Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናሲሚንቶ አየር በአየር ሸጠዋል የተባሉ ሁለት የደኅንነት ኃላፊዎች በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰሱ

ሲሚንቶ አየር በአየር ሸጠዋል የተባሉ ሁለት የደኅንነት ኃላፊዎች በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰሱ

ቀን:

  • ለግል ጥቅማቸው ያዋሉት ገንዘብ 30 ሚሊዮን ብር መሆኑ ተጠቁሟል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሁለት ኃላፊዎችና ሁለት ባለሙያዎችኧ ተቋሙ ሳያውቅና እንዲገዛ ምንም ዓይነት ትዕዛዝ ሳይሰጥ፣ ሲሚንቶ በተቋሙ ስም በመግዛትና አየር በአየር በመሸጥ ከባድ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

ተከሳሾቹ በአገልግሎቱ የኮንስትራክሽንና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ደሜ፣ ምክትል ዋና ክፍል ኃላፊ አቶ አሸናፊ ተስፋዬ፣ እንዲሁም በአገልግሎቱ የግዥ ባለሙያዎች አቶ ቱጁባ ቀልቤሳና አቶ ሙስጠፋ ሙሳ ሲሆኑ፣ ሰኞ ታኅሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም. በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀርበው ክስ ተነቦላቸዋል፡፡

ክሱን የመሠረተው የፍትሕ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ ክስ እንደተገለጸው፣ በአገልግሎቱ የኮንስትራክሽንና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ፣ ተቋሙ ሲሚንቶ የመግዛት ፍላጎት ሳይኖረው እንዳለው በማስመሰል፣ ‹‹ለአስቸኳይ የግንባታ ሥራ የሚውል›› በማለት 29,200 ኩንታል ሲሚንቶ ከደርባ እና ከዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች እንዲገዛ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ ትዕዛዙ የተላለፈላቸውና በስማቸው አራት ደብዳቤ የተጻፈላቸው አቶ ሙስጠፋና ሁለት ደብዳቤ የተጻፈላቸው አቶ ቱጁባ፣ ለሲሚንቶ መግዥያ የሚውለው ገንዘብ በየግል አካውንታቸው እንዲገባ ካደረጉ በኋላ፣ ገንዘቡን ወደ ሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ ገቢ በማድረግ የሲሚንቶ ግብይቱን መፈጸማቸውን ያብራራል፡፡

ከላይ ለተገለጹት ተከሳሾች ገንዘቡ በግል አካውንታቸው ገቢ እንዲደረግ፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብዳቤ የጻፉት፣ በአገልግሎቱ የኮንስትራክሽንና ሎጂስቲክስ ዋና ክፍል ኃላፊ አቶ አሸናፊ ተስፋዬ መሆናቸውንም የዓቃቤ ሕግ ክስ ይገልጻል፡፡

ተከሳሾቹ ማንኛውም ግዥ በተቋሙ የግዥ ሠራተኞችና በተቋሙ አካውንት መፈጸም ሲገባውና ለንብረት ክፍል ማስረከብ ቢኖርበትም ግዥውን በራሳቸው በመፈጸምና በየግል አካውንታቸው በገባ ከፍተኛ ገቢ ክፍያ በመፈጸም፣ ሲሚንቶ ወደ ተቋሙ ሳይደርስ አየር በአየር በመሸጥ፣ በወቅቱ በነበረ የአንድ ኩንታል ሲሚንቶ ዋጋ 1,030.80 ብር በድምሩ 30,099,360 ብር ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሮ አቅርቧል፡

ተከሳሾቹ ክሱ ተነቦላቸው በቀረበው ክስ ላይ መቃወሚያ ካላቸው ለመጠባበቅ፣ ለታኅሳስ 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...