Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊብሪቲሽ ካውንስል የእንግሊዘኛ ቋንቋ መመዘኛ ፈተናን በአምስት ዩኒቨርሲቲዎች ሊሰጥ ነው

ብሪቲሽ ካውንስል የእንግሊዘኛ ቋንቋ መመዘኛ ፈተናን በአምስት ዩኒቨርሲቲዎች ሊሰጥ ነው

ቀን:

  • በጦርነት ለወደሙ ትምህርት ቤቶች ከ30 ሺሕ በላይ መጻሕፍትን እያሰባሰበ ነው

የእንግሊዝ መንግሥት ቋንቋና ባህል ማዕከል የሆነው ብርቲሽ ካውንስል በአዲስ አበባ ብቻ ይሰጥ የነበረውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ መመዘኛ ፈተና፣ በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁንና በቅርቡም ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

በጎንደር፣ ሐዋሳ፣ ባህር ዳር፣ ሐሮማያና ጂማ ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናውን ለመስጠት ተቋሙ ስምምነት እንደጨረሰ ገልጿል፡፡ ይህን የቋንቋ መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ተፈታኞች አዲስ አበባ መምጣት ሳይጠበቅባቸው በአቅራቢያቸው ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ተቋሙ ባመቻቸው ሁኔታዎች መፈተን እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

በተቋሙ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዓለማየሁ እንደተናገሩት፣ ይህ ወደ ውጭ አገሮች ሄዶ ትምህርት ለመማርም ሆነ ሥራ ለመሥራት ጠቃሚ ነው ብለው የገለጹትን ፈተና፣ ከአዲስ አበባ ውጪ ተደራሽነቱን በማስፋት፣ ተፈታኞች አዲስ አበባ መምጣት እንደማይጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡ አሁን ‹‹ከእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ውል ፈጽመን በቀጣይ ደግሞ ከሌሎችም ዩኒቨርሲቲዎች ጋር አብረን እንሠራለን፤›› ብለዋል፡፡ የተቋሙ በኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ነፃነት ደመወዝ ስለ ፈተናው ሲገልጹ፣ አቅም ያላቸው ተማሪዎች በአገር ውስጥ ብቻ ተወስነው እንዳይቀሩና ፈተናውን ተፈትነው ዓለም ከሚሰጠው የትምህርት አማራጮች ላይም መጠቀም እንዲችሉ ያደርጋል ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ብሪቲሽ ካውንስል ይህን በእንግሊዝኛ (International English Language Testing System IELTS) የሚባለውን የእንግሊዝኛ ብቃት መመዘኛ ፈተና፣ በኢትዮጵያ መስጠት ከጀመረ ከአሥር ዓመት በላይ ሲሆነው፣ በዓመትም ከ4000 እስከ 5000 ሰዎችን ይፈትናል፡፡ ተቋሙ ሌሎችንም የሙያ ፈተናዎች የሚሰጥ ሲሆን ለእንግሊዝኛ መመዘኛ ፈተናው በአንድ ተፈታኝ 198 የእንግሊዝ ፓውንድ ያስከፍላል፡፡

ተቋሙ በኢትዮጵያ ሥራ ከጀመረ 80 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ይህን 80 ኛ ዓመት በማስመልከት የተለያዩ ክንውኖችን ለማካሄድ ዕቅድ ይዟል፡፡ ከእነዚህ ክንውኖች መካከል አንደኛው ከተቋሙ ጋር ከዚህ በፊት በተለያዩ መንገድ አብረው የሠሩ ተቋማትንና ግለሰቦችን በማስተባበር በኢትዮጵያ ግጭት በተፈጠረባቸው አካባቢዎች ለወደሙ ትምህርት ቤቶች ቤተ መጻሕፍት የሚውል መጻሕፍትን ማሰባሰብ ነው፡፡

ከእነዚሀ አካላት ከእያንዳንዳቸው ቢያንስ 80 መጻሕፍትን ለመሰብሰብ እንዲሁም በአጠቃላይ የተሰበሰቡትን መጻሕፍትን የሚያክል ደግሞ ማዕከሉ በራሱ በመጨመር ለመለገስ ያቀደ ሲሆን፣ በአቃላይ ቢያንስ 30 ሺሕ የሚሆን መጻሕፍትን ለማሰባሰብ መታቀዱን ኃላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡ ‹‹እያንዳንዱ ከዚህ በፊት ከእኛ ጋር የሠራ አካል ይህን ተነሳሽነት በመቀላቀል መጻሕፍትን ለወደሙ ትምህርት ቤቶች ለማሰባሰብ እንዲረዳን እንጠይቃለን፤›› ሲሉ አቶ ነፃነት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በትናንትናው ዕለት ማክሰኞ ታኅሣሥ 4 ቀን 2022 ከተቋሙ ጋር ከዚህ በፊት አብረው የሠሩና አሁንም በመሥራት ላይ የሚገኙ ተቋማትና ግለሰቦችን በማሰባሰብ በኔክሰስ ሆቴል በሰጡት ምስክርነት፣ የተቋቋመለትን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በደንብ የተወጣ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አቶ ነፃነትም ሲገልጹ መንግሥትና ፖሊሲዎች ቢቀያየሩም ተቋሙ ግን ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አድርጓል ብለዋል፡፡

በትምህርት፣ በእንግሊዝኛ፣ እንዲሁም ጥበባትና ባህል ላይ በዋነኛነት የሚሠራው ተቋሙ፣ ትምህርትን በተመለተ በመማርና ማስተማር ጥራት ላይ በሠሩት ሥራ ከ11,000 በላይ መምህራንና ከ5,000 በላይ የትምህርት ኃላፊዎች ጋር በመላው ኢትዮጵያ አብረው መሥራታቸውን ተገልጿል፡፡ በእንግሊዚኛ ቋንቋ ላይ በተመለከተም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን የትምህርት ካሪኩለሙን፣ የመምህራንና መማርያ ቁሳቁስን ያካተተ ፕሮግራም በመቅረጽ ላይ እንዳሉ ተገልጿል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...