Wednesday, April 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምአሜሪካ ከምታስተናግደው የአሜሪካ - አፍሪካ ጉባዔ ምን ይጠበቃል?

አሜሪካ ከምታስተናግደው የአሜሪካ – አፍሪካ ጉባዔ ምን ይጠበቃል?

ቀን:

በአሜሪካና በአፍሪካ መካከል የንግድ ዕድሎችን ያሰፋል፣ አሜሪካ ከአፍሪካ መሪዎች ዘንድ ተዓማኒነትን ትገነባበታለች የተባለው የአሜሪካ-አፍሪካ ጉባዔ ትናንት ታኅሣሥ 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በዋሽንግተን መካሄድ ጀምሯል፡፡

ለሦስት ቀናት በሚዘልቀው ጉባዔ የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ቀውስ፣ በመልካም አስተዳደር፣ በምግብ ዋስትና፣ በጤናና የአሜሪካና አፍሪካ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ማሳደግ በሚሉትና በሌሎች መሠረታዊ ችግሮች ዙሪያ የሚያተኩር ይሆናል፡፡

የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪን ጄክ ሳልቨን ጠቅሶ አልጀዚራ እንደዘገበው፣ ጉባዔው ለአፍሪካ የጂኦፖለቲካ ጠቀሜታ ዕውቅናን ከመስጠት የመነጨ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹አኅጉሪቷ የአፍሪካውያንን የወደፊት ሕይወት ብቻ ሳይሆን ዓለምን የምትቀርፅ ናት፤›› ሲሉም ሳልቨን ተናግረዋል፡፡

አሜሪካ ከምታስተናግደው የአሜሪካ - አፍሪካ ጉባዔ ምን ይጠበቃል? | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የአፍሪካ ልዑካን ሜሪላንድ ሲደርሱ

 በጉባዔው 49 የአፍሪካ መሪዎች እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት የተጋበዙበት ሁለተኛው የአሜሪካ-አፍሪካ ጉባዔ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከስምንት ዓመታት በፊት ያደረጉት ጉባዔ ተከታይ ነው ብለዋል፡፡ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ ዋሽንግተን ያስተናገደችው ትልቁ ዓለም አቀፍ ጉባዔ መሆኑንም አክለዋል፡፡

በዶናልድ ትራምፕ የፕሬዚዳንትነት ወቅት የአፍሪካና ሌሎችም አገሮች ከአሜሪካ ጋር የነበራቸው ግንኙነት ተሸርሽሮ የነበረ ቢሆንም፣ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አገራቸው ከአገሮች፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ከሌሎችም ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚፈልጉም ጠቁመዋል፡፡

በትራምፕ ዘመን የተቀዛቀዘውን የአሜሪካ አፍሪካ ግንኙነት የባይደን አስተዳደር ባለሥልጣናት፣ በአፍሪካ በተቋማት ሥር ከተሰባሰቡ አገሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተውት ነበር፡፡

ከኮንግረሱ ጋር በቅርበት በመሥራትም አሜሪካ ለአፍሪካ በቀጣይ ሦስት ዓመታት ውስጥ 55 ቢሊዮን ዶላር እንድትሰጥ ማመቻቸታቸውን ሳልቫን ጠቁመዋል፡፡  

ከአፍሪካ አገሮች ውስጥ የእርስ በርስ ጦርነት ያልለቀቃቸው፣ በአየር ንብረት ለውጥና በድርቅ፣ በጤናና፣ በሥራ አጥነት በአጠቃላይም የፖለቲካ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ሕይወት ቀውስ ውስጥ የገቡ አገሮች ቢኖሩም፣ በአኅጉሪቱ ያልተነካ የተፈጥሮ ሀብት አለ፡፡ በአፍሪካ ለእርሻ ሊሆን የሚችል ያልታረሰ መሬት አለ፡፡

ነዳጅን ጨምሮ የከበሩ ማዕድናት፣ የደን ሀብትና ሌሎችም ሀብቶች አሉ፡፡ ነገር ግን በአግባቡ ጥቅም ላይ ባለመዋላቸው ዛሬም አብዛኞቹ በተለይም ከሰሃራ በታች የሚገኙት አገሮች ሕዝቦች በድህነት ውስጥ የሚኖሩ፣ ኢንቨስትመንትና የሥራ ዕድል የናፈቃቸው ናቸው፡፡

ይህንን በሥራ መቀየር ይቻላል የምትለው ቻይና በአፍሪካ በተለያዩ አገሮች የውስጥ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ሳይኖራት ኢንቨስት በማድረግ ትታወቃለች፡፡ ቪኦኤ በ2022 መግቢያ እንደዘገበውም፣ ቻይና በአፍሪካ ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት ለማድረግ አቅዳለች፡፡

ትልልቅ የቻይና የመንግሥት ኩባንያዎች በኃይልና በትራንስፖርት ዘርፍ በስፋት ተሰማርተዋል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2010 ጀምሮ ሲሶ ያህሉ የአፍሪካ የኃይልና የመሠረተ ልማት ግንባታ የሚገነባውና በገንዘብ የሚደገፈው በቻይና መንግሥት ኩባንያዎች ነው፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2015 ወዲህም በአፍሪካና በሩሲያ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ በእጥፍ ጨምሮ በዓመት 20 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ ሩሲያ በዓመት 14 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ምርቶቿን ወደ አፍሪካ ስትልክ፣ አፍሪካ በበኩሏ አምስት ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ወደ ሩሲያ ትልካለች፡፡

የቻይና በአፍሪካ በስፋት በኢንቨስትመንትና መሠረተ ልማት መሳተፍና የሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከአፍሪካ ድጋፍ ለማግኘት የሄደችበትን መንገድ ደግሞ አሜሪካ ዋና አጀንዳ አድርጋው ከርማለች፡፡

የባይደን አስተዳደር ባለሥልጣናትም ይህንን የአሜሪካ ሥጋት ለማስቀረት ‹‹አፍሪካን በዓለም አቀፍ ውይይቶች ማሳተፍ አስፈላጊ ነው›› የሚለውን ሐሳብ ይዘው መጥተዋል፡፡

የዋይት ሃውስ አማሪካ ጀድ ዴቨርሞንትም በዚህ ወር መግቢያ ‹‹እኛ በርካታ የአፍሪካ ድምፆችን በዓለም አቀፍ ውይይቶች መስማት እንፈልጋለን፡፡ በዓለም የኢኮኖሚ፣ የዴሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የጤናና የደኅንነት ጉዳዮች ላይ ድምፃቸው መሰማት አለበት፤›› ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

በአፍሪካ መሠረተ ልማትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች አብሮ ከመሥራት ባለፈም፣ የአኅጉሪቷ አስፈላጊነት ላይ የአሜሪካ ባለሥልጣናት በተለያዩ ጊዜያት ባደረጉት ንግግር አሳውቀዋል፡፡

ፕሬዚዳት ጆ ባይደን ዛሬ ታኅሣሥ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ያደርጉታል ተብሎ በሚጠበቀው ንግግርም፣ የአፍሪካ ኅብረት በቡድን 20 አባል አገሮች መቀመጫ እንዲኖረው፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ‹‹በምክር ቤቱ ለአፍሪካ ቋሚ መቀመጫ እንዲሰጥ›› የሚለውን ጨምሮ ሪፎርም እንዲያደርግ አፅንኦት ይሰጣሉ ሲሉም ሳልቨን ተናግረዋል፡፡

ባይደንና የአፍሪካ መሪዎች በምግብ ዋስትና እንዲሁም በሩሲያና ዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት በአፍሪካ የምግብ አቅርቦት ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ ላይ ይመክራሉም ተብሏል፡፡

የአፍሪካ መሪዎች አሜሪካ በአኅጉሪቷ በግል ኢንቨስትመንትና ንግድ እንድትሰማራና ባይደን ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገሮችን እንዲጎበኙ ይጠይቃሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በጉባዔው የአፍሪካ ኅብረት 49 አባል አገሮች የተጋበዙ ሲሆን፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ጊኒ፣ ማሊ፣ ሱዳንና ኤርትራ ግን ለጉባዔው አልተጠሩም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...