Sunday, May 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየታሪካዊው የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ

የታሪካዊው የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ

ቀን:

የኳታር ዓለም ዋንጫ ከጅማሬው አንስቶ በድራማዊና አስገራሚ ክስተቶች ታጅቦ በ64 ጨዋታዎች፣ 172 ጎሎች ተቆጥረውበት ታሪካዊውን የፍፃሜ ጨዋታን አስመልክቶ ተጠናቋል፡፡ አርጀንቲና ፈረንሣይን በፍፁም ቅጣት ምት 4 ለ 2 በመርታት፣ የዓለም ዋንጫን ለሦስተኛ ጊዜ በማንሳት አዲስ ታሪክ መጻፍ ችላለች፡፡

የዓለም ሕዝብ ትኩረት ሆኖ የሰንበተው የዘንድሮ ዓለም ዋንጫ የምድብ፣ የጥሎ ማለፍ፣ ሩብ ፍፃሜ፣ ግማሽ ፍፃሜ እንዲሁም የፍፃሜ ጨዋታዎች በሙሉ በድራማዊ ክስተቶች የታጀቡ ነበሩ፡፡

በጨዋታዎች ላይ ከተስተዋሉት ትዕይንቶች ባሻገር በዓለም ዋንጫ አዲስ የተጻፉ ታሪኮችም ነበሩት፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ባልተለመደ ወቅት ላይ፣ እግር ኳስ እምብዛም በሆነበት በመካከለኛው ምሥራቅ የተሰናዳው ዓለም ዋንጫ መላው የዓለም ሕዝብ እንዳስደመመ ተጠናቋል፡፡ የምንጊዜም ምርጥ የዓለም ዋንጫ ያሰናዳችው ኳታር፣ እንግዶቿን ስታሰናብት ቅር ቢላትም፣ በታሪክ የማይረሳ አሻራን ማኖሯ አኩርቷታል፡፡

- Advertisement -

የኳታር ከተሞች በቅርብ ርቀት ላይ መኖራቸውን ተከትሎ፣ ዓለም ዋንጫውን ለመመልከት ከተለያዩ አገሮች የሚመጡ ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም አይኖራትም በሚል ስትተች የነበረው ኳታር፣ የከተሞቿን የትራንስፖርት ምቹና ዘመናዊ በማድረግ ተመልካች ሳታጉላላ ማስተናገድ ችላለች፡፡

ከሦስት ሚሊዮን ሕዝብ በታች ያላት ኳታር ዓለም ዋንጫውን በብቃት በመወጣት ዓለም ዋንጫ ለቀጣዮቹ አዘጋጆች የቤት ሥራ ሰጥታ አልፋለች፡፡ ዓለምም ፍፁማዊነት የታየበት የምንጊዜም ምርጥ ዓለም ዋንጫ ነው ሲሉ መስክረዋል፡፡ ኳታር ካደረገችው መስተንግዶ በዘለለ የሜሲ ስም ደምቆ መነሳቱ ሌላው ውበት የዓለም ዋንጫ ድምቀት አድርጎታል፡፡ በእግር ኳስ የሰው ልጅ ሊያሳካው የሚችለውን ሽልማት ሁሉ ሰብስቦ፣ የዓለም ዋንጫ ብቻ ቀርቶት የነበረው ሊዮኔል ሜሲ፣ በመጨረሻው ዓለም ዋንጫ ተሳትፎ እንዲያሳካለት የሁሉም ምኞት ነበር፡፡  አርጀንቲና በሳዑዲ ዓረቢያ ስትረታ በአጭር መቅረቷ ቢያስመስለውም በአንፃሩ ለረዥም ስኬቷ የጉዞዋ ስንቅ ነበር የሆነላት፡፡ ሳዑዲ ዓረቢያ አርጀንቲናን በረታችበት ወቅት፣ ደጋፊዎች ‹‹ሜሲ የት አለ?›› የሚል ማሽሟጠጫ ቢሰነዘርም ሜሲም መዳረሻውን የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮና ሆኖ አስመልክቷል፡፡

የ35 ዓመቱ ሜሲ በዓለም ዋንጫው ሰባት ጎል በማስቆጠር፣ ሦስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት ተጎናጽፏል፡፡ የኳታር አሚር ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ ለአርጀንቲናው አምበል በወርቅ ባጌጠ ካባ ወይም ሺታ የዓለም ዋንጫውን አሳልፈው ለዘመኑ ድንቅ ተጫዋች ሜሲ ካስረከበ በኋላ አዲስ ታሪክ መጻፍ ጀመረ፡፡ የአርጀንቲና የዓለም ዋንጫን ማንሳት መላውን ዓለም ጮቤ ያስረገጠ ነበር፡፡

አርጀንቲናውያን በማዕክላዊ ቦነስ አይረስ መታሰቢያ መትመም የጀመሩት ሰኞ ሌሊት ለማክሰኞ አጥቢያ ነበር፡፡ ከተማዋ ከዳር እስከ ዳር በሰው ተጥልቅልቃ ጀግኖችዋን ስትጠባበቅ አምሽታ በክብር ተቀብላለች፡፡ አርጀንቲና የ1986 ዓለም ዋንጫን ስታነሳ ከነበረው ድባብ በላይ ይሔኛው የበለጠ ደማቅ እንደሆነ ሁለቱም ድል መመልከት የቻሉ ተመልካቾች አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

ምንም እንኳን የአርጀንቲና የዓለም ዋንጫው ሻምፒዮን መሆን ብትችልም፣ ፈርንሣይም በኳታር ስኬታማ ጊዜን ማሳለፍ ችላለች፡፡ የ2018 የሩሲያ ዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ፈረንሣይ በፍፃሜው ጨዋታ እስከ 80 ደቂቃ ላይ ካንቀላፋችበት ነቅታ በ97 ደቂቃ ሁለት ግቦች በኬሊያን ማፔ አማካይነት ስታስቆጥር ጨዋታው አዲስ መንፈስ ዘራበት፡፡

ማፔም በዓለም ዋንጫ ታሪክ ከ1966 በኋላ ሀትሪክ መሥራት የቻለ ሁለተኛው ተጫዋች በመሆን ሌላ አዲስ ታሪክ የሠፈረበት አጋጣሚ ሆነ፡፡ ማፔ በዓለም ዋንጫው ስምንት ጎሎችን በማስቆጠር የወርቅ ጫማውን ከመውሰዱም በላይ በግሉ በርካታ ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ተጫዋች መሆን የቻለበት ነበር፡፡ ሜዳው ውስጥ የለም እስኪባል ድረስ ደብዛው የጠፋው ማፔ ከ97ኛው ደቂቃዎች በኋላ የጨዋታው ድባብ መቀየር ያስቻለ የማይረሳ ትዕይንት ነበር፡፡

የፈረንሣይ ብሔራዊ ቡድን ወደ አገሩ ሲመለስ፣ የጀግና አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ ሦስተኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቅ የቻለችው ክሮሽያና ለመጀመሪያ ጊዜ ግማሽ ፍፃሜ መድረስ የቻለችው ሞሮኮ፣ ተመሳሳይ የጀግና አቀባበል ከተደረገላቸው ብሔራዊ ቡድኖች ውስጥ ናቸው፡፡

ኳታር ዓለም ዋንጫ እውነታዎች

በዓለም ዋንጫው 3.4 ሚሊዮን ተመልካች ስታዲየም ገብቶ መመልከት ችሏል፡፡ ከስታዲየም ውጪ በሚገኙ ፊፋ ባሰናዳቸው ስክሪኖች ያሉባቸው ሥፍራዎች 1.8 ተመልካቾች መታደም ችለዋል፡፡ ከ150 የተለያዩ አገሮች የተወጣጡ 200 ሺሕ በጎፈ ቃደኞች በዓለም ዋንጫው ተሳትፈዋል፡፡ አፍሪካ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለመግባት 88 ዓመት በላይ ከቆየች በኋላ ዘንድሮ በሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ማሳካት የቻለችበት አጋጣሚ ነበር፡፡

የአርጀንቲናው አሠልጣኝ ሊዮ ኒልስ ካሎኒ በ44 ዓመቱ ዓለም ዋንጫን በማንሳት በ39 ዓመት ዕድሜው በ1978 የዓለም ዋንጫን ማንሳት ከቻለው የአገሩ ልጅ ሰዛርሲዊስ ቀጥሎ ሁለተኛው ወጣት አሠልጣኝ ሆኗል፡፡

የፈረንሣዩ ኦሊቨር ጅሩድ አራት ጎሎችን በማስቆጠር የቴየ ሬሄነሬ 51 ጎል፣ በሁለት በመላቅ 53 ጎል በማስቆጠር የፈረንሣይ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችሏል፡፡ ፊፋ ለብሔራዊ ቡድን ቅድመ ዝግጅት እንዲሁም ከውድድር በኋላ ለተካፋይ ብሔራዊ ቡድኖች ከ440 ሚሊዮን ዶላር ወጪ አውጥቷል፡፡ ይህም 40 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ክፍያዎች ብልጫ አሳይቷል፡፡

የዓለም ዋንጫውን ያነሳችው አርጀንቲና 42 ሚሊዮን ዶላር፣ ፈረንሣይ 30 ሚሊዮን ዶላር፣ ክሮሽያ 27 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ሞሮኮ 25 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ተብርክቶላቸዋል፡፡

የዘንድሮ ዓለም ዋንጫ አርጀንቲና፣ ሜሲና ማፔ የጥንቶቹን ፔሌና ማራዶናን የታወሱበት አጋጣሚም ነበር፡፡

ይህም ‹‹በሸዋ ላይ ደሴታቹን በአርጀንቲና ናና ማራዶና›› እየተባለ ሲዘፈን የነበረውን ግጥም በርካቶችን እንዲያስታውሱ አስችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...