Tuesday, April 16, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የሎጂስቲክስ መሪ ዕቅድ ሲገባደድ የአገሪቱ ወጪና ገቢ ዝውውር ከጅቡቲ ወደብ በ46 በመቶ እንደሚያንስ ተጠቆመ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኢትዮጵያ ያዘጋጀችው አዲሱ የ30 ዓመታት የሎጂስቲክስ መሪ ዕቅድ ሲገባደድ፣ አገሪቱ ለውጪና ለገቢ ዝውውር በዋነኝነት የምትጠቀምበት ወደብ የማስተናገድ መጠን በ46 በመቶ እንደሚያንስ ተጠቆመ፡፡

በአማራጭም የአምስት ጎረቤት አገሮች ወደቦችን በስፋት የመጠቀም ዕቅድ እንዳለና፣ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ ከተጠቀመችበት ከ23 ዓመታት በላይ የሆነውን የአሰብ ወደብም አንደኛው እንደሆነም ዝርዝር ዕቅዱ ያሳያል፡፡

የትራንስፖር ሎጂስቲክስ ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ባለፈው ሰኞ ኅዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ዕቅዱን አጋርተውት ነበር፡፡ ‹‹ይህ ዕቅድ የወደብ በሮችን አማራጭ ማስፋት፣ አዳዲስ ደረቅ ወደቦችን ግንባታ ማከናወን፣ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ማሳደግና የተለያዩ የትራንስፖርት አማራጮችን የማሳለጥ አስፈላጊነትን ይመክራል፤›› ሲሉ አብራርተዋል፡፡   

በሚኒስቴሩ ተዘጋጅተው ይፋ ከሆኑት የኢትዮጵያ ትራንስፖርት መሪ ዕቅዶች (Ethiopian Transport Master Plans) ውስጥ አንደኛው የሆነው የሎጂስቲክስ ዘርፉ መሪ ዕቅድ፣ በርካታ ውጥኖችን ያሳያል፡፡ ከእነዚህም መካከል አሁን በዝቅተኛ አቅም የምትጠቀምበትን የሱዳን ወደብ፣ የሶማሌላንድ በርበራ ወደብና የኬንያ ላሙ ወደብን በስፋት አጠናክሮ መቀጠል ሲሆን፣ አሰብ ወደብንም መጠቀም እንደሚጀመር ተጠቁሟል፡፡

በዕቅዱ ሰነድ ላይ እንደሠፈረው፣ እ.ኤ.አ. በ2020 ኢትዮጵያ የጂቡቲ ወደብን 92 በመቶ ለሚሆነው ወጪና ገቢዋ የምትጠቀምበት ሲሆን፣ የሱዳን ወደብን አራት በመቶ፣ የበርበራ ወደብን ሦስት በመቶና ላሙ ወደብን ደግሞ አንድ በመቶ እንደምትጠቀም ተጠቅሷል፡፡

ከ30 ዓመት በኋላም የጂቡቲ ወደብን አጠቃቀም ወደ 50 በመቶ ዝቅ በማድረግ የሱዳንና ላሙ ወደብ እያንዳንዳቸው ወደ 10 በመቶ፣ እንዲሁም የበርበራና አሰብ ወደብን ደግም እያንዳንዳቸው 15 በመቶ መጠቀም ወደሚቻልበት ሁኔታ እንደሚሄድ ይጠቁማል፡፡

የአገሪቱን ገቢና ወጪ ከሚያስተናግዱት ስምንት ደረቅ ወደቦች ትልቁ የሆነውና ወደ ኢትዮጵያ ከሚገባው ምርት ሦስት አራተኛውን የሚያስተናግደው የሞጆ ደረቅ ወደብ ነው፡፡ አምስቱ የጎረቤት አገሮች ወደቦች ከዚህ ደረቅ ወደብ ባላቸው ርቀት የጂቡቲው ወደብ ዝቅተኛ ርቀት ያለው ሲሆን፣ ርቀቱም 822 ኪሎ ሜትር ነው፡፡፡ ረዥም ርቀት ያለው ደግም የሱዳን ወደብ ሲሆን እሱም ከሞጆ ደረቅ ወደብ ያለው ርቀት 1,830 ኪሎ ሜትር ነው፡፡  

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባወጣው ዕቅድ ላይ እንዳሠፈረው፣ የሎጂስቲክስ ዘርፉ ኢንቨስትመንት ወደቡን ማሳደግ በሚመለከት፣ እ.ኤ.አ. በ2025 የመንግሥት የአዳዲስ ደረቅ ወደቦች ግንባታ ወጪ 13.5 ሚሊዮን ዶላር እንደሚሆን ወጥኗል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2035 ደግሞ 9.6 ሚሊዮን ዶላር እንደሚሆንና ከ30 ዓመታት በኋላም 133 ሚሊዮን ዶላር እንደሚሆን ታቅዶ ሠፍሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች