Sunday, May 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊፈጠራና ቴክኖሎጂ የተሳሰሩበት ዓውደ ርዕይ

ፈጠራና ቴክኖሎጂ የተሳሰሩበት ዓውደ ርዕይ

ቀን:

በአበበ ፍቅር

ዘጠነኛው ዓለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሺፕ ሳምንትን በማስመልከት የተለያዩ   የፈጠራ ሥራዎችን የሚያሳይ ዓውደ ርዕይ ተካሄደ። በዓውደ ርዕዩ ላይ ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ባለሙያዎች የፈጠራ ሥራችውን አቅርበዋል።

በዓውደ ርዕዩ ላይ የፈጠራ ሥራቸውን ካቀረቡት መካከል መምህርት ጽዮን መንግሥቱ አንዷ ናት፡፡ መምህርት ጽዮን ፀሐይ ብርሃን (ሶላር)  በምታገኘው ጉልበት የምትሠራ ተሽከርካሪ ነው ለዕይታ ያቀረበችው። በሀመር አካባቢና በቱር ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ኮሌጅ ያለው የትራንስፖርት ችግር ሐሳቧን እንዳመነጨላት መምህርቷ ተናግራለች። በዚህ አካባቢ እናቶች ረዥም መንገድ በእግራቸው ተጉዘው ነው ማንኛውንም ሥራ የሚሠሩት። የፈጠራ ሥራዎች የሚሠሩት ደግሞ ከአካባቢ ችግር በመነሳት እንደሆነ አስረድታለች። ሌላው አካባቢው ከፍተኛ የሆነ የፀሐይ ኃይል ስላለው ያለውን የተፈጥሮ ሀብት ጥቅም ላይ ለማዋል በመነሳሳት  እንደሆነ አብራርታለች።

- Advertisement -

ማንኛውንም የተፈጥሮ ሀብት ቴክኖሎጂን በመጠቀምጰ ወደጥቅም በመቀየር ከራሳችን አልፈን ለሌሎች የሥራ ዕድልን በመፍጠር ችግር ፈቺዎች መሆን ይኖርብናል፤›› ብላለች። 

አሽከርካሪውን ጨምሮ ሰባት ሰዎችን በመያዝ በሰዓት 40 ኪሎ ሜትርን በአንድ ጊዜ ቻርጅ 120 ኪሎ ሜትርን እንደምትጓዝ ባለሙያዋ ተናግራለች። 4,000 ብር የፈጀችው ይህች መኪና ባለው የገንዘብ እጥረት ካልሆነ በቀር የተወሰኑ ማሻሻያዎች ተደርጎባት ለገበያ መቅረብ ስለምትችል የሚመለከተው አካል ድጋፍ ያድርግልን  ብላለች።

 በዓውደ ርዕዩ ኢንስትራክተር ጌጡ ሸዋንግዛው ‹‹ፎርክሊፍት››  የተሰኘ  የፈጠራ ሥራውን ይዞ ቀርቧል። ፎርክሊፍት በግንባታ ሥራው ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ታስቦ የተሠራ እንደሆነ የፈጠራ ባለሙያው አብራርቷል። እስከ አራት ሜትር ከፍታ ያለው ፎርክሊፍት የቤት ውስጥ  ቀለሞችን ለመቀባት፣ እንዲሁም የመብራት ገመዶችን በቀላሉ ለማስተካከልና መሰል ሥራዎችን ለማከናወን እንደሚያገለግል ተናግሯል።

የዲዛይንና ሌሎች ማሻሻያዎች ተደርጎበት 500 ኪሎ ግራም የሚመዝን ማንኛውንም ዕቃ በመያዝ 18 ሜትር ከፍታ ድረስ መውጣት እንደሚችል በተለይም በግንባታ ወቅት ሊደርስ የሚችለውን የእንጨት ብክነት ይከላከላል ብሏል። ሥራው 35,000 ብር ገደማ የፈጀ ሲሆን፣ አሥር በመቶ በመጨመር ለተጠቃሚዎች ገበያ ላይ እንደሚያቀርቡት ኢንስትራክተር ጌጡ አብራርተዋል። ለአጠቃቀም ምቹ የሆነና ማንኛውም ሰው በቀላሉ ሊጠቀምበት  የሚችል  ሲሆን፣ የኃይል አጠቃቀሙም አንድ ምድጃ (ስቶቭ) ሊጠቀም የሚችለው ኃይል እንደሚያንቀሳቅሰው ተናግሯል።  

እነዚህና ሌሎች የፈጠራ ሥራዎች በዓውደ ርዕዩ ለእይታ የቀረቡ ሲሆን፣ ከእነዚህ የተሻሻሉ የፈጠራ ሥራዎችን ለማቅረብ ትልቁ ፈተና የገንዘብ እጥረትና የመሥሪያ ቦታ አለመመቻቸት ተጠቃሽ እንደሆነ ሁለቱም ተናግረዋል። ካሁን በፊትም በአገር ደረጃ በርካታ የፈጠራ ሥራዎች ታይተው በሚፈለገው ደረጃ አገልግሎት ሳይሰጡ በጅምር እንደቀሩ አንስተው ተመሳሳይ ሁኔታ እንዳያጋጥም ሲሉ ሥጋታቸውን ሰንዝረዋል።

በኢንተርፕርነርሺፕ እስካሁን የነበረውን የተቆራረጠ አሠራር በማሻሻል በሚኒስቴር ደረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን ‹‹ለሚሊዮን ፈተናዎች ሚሊዮን ዕድሎችን በመፍጠር›› በቁርጠኝነት እንደሚሠራ  የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ገልጸዋል።

ትልቁ ችግር ገንዘብ ሳይሆን የአመለካከትና የክህሎት ጉዳይ መሆኑን ያነሱት ሚኒስቴር ዴኤታው ለዚህም ዜጎች ችግር ፈች አስተሳሰብ፣ ባህሪና ሥነ ምግባር ተላብሰው ሥራ ጠባቂ ሳይሆኑ ችግሮችን ወደ ወርቃማ ዕድል በመቀየር ሥራ ወይም ሀብት ፈጣሪ እንዲሆኑ እናበረታታለን ብለዋል።

የገንዘብ ችግሩንም ለመፍታት ከተለያዩ የልማት ተቋማት ጋር ለመሥራት ከስምምነት ላይ መደረሱን ለዚህም ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር በቅርበት እየሠራን ነው ብለዋል።

ከኅዳር 21 እስከ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. የተካሄደውን የኢንተርፕርነርሺፕ ሳምንትን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተለያዩ መንግሥታዊ አካላት ጋር ያዘጋጀው ሲሆን፣ በመድረኩ የታዩት አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች አገሪቱ ለጀመረችው የቴክኖሎጂ ሽግግር እንደ ማሳያ ይሆናሉ ተብሏል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...