Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ አሥር በመቶ በእሳት መቃጠሉ ተነገረ

የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ አሥር በመቶ በእሳት መቃጠሉ ተነገረ

ቀን:

  • በፓርኩ ውስጥ 18,216 ሔክታር መሬት በሕገወጥ መንገድ ታርሷል

በኢዮብ ትኩዬ

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ አሥር በመቶ የሚሆነው ደን መቃጠሉንና ለእርሻ በሚል ሰበብ መመንጠሩን የፓርኩ ኃላፊዎች አስታወቁ፡፡

ከአምስት እስከ አሥር በመቶ የሚሆነው የፓርኩ ደን በእሳት መቃጠሉን፣ የፓርኩ ዋና ኃላፊ አቶ አስቻለው አዱኛ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ በፓርኩ የሚገኙት እንስሳት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ ነው ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ኃላፊው እስካሁን ምን ያህል ሔክታር ደን እንደተቃጠለ ማወቅ እንዳልተቻለ፣ ኢትዮጵያ በገጠመማት የፀጥታ ችግር የፓርኩ ደንና ንብረት ውድመት እንደገጠመው አስረድተዋል፡፡

የአካባቢው አርሶ አደሮች በፓርኩ ውስጥ ከ13 ሺሕ እስከ 18,216 ወይም ከስድስት እስከ 8.36 በመቶ የሚሆነውን መሬት፣ በሕገወጥ መንገድ እንዳረሱት በጥናት መረጋገጡን አስቻለው አክለው ገልጸዋል፡፡

በፓርኩ ከነበሩ አራት ተሽከርካሪዎች መካከል በፀጥታው ምክንያት ሁለቱ ተዘርፈው ያሉበት እንደማይታወቅ፣ አንዱ ከጥቅም ውጪ እንደሆነና ሌላው ደግሞ በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ሥር ውሎ ጉዳዩ በሕግ እየታየ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር በፓርኩ ውስጥ የነበሩ ሦስት ካምፖች መፈራረሳቸውን፣ የቢሮ ዕቃዎችን ጨምሮ በርካታ ንብረቶች መውደማቸው ፈታኝ ሆኗል ተብሏል፡፡

የፓርኩ ጥበቃ ሠራተኞች በበኩላቸው ከጥቅምት 18 እስከ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ከ800 ሔክታር በላይ የሚገመት የፓርኩ ደን መቃጠሉን ጠቁመዋል፡፡ ፓርኩ የመቃጠልና የመመንጠር አደጋ የገጠመው፣ የጥበቃ ሠራተኞች በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ምክንያት በመበታተናቸው ነው ብለዋል፡፡

ከ60 በላይ የጥበቃ ሠራተኞች አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር፣ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ በመበተናቸው ፓርኩ አደጋ እንደተጋረጠበት በቦታው ያሉ የጥበቃ ሠራተኞች ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ነበር፡፡

ከሪፖርተር ጋር ቆይታ ያደረጉት የፓርኩ ዋና ኃላፊ በበኩላቸው፣ የጥበቃ ሠራኞች ከዚህ በፊት በፓርኩ በተከሰተ የፀጥታ ችግር በመበተናቸው የጥበቃ አገልግሎት እየሰጡ ያሉት 12 ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በወቅቱ በነበረው ችግር የፓርኩ መደበኛ የጥበቃ አገልግሎት ተስተጓጉሎ ቢቆይም፣ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ባለሥልጣን በፓርኩ ላይ የተጋረጠውን ችግር ለመቅረፍ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተጠቁሟል፡፡ በመሆኑም ባሉት ሠራተኞችና የፀጥታ አካላት መደበኛ ሥራዎች ስለመጀመራቸውና ተጨማሪ የጥበቃ ሠራተኛ ለመቅጠር በሒደት ላይ መሆናቸውን ነው ኃላፊው የጠቆሙት፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት የጥበቃ ሥራው በመስተጓጎሉ ምክንያት በፓርኩ ውስጥ ከሚገኙ እንስሳት መካከል፣ በተለይም ዝሆኖች ፓርኩን ጥሰው በመውጣት በአካባቢው ያለውን የአርሶ አደር ሰብል እስከማውደም የደረሱበት አጋጣሚ እንደነበርም ተገልጿል፡፡

አቶ ምሕረት አምሳሉ በፓርኩ ዙሪያ የማሽላ ማሳ የነበራቸው አርሶ አደር ሲሆኑ፣ በፓርኩ የሚኖሩ ዝሆኖች የአርሶ አደሮችን ማሽላ ስላወደሙባቸው፣ የማሽላ ጥበቃ ሠራተኞችን ቀጥረው ለወጪ ሲዳረጉ መክረማቸውን ተናግረዋል፡፡ በፓርኩ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮችም ሰብሉን ከመሰብሰባቸው በፊት፣ በሺዎች ሔክታር የሚገመት ማሽላ እንደወደመባቸው ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም በቀጣዩ የእርሻ ወቅትም ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት የሚመለከተው አካል የፓርኩን ችግር እንዲፈታ አርሶ አደሩ ጠይቀዋል፡፡ የፓርኩ ኃላፊ ጉዳዩን በተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡ፣ ዝሆኖቹ ከፓርኩ ውጪ ባሉ ማሳዎች ላይ ጉዳት ያደረሱበት አጋጣሚ አለ ብለዋል፡፡ በብዛት ግን አርሶ አደሮች በሕገወጥ መንገድ ፓርኩን መንጥረው በዘሩት ሰብል ላይ ነው ጉዳት የደረሰው ብለዋል፡፡

በ1999 ዓ.ም. የተቋቋመው የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ 2,176.4 ካሬ ኪሎ ሜትር (217,643 ሔክታር) የቆዳ ስፋት ሲኖረው፣ 200 የአዕዋፋት፣ ዘጠኝ ተሳቢ እንስሳት፣ ከ40 በላይ ሌሎች እንስሳት፣ እንዲሁም 53 ያህል የዛፍ ዝርያዎች እንደሚገኙበት ይነገራል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...