Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊተጠያቂነቱ የተዘነጋው ሕፃናትን ለውትድርና መመልመል

ተጠያቂነቱ የተዘነጋው ሕፃናትን ለውትድርና መመልመል

ቀን:

ማንኛውም ሕፃን በግጭት ወቅትም በሕይወት የመኖር ተፈጥሯዊ የሆነ መብት አለው፡፡ ስለዚህም አገሮች የሕፃናትን ህልውና እና ዕድገት በተቻላቸው መጠን ማረጋገጥ እንዳለባቸው በየጊዜው ይስተጋባል፡፡ 

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት፣ በግጭት ወቅት በሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ስድስት ከባባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እንደሚከተለው ይዘረዝራል፡፡  ሕፃናትን መግደል እና አካል ጉዳተኛ ማድረግ፣ ሕፃናትን ለውትድርና መቅጠር ወይም ማዋል፣ በሕፃናት ላይ ወሲባዊ ጥቃት ማድረስ፣ ሕፃናትን መጥለፍ፣  በትምህርት ቤቶች እና የጤና ተቋማት ላይ ጥቃት ማድረስ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ለሕፃናት መከልከል ናቸው፡፡ ከነዚህ ከተዘረዘሩት ጥሰቶች አንዱ ሕፃናትን ለውትድርና መመልመሉ ነው፡፡

የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች የሕፃናትን ለውትድርና ምልመላ በተመለከተ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ጥናታቸውን ያቀረቡት የሕግ ባለሙያና አማካሪ ሽመልስ ሲሳይ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትን፣ ለወታደራዊ አገልግሎት መመልመል ተጠያቂ ያደርጋል፡፡ ቅጣቱም ከፍተኛ ከሚባሉት ውስጥ የሚመደብ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ትልቁ ችግር ሕፃናትን ለውትድርና የሚመለመሉት ሕገወጥ ታጣቂ ቡድኖች በመሆናቸው ለተጠያቂነት አመቺ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሕፃናት ለጦርነት ሲሳተፉ የሚያሳዩ ምሥሎችን ቢታዩም፣ በሕጉ መሠረት ተጠያቂነት ማስፈን እንዳልተቻለ የሕግ ባለሙያ ያስረዳሉ፡፡

ድርጅቱ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አገሮች የተደረጉ የእርስ በርስ ጦርነቶች ላይ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ሕፃናት እንደተሳተፉም ተገልጿል፡፡ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ለውትድርና ለመመልመል ዕድሜ ሳይሆን አካላዊ ሁኔታን ማየት በቂ ተደርጎ ይወሰድ እንደነበር ያስታወሱት የሕግ ባለሙያው፣ በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ መሠረት ከ18 ዓመት በታች የሆናቸውን ሕፃናት ለወታደራዊ አገልግሎት የመለመለ፣ በቀጥታም ያሳተፈ አካል ቅጣቱ ከአምስት እስከ 20 ዓመታት ፅኑ እስራት፣ አልፎም ከዕድሜ ልክ እስከ የሞት ቅጣት እንደሚበየንበት አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የችግሩ ስፋት አሳሳቢ ቢሆንም፣ ስለተወሰደ ዕርምጃ አይታወቅም ይላሉ፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተደረገው የሰሜኑ ጦርነት ሕፃናትን በጦርነቱ መሳተፋቸውን የሚያሳይ ምሥል በማኅበራዊ ሚዲያው መታየቱን ያስታውሳሉ፡፡

መንግሥትም ችግሩን ከማንሳት የዘለለ ክስ አቅርቦ ተጠያቂነት ሲያስፍን አይስተዋልም ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮች ላይ መንግሥት ክስ ቢመሠርትም ክሳቸው ከአገር ክዳት፣ ሕገመንግሥት በኃይል በመናድና በመሳሰሉት እንደነበረ ያስታውሳሉ፡፡

በጥናቱ መሠረት ክሶች ሲቀርቡ በአንዱም ሕፃናትን በጦርነት ላይ በመጠቀሙ ክስ የቀረበበት አካል አለመኖሩን ይጠቅሳሉ፡፡ ለዚህ ሁሉ ችግር ትልቁ መፍትሔ ያሉት ማኅበረሰቡን ማሳወቅና ማስተማር ነው፡፡

መረጃዎችን ዋቢ አድርገው የተናገሩት የሕግ ባለሙያው፣ በዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ 300 ሺሕ ሕፃናት ለውትድርና ይመለመላሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...