Sunday, May 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ከመቼውም ምርጡና ልዩ የተባለው የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ

ትኩስ ፅሁፎች

አርጀንቲናን ከሠላሳ ስድስት ዓመታት በኋላ ባለድል ያደረጋት የዘንድሮው 22ኛው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ፣ ጉዞው ባስደናቂና ባስገራሚ መልኩ የተጠናቀቀ ነበር፡፡ አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ከአኅጉሯ የመጀመርያዋ አራቱ ውስጥ የገባችበት፣ ለአፍሪካም ብሩህ ተስፋን እንድትሰንቅ ያደረገችበት ሆኖ አልፏል፡፡ አርጀንቲና ለሦስተኛ ጊዜ ዋንጫውን ያነሳችው፣ ከአራት ዓመት በፊት የተካሄደውን ውድድርን ጨምሮ ለሁለት ጊዜ ዋንጫውን ካሸነፈችው ፈረንሳይ ጋር 120 ደቂቃውን 3ለ3 ከተለያየች በኋላ፣ በፍጹም ቅጣት ምት 4ለ2 በመርታት ነው፡፡ ሁለት ያገባው ኮከቡ ሊዮኔል ሜሲ እና ሦስት አስቆጥሮ ሃትሪክ የሠራው ኮከቡ ክሊያን ምባፔ የውድድሩ ድምቀት ነበሩ፡፡ ጌቲ ኢሜጅ ከሃምሳ በላይ የፎቶ ባለሙያዎቹን በውድድሩ ሥፍራ በኳታር አሰማርቶ ምርጥ ብሎ ካጋራቸው መካከል ቢቢሲ በድረ ገጹ ያወጣቸው በከፊል እዚህ ላይ ቀርበዋል፡፡

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች