Tuesday, April 16, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው እርጅና የተጫጫናቸው አጎታቸውን ለመጠየቅ ቢሄዱም ሚኒስትሩ ራሳቸው ተጠያቂ ሆነዋል]

 • ዛሬ እንዴት ትዝ አልኩህ ክቡር ሚኒስትር?
 • ልትመዛት ያሰብካት ነገር አለች ማለት ነው?
 • እንዴት?
 • ክቡር ሚኒስትር ብለህ ጠራኸኛ?!
 • ክቡር ሚኒስትር አይደለህም እንዴ?
 • እንደዚያ ብለህ በጠራኸኝ ቁጥር አንድ ያልተዋጠለህን ነገር ታነሳለህ። ስለዚህ ዛሬም አንድ ነገር አለ ማለት ነው።
 • አንድ ብቻ አይደለም።
 • ይኸው…?
 • እንዲያው ግን ምን እየሆናችሁ ነው? የምታደርጉትን ነገር ታውቁታላችሁ?
 • ምን አደረግን ደግሞ?
 • የበለጠ የሚያብከነክነኝ ደግሞ ይኼ ነገራችሁ ነው?
 • ምኑ?
 • የምትፈጽሙትን ስህተት እንኳን በቅጡ አትገነዘቡትም።
 • ስህተት ያልከውን ለምን አትነግረኝም?
 • የክረምቱን ዝናብና ቁር ችሎ ሕዝብ ድምፁን በሰጣችሁ ማግስት አናውቅህም አላችሁት?
 • መቼ ነው ደግሞ እንደዚህ ያልነው?
 • አንድ የሕዝብ እንደራሴ ሰሞኑን ላነሱት ጥያቄ ምን ብላችሁ ነው የመለሳችሁት?
 • ምን አልን?
 • ሕዝብ ድምፁን የሰጠው ለፓርቲያችን እንጂ እርስዎን ማን ያውቅዎታል ብላችሁ የሕዝብ ተወካይን አላንጓጠጣችሁም?
 • ማንጓጠጥ እኮ አይደለም?
 • እና ምንድነው? ለዚያውም ለሰፊው ሕዝብ በቴሌቪዥን እያስተላለፋችሁ አይደል እንዴ ያንጓጠጣችሁት?
 • አገላለጹን ላትወደው ትችል ይሆናል ነገር ግን በወቅቱ የተባለው ዓለም አቀፍ እውነታ ነው።
 • ሆሆ… የሕዝብ ተወካይን ማንጓጠጥ ነው ዓለም አቀፍ እውነታ?
 • እንደዚያ ማለቴ አይደለም።
 • እህሳ?
 • የፓርላማ ሥርዓት በሚከተሉ አገሮች ውስጥ ሕዝብ የሚወክለውን ፓርቲ እንጂ ግለሰብን አይመርጥም ማለቴ ነው።
 • አርጅቷል ምንም አያውቅም ብለህ ነው?
 • ኧረ በጭራሽ? እውነታውን ነው የነገርኩህ አጎቴ።
 • እንደዚያ ከሆነ መራጩ ሕዝብ አንድን የሕዝብ ተወካይ አልሠራልኝም ብሎ ሲያምን ማንሳት አይችልም ማለት ነው?
 • እንደዚያ እንኳ ማለቴ አይደለም።
 • ፓርቲውስ አባሉ የሆነ አንድ የሕዝብ ተወካይን ስላልፈለገው ብቻ ከሕዝብ ተወካይነቱ ሊያነሳው ይችላል?
 • ኧረ በጭራሽ። ምናልባት ከፓርቲ አባልነቱ ያሰናብተው ይሆናል እንጂ ከሕዝብ ተወካይነቱ እንኳ ማንሳት አይችልም።
 • እና አንድን የሕዝብ ተወካይ ማን ያውቅሃል፣ የተመረጠው ፓርቲያችን ነው ማለት ማንጓጠጥ አይደለም።
 • ምን መሰለህ አጎቴ?
 • ቆይ ቆይ! ልጨርስ!
 • እሺ
 • አንድ የሕዝብ ተወካይ እንደዚያ ሲንጓጠጥ ማየቴ ሲገርመኝ ትልቁን ጉድ ዘርግፋችሁት መደበቂያ አጣሁ። አሁን እንደዚያ ይባላል?
 • ምንድነው እሱ?
 • የአገሪቱ የመጨረሻ የሥልጣን አካል የሆነውን ምክር ቤት በጀት አልሰጠኸኝምና ልትቆጣጠረኝ አትችልም አላላችሁም።
 • ቆይ ላስረዳህ አጎቴ!
 • ምክር ቤቱ በጀት ባይፈቅድስ? ልማት ተብዬው የመንግሥትና የሕዝብ የጋራ ሀብት በሆነው መሬት ላይ አይደለም የሚገነባው?
 • ቆይ አጎቴ ምን መሰለህ ላስረዳህ፡፡
 • እንደዚያ ከሆነ ምክር ቤቱ ከውጭ የተገኘ ብድርና ስጦታ አጸደቀ ከምትሉን ስጦታውን ወስዳችሁ ብድር ብቻ አጸደቀ ለምን አትሉንም?
 • እንዴት ይሆናል?
 • እናንተ ዘንድ ምን የማይሆን ነገር አለ?
 • እንዴት? ምን ማለትህ ነው?
 • ከአሁን አሁን የሕዝብ ተወካዮቹ ይቃወማሉ ስል….
 • እ… ምን ሆነ?
 • አጨብጭበው እርፍ!
 • ይኸውልህ አጎቴ፣ የፓርላማ ሥርዓትን በሚከተል አገር…
 • አታስረዳኝ አልኩህ እኮ። እናንተን የሚያስልፍጋችሁ ሌላ ነገር ነው።
 • ምንድነው?
 • ትግል ነው!
 • ኪኪኪኪ… አይ አጎቴ…
 • እውነቴን ነው።
 • እንዴት?
 • አልተገነዘባችሁትም እንጂ ጊዜው የትግል ሊሆንባችሁ ነው።
 • ታዲያ ለምን አትቀላቀልም?
 • ምኑን?
 • ትግሉን?
 • መድኃኒት ላይ ነኝ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

ስለዘር ፖለቲካ

በሀብታሙ ኃይለ ጊዮርጊስ  ‹‹በቅሎዎች ዝርያችን ከአህያ ነው እያሉ ይመፃደቃሉ›› የጀርመኖች...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ? አላስታውስም። ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር ከውጭ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ምርቶች እያወሩ ነው]

እኔ እምልህ ...ኤል ሲ እንዳይከፈት ተከልክሏል ሲባል አልነበረም እንዴ? ኤል ሲ ደግሞ ምንድነው? ሌተር ኦፍ ክሬዲት ነዋ!? አልገባኝም? አስመጪዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ዕቃ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች አይደል የሚያገኙት? አዎ። ኤል...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሥራ መልስ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን በተመስጦ እየተከታተሉ አንዳንዴም በመገረም እየሳቁ አገኟቸው]

አንዴ? ምን አገኘሽ? ምን አገኘሽ ማለት? ለብቻሽ የሚያስቅሽ ማለቴ ነው? እ... ምን ላድርግ ብለህ ነው? ወዶ አይስቁ ሆኖብኝ ነው። እንዴት? ምንድነው ነገሩ? በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን እያዳመጥኩ ነዋ? አለቃ ከሕዝብ ተወካዮች ጋር...