እንበል …
 • ከተነሳማ በዚህ ተቋም ያሉ ሠራተኞች ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ እንዲያስረዱልንና መፍትሔ እንዲጠይቁልን ነው፡፡
 • ምን ብዬ ነው መፍትሔ የምጠይቀው?
 • ሠራተኛው በሚያገኘው ደመወዝ የኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም አልቻለም ይበሉልን።
 • እሺ … ከዚያስ?
 • ከዚያማ ሠራተኛው የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ እያቀረበ ነው ሊጨመርለት ይገባል ይበሉልን!
 • እሺ እንደዚያ አልኩ እንበል። ለደመወዝ ጭማሪ የሚሆነው በጀት ከየት እንደሚመጣ አመላክት ብባልስ?
 • እሱን በጋራ የምትመልሱት እንጂ ለእርሶ ብቻ የሚተው አይመስለኝም።
 • በጋራ መፍትሔ ለመስጠትም እኮ ሐሳብ ማቅረብ ይጠይቃል።
 • ክቡር ሚኒስትር መንግሥት የሠራተኛውን ችግር በቅንነት ከተመለከተውና ካሰበበት መፍትሔ አይጠፋም።
 • አይ አንተ … እስኪ መፍትሔ ጠቁም ብትባል አንድ መፍትሔ የለህም ለማማረር ግን…
 • ክቡር ሚኒስትር በእርሶ ያምራል ብዬ እንጂ ጠቁም ካሉኝማ እጠቁማለሁ!
 • እስኪ በላ … ?
 • መቼም የጫካ ቤተ መንግሥት ፕሮጀክት ይታጠፍ አልልም።
 • እ … ብትልስ?
 • እኔም አልልም ግን …
 • ግን ምን ልትል?
 • ይዘግይና ሰው እንታደግ እላለሁ!
 • አሃ … ለዚህ ነው የመጣኸው?
 • ክቡር ሚኒስትር በቀን አንዴ ብቻ ተመግበው የሚውሉ ባልደረቦቻችን ቁጥር እየጨመረ ነው። ጥያቄያችን ከፖለቲካ ንፁህ መሆኑንም እንዲረዱኝ እፈልጋለሁ።
 • እንዴት ነው ከፖለቲካ ንፁህ የሚሆነው?
 • እውነቴን ነው ክቡር ሚ;ለስትር!
 • እውነቱ ምንድነው?
 • የኑሮ እንጂ የፖለቲካ ጥያቄ የለንም ክቡር ሚኒስትር!
 • የቤተ መንግሥት ግንባታ ይቁም እያልክ?
 • መፍትሔ ጠቁም ስላሉኝ ነዋ!
 • ብልህስ? የቤተ መንግሥት ግንባታ ይቁም ትላለህ?
 • ተከራከር ካሉኝም ሠራተኛው እየተራበ ቤተ መንግሥት መገንባት ቅደም ተከተሉን የጠበቀ መስሎ አይታየኝም።
 • ይኸው … ዋናው ጉዳይህ ቤተ መንግሥቱ ነው።
 • አይደለም ክቡር ሚኒስትር!
 • እየሰማሁህ?
 • ክቡር ሚኒስትር ጉዳዬ መንግሥት ችግሩን ተረድቶ ደመወዝ እንዲጨምር መጠየቃችንን እንዲያስረዱልን ነው። ካልሆነ ደግሞ …
 • ካልሆነ ምን?
 • ደመወዝ ካልሆነ ደግሞ ለተማሪዎች እንደተዘጋጀው ለእኛም እንዲዘጋጅልን ነው።
 • ለእኛም ማለት?
 • ለመንግሥት ሠራተኛው ማለቴ ነው?
 • ለመንግሥት ሠራተኛው ምን ይዘጋጅ ነው ምትለው?

–        የምገባ ፕሮግራም!

–         

 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...

ያልነቃ ህሊና!

ከሽሮሜዳ ወደ አራት ኪሎ ልንጓዝ ነው። ነቀፋ አንሶላው፣ ትችት...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትር በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እንዲሳተፉ ከተለዩ ባለሀብቶች መካከል እንዱ ጋ ስልክ ደውለው በንቅናቄው ላይ እንዲሳተፉ ግብዣቸውን እያቀረቡ ነው]

መቼም ኢትዮጵያ ታምርት በሚል የተጀመረውን አገር አቀፍ ንቅናቄ ሳትሰማ አትቀርም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ልክ ነው፣ ሰምቻለሁ ክቡር ሚኒስትር። አሁን ደግሞ ንቅናቄውን ለማጠናከር ኢትዮጵያ ታምርት የሚል የታላቁ...

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት]

ውይ መጣህ እንዴ? እስኪ አረፍ በል፡፡ ምንድነው እንዲህ ያስደነቀህ? ተደንቄ ሳይሆን ግራ ግብት ብሎኝ ነው። ምኑ ነው ግራ ያጋባህ? የድልድይ ማስመረቅና የድልድይ ማፍረስ ነገር ነዋ። አልገባኝም? አለቃችሁ ድልድይ ሲያስመርቁ የተናገሩትን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በዓሉን በመኖሪያ ቤታቸው እያከበሩ ነው። ባለቤታቸውም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዳቦ ባርከው እንዲቆርሱ ለሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

በል ዳቦውን ባርክና ቁረስልንና በዓሉን እናክብር? ጥሩ ወዲህ አምጪው... አዎ! በል መርቅ... ከዓመት ዓመት ያድርሰን... ኧረ በሥርዓት መርቅ ተው? ከዓመት ዓመት ያድርሰን አልኩኝ እኮ ...አልሰማሽም? ከዓመት ዓመት መድረሱ ብቻ ምን...