Tuesday, May 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊጤና ሚኒስቴር ጥራት ያላቸው መረጃዎች ማግኘት ፈተና ሆኖብኛል አለ

ጤና ሚኒስቴር ጥራት ያላቸው መረጃዎች ማግኘት ፈተና ሆኖብኛል አለ

ቀን:

  • አሠራሩን ለማሻሻል የሚያስችል ‹‹የመረጃ አብዮት ጥናት›› ይፋ ተደርጓል

በኢዮብ ትኩዬ

የጤና ሚኒስቴር በየክልሉ ባሉ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ከጤና ተቋማት ጥራት ያላቸው መረጃዎች ማግኘት ፈተና እንደሆነበት ታኅሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል ባካሄደው ውይይት ላይ አስታወቀ፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች ከታች ካሉ ጤና ኬላዎች ጀምሮ ወደ ጤና ሚኒስቴር የሚመጡ መረጃዎች፣ የጥራት ክፍተት ፈተና መሆናቸውን፣ በጤና ሚኒስቴር የፖሊሲ ዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር አቶ መሱድ መሐመድ ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

በዚህም ምክንያት የመረጃ አጠቃቀምን የተሻለ ማድረግ ለማስቻል፣ በተመረጡ ስድስት የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ‹‹የመረጃ አብዮት ጥናት›› ይፋ ተደርጓል ብለዋል፡፡

የጥናቱ ዋነኛ ዓላማ የመረጃ አብዮት ማሻሻል ተብሎ በጤናው ሴክተር ከሰባት ዓመታት በፊት የተያዘውን ዕቅድ፣ የተለያዩ አካላት እንዲሠሩት ማድረግ፣ ከታች ጀምሮ ወደ ጤና ተቋማት የሚያቀኑ መረጃዎችን ጥራት የተሻሻለ ማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ጥናቱ የነበሩ አሠራሮችን በማሻሻል (ለአብነትም በማኑዋል የተሰበሰቡትን መረጃዎች በዲጂታል አድርጎ መረጃዎችን ማግኘት የሚያስችል) ዓላማን ጭምር ያነገበ መሆኑን አቶ መሱድ አብራርዋል፡፡

በአገር ደረጃ በ2008 ዓ.ም. በጤናው ዘርፍ የመረጃ አብዮት (information revolution) እንቅስቃሴ ተጀምሮ፣ በየጤና ተቋማቱ መረጃዎች በጥራትና በብዛት በየጊዜው እየላኩ እስከ ከክልል ወረዳዎች ይመጡ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

እንደዚያም ሆኖ በየክልሉ በሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች የጤና ተቋማት የመረጃ ጥራት ክፍተት ችግር ፈተና በመሆኑ፣ በኢትዮጵያ በተመረጡ ስድስት ዩኒቨርሲቲዎች የመረጃ አብዮት ጥናት እንዲካሄድ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ይህ ጥናት ቀድሞውን በጤና ሚኒስቴር ከታች ያሉ መረጃዎች በገለልተኛ አካል እንዲጠኑ ታቅዶ ነበር ያሉት አቶ መሱድ፣ ጥናቱ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት የመረጃ አብዮት ዕቅድን ከማሳካት አኳያ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በ2008 ዓ.ም. የመረጃ አብዮትን በዲጂታላይዝድ፣ በካልቸራል ትራንስፎርሜሽንና በገቨርናንስ ብሎ ሲቀርፅ፣ በአፋርና በትግራይ ክልሎች መቀሌ ዩኒቨርሲቲን፣ በአማራና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ጎንደር ዩኒቨርሲቲን፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን፣ በሶማሌ፣ በድሬዳዋና በሐረር ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲን፣ በደቡብ ክልል (ሲዳማን ጨምሮ) ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲን፣ እንዲሁም በጋምቤላና በኦሮሚያ ክልል ዕገዛ ለማድረግ ጅማ ዩኒቨርሲቲን የመረጃ አብዮት ጥናትን መሬት ላይ ለማውረድ ያግዛሉ ተብለው ተመርጠው ነበር ተብሏል፡፡

ከተመረጡት ስድስት ዩኒቨርቲዎች በየክልሉ የተመደቡ አካላት በበኩላቸው የመረጃ አብዮት ጥናት ማካሄዳቸውን ጠቁመዋል፡፡ በመረጃ አብዮቱ ላይ የሰው ኃይል እጥረት ትልቅ ፈተና መሆኑን በጥናቱ ስለማረጋገጣቸው የጤና ሚኒስቴርና ዩኒቨርሲቲዎች በሚያደርጉት የአቅም ግንባታና ክትትል በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮግራም መሪ የሆኑት አድማስ አበራ (ረዳት ፕሮፌሰር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡

በዚህም ከማኅበረሰቡ መረጃ በመሰብሰብ በጤና ሚኒስቴር ዕይታ ውጭ ሆነው የነበሩ ችግሮችን ድንገተኛ፣ ዕጩ፣ ሞዴልና ዲጅታል ብሎ በመለየት በገለልተኛ አካል የተደረገ ጥናት ይፋ መደረጉን፣ ይህ ጥናትም በመረጃ አብዮት ረገድ ለወዲፊት የመረጃ ጥራትንና አጠቃቀምን በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት ለማሻሻል እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

በመረጃ አብዮት ባለፉት አምስት ዓመታት የተለያዩ አመርቂ ውጤቶችን በማምጣት፣ ከዚህ በፊት ከአሁን ጋር ሲነፃፀር ኢትዮጵያ አሁን የተሻለ ደረጃ ላይ ብትሆንም፣ የመረጃ አብዮት ሰፋ ያለና ብዙ ለውጦችን የሚፈልግ በመሆኑ፣ ገና ብዙ መሻሻል ያለባቸው ነገሮች እንዳሉም በጥናቱ ማረጋገጥ ስለመቻሉ አድማስ (ረዳት ፕሮፌሰር) ገልጸዋል፡፡

አክለውም በመሠረተ ልማት ግንባታ፣ በሰው ኃይል ማነስና በሌሎች መሰል ምክንያቶች የመረጃ አብዮት ጥናት ፈታኝ መሆኑን በጥናቱ መረጋገጡን አስረድተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ መምህራን ጥናቱን ከማጠናቀር ባሻገር ተማሪዎችን ሲያስተምሩ መሬት ላይ ያለውን እውነታ መሠረት እንዲያደርጉ፣ ችግሮችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ተንትነው ለመንግሥት እንዲያሳውቁ፣ እንዲሁም ለአቅም ግንባታ ሥራዎች ሥልጠና በመስጠት በማገዝ ዕርዳታ እንደሚያደርጉ ተጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...