Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልበትወና ብቃቱ ተወዳጅነትን ያተረፈው ታሪኩ ብርሃኑ ኅልፈት

በትወና ብቃቱ ተወዳጅነትን ያተረፈው ታሪኩ ብርሃኑ ኅልፈት

ቀን:

በወጣትነት ጊዜያቸው ከፍተኛ ዝና ካገኙት እውቅ ተዋንያን መካከል ይመደባል፡፡ በተለይም አስቂኝ የፍቅር ፊልሞችን በመተወን በበርካታቶች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፏል፡፡ ገና በወጣትነት ዕድሜው ከ40 ያላነሱ ፊልሞች ላይ በዋና ገፀ ባህሪነት ተጫውቷል፡፡ መንፈሳዊ ተውኔቶችን በመተወን መጀመሩ የሚነገርለት ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ)፣ ከአንጋፋው አርቲስት ተስፋዬ አበበ ተውኔትን ከተማሩ ልጆች አንዱ መሆኑም ይነገርለታል፡፡

ተዋናዩ የመጀመሪያው ፊልሙ ‹‹ላውንደሪ ቦይ›› ሲሆን ከሳያት ደምሴ ጋር በዋና ገፀ ባህሪነት ተጫውተዋል፡፡ ከዚያ በኋላ በርካታ የፍቅርና አስቂኝ ፈልሞች ላይ በመሥራት፣ ከፍተኛ ተከፋይም ለመሆን በቅቷል፡፡ በኪነ ጥበብ ሙያ ውስጥ በበጎ ሥራም ቀድመው ከሚጠቀሱ ወጣቶች አንዱ ነው፡፡ በፊልሞቹም ጭምር ለትውልድ የሚተርፍ ሥራ በመሥራቱ በሕይወት ባሉ ሰዎች ዓይንና ልብ ውስጥ ቀርቷል፡፡ ተዋናዮችም አብሬው ብሠራ ብለው ከሚመኟቸው ባለሙያዎች አንዱ ነበር።

ታሪኩ ብርሃኑ /ባባ/ ከአባቱ አቶ ብርሃኑ አምባውና ከእናቱ ወ/ሮ አባይነሽ ክብረት በአዲስ አበባ፣ በተክለሃይማኖት ጅምናዚየም ተብሎ በሚጠራው ሠፈር በ1977 ዓ.ም. ተወለደ።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ዕድሜው ለትምህርት እንደደረሰ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በባልቻ አባነፍሶ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአዲስ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማረ፡፡ ከዚያም በኋላ ወደ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በማምራት በሌዘር ቴክኖሎጂ ዲፕሎማውን አግኝቷል።

በትምህርት በነበረበት ወቅት በኢንስቲትዩቱ አስተማሪዎች ተወዳጅ እንደነበረ መምህራንና ባለሙያዎች የሚመሰክሩለት ተማሪ ነበር።

ተዋናይ ታሪኩ የጥበብ ሕይወት ጉዞ የጀመረው በአበቦች የቴአትር ክበብ ሲሆን፣ ጅማሬውን እንዲያብብና ከፍታ ያወጣለት ነው፡፡ በጸሐፌ ተውኔት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) የቴአትርን ሀ..ሁ የቆጠረ ሲሆን ለስኬቱ እንዲረዳውም በተለያዩ ጊዜያት የፊልምና የቴአትር ኮርሶችን ወስዷል።

ታሪኩ በፅርሐ ጽዮን ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ሰንበት ትምህርት ቤት አባል ሆኖ ባገለገለበት ጊዜ ዋዜማ፣ መንገደኛውና የይቅርታ ዘመን የተሰኙ የሙሉ ጊዜ መንፈሳዊ ተውኔቶች ላይም ሠርቷል።

በአበቦች የቴአትር ክበብ በባይተዋር የተጀመረው የቴአትር ሥራው በቀንዲል ቤተ ተውኔት በጥበብ ዝግጅቶች አቅሙን አሳይቷል። ከዚህ በኋላም ወደ ስኬት ጉዞ የወሰደውን የፊልም ሕይወት በዋና ገፀ ባህሪ የተሳተፈበትን ‹‹ላውንደሪ ቦይ›› የተሰኘውን ፊልም አበረከተ።

ባላገሩ፣ ሕይወትና ሣቅ፣ ወንድሜ ያዕቆብ፣ የፍቅር ኤቢሲዲ እና በተለያዩ ፊልሞች ላይ በድንቅ ብቃት በመተወን በወጣቶች ዘንድ እጅግ የሚወደዱ ፊልሞች ላይ መተወኑ በገጸ ታሪኩ ተገልጿል፡፡

ወጣት በ97፣ ላውንድሪ ቦይ፣ ማርትሬዛ፣ ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2፣ ሞኙ የአራዳ ልጅ 4፣ አንድ ሁለት፣ ብር ርር፣ ወደው አይሰርቁ፣ ወፌ ቆመች፣ እንደ ቀልድ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር፣ የሞግዚቷ ልጆች፣ ይዋጣልን፣ ዋሻው፣ ወሬ ነጋሪና ሌሎችም ፊልሞች ላይ ተውኗል።

በሥራዎቹ እየጎላ የመጣው ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) የጥበብ ሕይወቱ በተለያዩ ሽልማቶች የደመቀ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በአዲስ ሚውዚክ አዋርድና በሸገር ኤፍኤም 102.1 የለዛ የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ ሆኖ የተሸለመበትና በጉማ አዋርድ ኢንተርናሽናል የፊልም ፌስቲቫል ለዕጩነትና ለሽልማት የበቃበት የሚጠቀሱ ስኬቶቹ ናቸው።

ከጥበብ ሕይወቱ ባሻገር በተለያዩ ማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ በትህትናውና በለጋስነቱም ይታወቃል፡፡

ተዋናይ ታሪኩ በ2000 ዓ.ም. በ23 ዓመቱ ለኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ሕይወቱ ሲያልፍ የዓይኖቹን ብሌን በሕይወት ኖረው ማየት እክል ላጋጠማቸው ወገኖች መለገሱ ይታወሳል።

ተዋናዩ ባጋጠመው የጤና እክል በተለያዩ ጊዜያት በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ታኅሣሥ 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ሥርዓተ ቀብሩም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በማግስቱ ተፈጽሟል። ተዋናይ ታሪኩ የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር፡፡

በኑዛዜው መሠረት ብሌኖቹን የዓይን ባንክ የተረከበ ሲሆን፣ የባንኩ ተወካይ ሲስተር ሊያ ተካበው ተዋናዩ ዓይኑን መለገሱን የተመለከተ የምስክር ወረቀት ለታላቅ ወንድሙ አሸናፊ ብርሃኑ ሰጥተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ (ክፍል አንድ)

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...