ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ ታህሣሥ 8 ቀን 2015 ዓም በሚሊኒየም አዳራሽ ያካሄደው ደቡብ ግሎባል ባንክ፣ ስያሜውን ወደ “ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ” መቀየሩን አስታወቀ።
የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ባንኩ ከዚህ በኋላ በአዲስ ስያሜና አርማ እንደሚቀጥል ያቀረበውን ሀሳብ የባንኩ ጠቅላላ ጉባኤ አጽድቆታል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ስያሜ የሚቀጥለው የቀድሞ ደቡብ ግሎባል ባንክ በ2014 ሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 370 ሚሊዮን ብር ማትረፉም ተገልጿል። ይኸም ካለፈው ተመሳሳይ የሒሳብ ዓመት ጋር ሲነፃጸር 41 በመቶ ወይም የ108.4 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ተነግሯል። ባንኩ ተቀማጭ ሒሳቡን ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ ማድረሱንና ፣ በ2014 ሒሳብ ዓመትም 2.3 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል።