Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሕፃናት ጆሮ ለምን ይታመማል?

የሕፃናት ጆሮ ለምን ይታመማል?

ቀን:

የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በዓለም ውስጥ 7.5 ሚሊዮን ሕፃናት የመስማት ችግር ያጋጥማቸዋል፡፡ ችግሩ ከሚያጋጥማቸው ውስጥ ከ25 በመቶ እስከ 80 በመቶ የሚሆኑት በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች የሚኖሩ ናቸው፡፡

በእዚህም አገሮች የሚኖሩ አብዛኛው ዜጎች በተፈጥሮም ይሁን በሰው ሠራሽ ምክንያቶች የዚህ ችግር ገፈት ቀማሽ ሆነዋል፡፡ የችግሩ መከሰት ብቻ ሳይሆን የጆሮ ሕመምን ለማከም፣ ቀድሞ ችግሩን ለመለየትና መፍትሔ ለማድረግ የሚያስችል የተሟላ ሕክምና የሚሰጡ ባለሙያዎች፣ ቁሳቁሶችና ለዚሁ ተብለው የተዘጋጁ የሕክምና ተቋማት በአግባቡ አለመኖርም፣ በተለይ ለደሃ አገሮችና ለሕዝቦች ፈተና ሆኗል፡፡ በአብዛኛው ተጋላጭ የሆኑት ደግሞ ሕፃናት ናቸው፡፡

በኢትዮጵያም የሕክምና አገልግሎት አሳጣጡ ላይ ክፍተት መኖሩና መንግሥት ለዘርፉ የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ መሆኑ ዕርዳታ ሳያገኙ ከችግሩ ጋር የሚኖሩ  የሕሙማን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹መስማት ለኢትዮጵያ›› የተሰኘ ድርጅት በጨቅላ ሕፃናት ደረጃ የመስማት ችግር እንዳይከሰትና አስፈላጊውን የሆነ የሕክምና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን፣ ሰሞኑን ከባለድርሻ አካላት ጋር በነበረው ውይይት ላይ አስታውቋል፡፡

የውይይቱን መነሻ ሐሳብ ያቀረቡት የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከአንገት በላይ ሐኪም ነቢያት ተፈሪ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ጨቅላ ሕፃናት ከተወለዱ በኋላ የመስማት ችግሮች በጊዜ እንዲታወቁና ማኅበረሰቡም የችግሩን አሳሳቢነት እንዲረዳ ለማስቻል ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

በኢትዮጵያ በሰው ሠራሽ አደጋዎችም ሆነ በተፈጥሮ መስማት የተሳናቸው ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንና የጨቅላ ሕፃናትን ጆሮ የመስማት ችሎታ የሚመረምር ምንም ዓይነት ፕሮግራም አለመኖሩም ችግሩን እንዳባባሰው ነቢያት (ዶ/ር) ጠቁመዋል፡፡

የጨቅላ ሕፃናትን የመስማት ችሎታ ለማወቅ የአንድ ቀን ምርመራ ብቻ በቂ ቢሆንም፣ አሠራሩ በኢትዮጵያ ባለመለመዱ በርካታ ሕፃናት ለችግሩ ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸውን አብራርተዋል፡፡

በአብዛኛው ሕፃናት የመስማት ችግር እንዳለባቸው የሚታወቀው ሦስት ዓመት የዕድሜ ክልል ላይ ሲደርሱ መሆኑንና ለዚህም ምክንያቱ ቀደም ብለው ምርመራ ሳይደረግላቸው በመቆየታቸው እንደሆነ አክለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የመስማት ችሎታን የሚመረምሩ የሕክምና ተቋማት ባለመኖራቸው ችግሩን አባብሶታል የሚሉት ነቢያት (ዶ/ር)፣ ችግሩን ለመታደግ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የሕክምና አገልግሎቱን ከሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ውስጥ ስለበሽታው በቂ ግንዛቤ የሌላቸው እንዳሉና በተለያዩ ጤና ተቋማት ውስጥ ለሕክምና የሚሆኑ ምንም ዓይነት የመመርመርያ ግብዓት አለመኖሩ ችግሩን ይበልጥ አጉልቶታል ብለዋል፡፡

በቀጣይ ዓመትም መስማት ለኢትዮጵያ በተመረጡ ሆስፒታሎች ላይ የጨቅላ ሕፃናትን የመስማት ምርመራ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን፣ ይህም ዘርፉ ላይ ያሉትን ችግሮች በተወሰነ መልኩ ከመቅረፍና ጤና ሚኒስቴር ያሉበትን ክፍተቶች ለማሳየት ሊረዳን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ጤና ሚኒስቴርም ችግሩን የራሱ አድርጎ እንዲሠራ ድርጅቱ የበኩሉን የሚወጣ መሆኑን፣ ለመጀመርያ ያህል የተወሰኑ የመመርመርያ ግብዓቶችን ለተወሰኑ የሕክምና ተቋማት ተደራሽ የሚያደርግ እንደሆነም አክለዋል፡፡

ሕፃናት ገና ሲወለዱ ለመስማት ችግር ተጋላጭ እንዳይሆኑ አስቀድሞ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት እንደሚኖርባቸው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የአንገት በላይ ስፔሻሊስትና የጆሮ የመስማት ችግሮች ሐኪም ሚካኤል ከበደ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የመስማት ችግር የሚታይ ነገር ባለመሆኑ የተነሳ አብዛኛዎቹ ሕፃናት በሽታው ቢኖርባቸውም፣ ወላጆች የልጆቻቸው ጆሮ እንደማይሰማ የሚያውቁት የልጆቹ ዕድሜ ከፍ ሲል መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡

ሕፃናት ተወልደው አንድ ወር ሲሞላቸው የመስማት ችሎታ ምርመራ ማድረግ እንደሚኖርባቸው፣ ነገር ግን በኢትዮጵያ ይህ አሠራር ባለመዘርጋቱ በርካታ ሕፃናት ከመስማት ችግሮቻቸው ጋር እንደሚኖሩ ሚካኤል (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡

መስማት ለኢትዮጵያ በጆሮ ሕመምና አለመስማት ዙሪያ ያሉትን ተግዳሮቶች ለመታደግ የተቋቋመ መሆኑን የተናገሩት የአንገት በላይ ስፔሻሊስቱ፣ 50 በመቶ የመስማት ችግር ያለባቸው ሕፃናት ምንም ዓይነት ምልክት እንደማይታይባቸው አብራርተዋል፡፡

ባደጉት አገሮች የመስማት ችሎታ ምርመራ የተለመደ መሆኑን፣ አብዛኛውን ጊዜም በኢትዮጵያ ለምርመራ የምንጠቀምባቸው አዮንና ኤያር እስክሪን ማሽኖች በርካታ የሕክምና ተቋማት ላይ ባለመኖራቸው የተነሳ የሕክምና አገልግሎቱ ተደራሽ አለመሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በዘርፉ ላይ የሠለጠነ የሰው ኃይል አለመኖሩም ሌላው ችግር ነው፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ድርጅቱ ውጭ አገር ከሚገኙ አጋሮች ጋር ለጤና ባለሙያዎች ሥልጠና ለመስጠት ዕቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ድርጅቱ በቀጣይ ማሽኖችን በመግዛትና ለተመረጡ ሰባት የሕክምና ተቋማት በመስጠት አገልግሎቱን የሚሰጥ መሆኑን፣ ይህ ተግባራዊ ከተደረገ በርካታ ሕፃናትን መታደግ ይቻላል ብለዋል፡፡

ለመስማት ችግር የተጋለጡ፣ ራሳቸውን ከማኅበረሰቡ የሚያገሉ መሆኑን፣ ከሚወለዱት ከአንድ ሺሕ ሕፃናት ውስጥም ስድስቱ ለመስማት ችግር ተጋላጭ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያም የመስማት ችግር ያለባቸው ዜጎች ምን ያህል ናቸው? የሚለውን ለማወቅ በቂ ጥናት አለመደረጉን፣ ነገር ግን በርካታ ሕፃናት በአሁኑ ወቅት የችግሩ ሰለባ እየሆኑ መምጣታችቸውን ገልጸዋል፡፡

የጆሮ ሕመም በተለያዩ ምክንያቶች ይከሰታል፡፡ ከእነዚህም የጆሮ ኩክ ለረዥም ጊዜ መጠራቀም፣ በጭንቅላት ወይም በጆሮ ላይ የሚደርስ አደጋ፣ ከፍተኛ ድምፅ፣ መርዛማነት ያላቸው መድኃኒቶች፣ ከሥራ ጋር የተያያዙ መርዛማ ኬሚካሎች፣ በቫይረስ አማካይነት የሚከሰት ኢንፌክሽንና አንዳንዴ በዘርና በዕድሜ መግፋት የሚተላለፉ ያለመስማት ችግሮች ይጠቀሳሉ፡፡  

ከእነዚህ በአንዱ ወይም በሌላ ምክንያት የመስማት ችግር ያሉባቸው ሰዎችም ሌሎች ሰዎች በግልጽ የሚሰሙትን ያለመስማት፣ በተለይ ጫጫታ ባለባቸው ሥፍራዎች የተነገራቸውን በቅጡ አለመስማት፣ ከሰዎች ጋር ሲነጋገሩ ድገምልኝ እያሉ በተደጋጋሚ መጠየቅ፣ ሙዚቃ ሲያዳምጡ ወይም ቴሌቪዥን ሲመለከቱ ሌሎች ሰዎች ከሚፈልጉት ልክ በላይ ከፍተኛ ድምፅ መፈለግና በስልክ ሲያወሩ ለመስማት መቸገር የመስማት ችግር ያለባቸው ሰዎች የሚሳዩዋቸው ምልክቶች ናቸው፡፡

የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ድርጅት እንደሚለው፣ በከፍተኛ ድምፅ ምክንያት ለተከሰተ የመስማት ችግር የመድኃኒትም ሆነ የቀዶ ሕክምና የለም፡፡ በመሆኑም ቤተሰቦች ለራሳቸውም ሆነ ለልጆቻቸው ጆሮና የጆሮ መስማት ደኅንነት በተቻለ መጠን ከፍተኛ ድምፅ ካለባቸው ቦታዎች ራሳቸውን ማራቅ አለባቸው፡፡ ከፍተኛ ድምፅ ባሉባቸው አካባቢዎች አቅም ካለ ጆሮን ድምፅ እንዳይገባ በሚከላከሉ መሣሪያዎች መክደን፣ የጆሮ ማዳጫ የሚጠቀሙ ከሆነ ድምፁን መቀነስ፣ የጆሮ ኩክን የሕክምና ባለሙያ በሚያዘው መሠረት ማፅዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የደም ግፊትንና የልብ ጤናን መጠበቅ፣ አለማጨስና የአልኮል መጠጥን መገደብ፣ የስኳር መጠንን መቆጣጠር፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴንና ድብርትን ማስወገድም ለጆሮና መስማት ጤና ይመከራሉ፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...