Sunday, January 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሶማሌ ክልል የደጎዲያ ጎሳ  ባህላዊ መሪ የሰላም ሽልማት ተበረከተላቸው

የሶማሌ ክልል የደጎዲያ ጎሳ  ባህላዊ መሪ የሰላም ሽልማት ተበረከተላቸው

ቀን:

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከሚገኙ ጎሳዎች አንዱ የሆነው የደጎዲያ ጎሳ መሪ የሆኑት ዋባር አብዲሌ አብዲ፣ በክልሉ ተከስቶ በነበረው ግጭት ወቅት ሰላምን በማረጋጋት ላደረጉት አስተዋጾ ከቀድሞ ኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡

የደጎደያ ጎሳ መሪ የሆኑት ዋበር አብዲሌ ከዓመት በፊት ወደ ኬንያ ባቀኑበት ወቅት፣ ለሰላም ያደረጉትን አስተዋጽኦ የተረዱት ፕሬዚዳንት ኡሁሩ በቤተ መንግሥት ግብዣ ካቀረቡላቸው በኋላ በአገሪቷ ከፍተኛ ማዕረግ ያለውን የሰላም ሜዳሊያ ሽልማት እንዳበረከቱላቸው ተገልጿል፡፡ 

ዋበር አብዲሌ ከአራት ዓመታት በፊት በክልሉ ተከሰቶ በነበረው ግጭት ወቅት፣ ሶማሌ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን ላይ ምንም ዓይነት በደል እንዳይደርስባቸው ጎሳዎቹን ሲያስጠነቅቁና ሲከላከሉ እንደነበርና ሁሉም ዜጋ ተከባብሮና ተቻችሎ እንዲኖር የጎላ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተጠቅሷል፡፡

በተለይ ደጎደያ ጎሳ የሚገኝበት የኬንያና የቦረና አዋሳኞች አካባቢ የሚገኙ ሁለት ዞኖች ላይ የሚኖሩ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ላይ ምንም ዓይነት ችግር እንዳይደርስባቸው መከላከላቸው ተነግሯል፡፡

በምሥራቅ አፍሪካ ማለትም ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱማሊያ፣ ጂቡቲ ያሉት የደጎድያ ጎሳ አባላት በአንድ መሪ እንደሚመሩ የተገለጸ ሲሆን፣ ከሌሎች ጎሳዎች ደግሞ የተለየ እንደሚያደርገው ይነገራል፡፡ የደጎድያ ጎሳ መሪ ዋባር የሚል መጣሪያ ሲኖረው ሥረዓቱ የራሱ ፓርላማ ያለውና 120 አባላት እንዳሉት ተነግሯል፡፡

በውስጡም 14 የሥራ አስፈጻሚ ሸንጎዎችና አፈ ጉባዔን አካቶ ሥርዓቱን እንደሚያካሄድ ተገልጿል፡፡ ፓርላማው በተወሰነለት ጊዜ የሚሰበሰብ ሳይሆን በጎሳው ውስጥ ችግር በተፈጠረበት ወቅት ጥሪ ቀርቦ ተሰብስቦ መፍትሄው ላይ እንደሚመክር የጅግጅጋ የአገር ሽማግሌ የሆኑት አቶ ሙስጠፋ ሐጂ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በዚህም መሠረት ሥርዓቱ፣ የጎሳ ግጭት፣ ጦርነት እንዲሁም ረሃብ ሲገጥም ስብሰባ ጠርቶ መፍትሄ ላይ እንደሚመከር አቶ ሙስጠፋ ያብራራሉ፡፡

የዋባር (የጎሳ መሪው) ውሳኔ የሚከወነው 14ቱ የሥራ አስፈጻሚ አባላት ተመካክረውና ተወያይተው ከውሳኔ ሲደርሱ ብቻ እንደሆነ አቶ ሙስጠፋ ያክላሉ፡፡ የደጎድያ ጎሳ ያልሆኑ ከክልሉ ጋር የሚዋሰኑ የኦሮሞ ጎሳዎች፣ ቦረና፣ ጉጂና አርሲ ጋር ግጭቶች ሲከሰቱ በዚህ ሥርዓት ሲፈቱ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በሱማሌ ክልል ከ30 በላይ ጎሳዎች እንዳሉ የሚነገር ሲሆን፣ በደጎዲያ ጎሳ ውስጥ ሊበን ዞን፣ አፈዴር፣ ፋፈን፣ ሄረር፣ ሽበሌ እንዲሁም ዳዋ ዞኖች ይገኛሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...