Tuesday, March 5, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየጮቄ ተራራ ‘ምርጥ የቱሪዝም መንደር’ ሆኖ በዓለም አቀፉ ተቋም ተመረጠ

የጮቄ ተራራ ‘ምርጥ የቱሪዝም መንደር’ ሆኖ በዓለም አቀፉ ተቋም ተመረጠ

ቀን:

ሞሮኮ ሁለት መንደሮችን አስመርጣለች

በምሥራቅ ጎጃም የሚገኘውን የጮቄ ተራራና አካባቢውን የዓለም የቱሪዝም ድርጅት፣ ከዓለም ‹‹ምርጥ የቱሪዝም መንደሮች›› አንዱ አድርጎ መርጦታል።

የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ትናንትና (ታኅሣሥ 11 ቀን 2015 ዓ.ም.) በስፔን ማድሪድ ባወጣው መግለጫ፣ የጮቄ ተራራ ኢኮቪሌጅን ጨምሮ ከአምስቱ አኅጉሮች ከ18 አገሮች በድምሩ 32 መንደሮች የ2022 ‹‹ምርጥ የቱሪዝም መንደር››ነት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ለ2022 ውድድር ከ57 አባል አገሮች በአጠቃላይ 136 መንደሮች (እያንዳንዱ አባል አገር ቢበዛ ሦስት መንደሮችን ማቅረብ ይችላል) ቀርበዋል። ኢትዮጵያ ያቀረበችው አንድ መንደር  ያም የጮቄ ተራራ ብቻ ነው፡፡

ከአፍሪካ ከኢትዮጵያ ሌላ ፣ ሞሮኮ ሁለት መንደሮችን አስመርጣለች፡፡ ዓለም አቀፉ የቱሪዝም ድርጅት በሌላ ምድብ መንደሮችን ለማሳደግ ከተለያዩ አገሮች ከተመረጡት 20 መንደሮች ውስጥ የኢትዮጵያ አዳባ፣ የኬንያ፣ የሞሪሸስና የኬፕ ቨርዴ ይገኙበታል፡፡

ምርጥ የቱሪዝም መንደሮችን የመምረጥ ተነሳሽነት፣ የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት የተለመው የገጠር መንደሮችን ከነመልክዓ ምድራቸው፣ እንዲሁም የኅብረተሰቡን ተፈጥሯዊና ባህላዊ ብዝኃነታቸው ማኅበራዊ እሴቶቻቸውን የአካባቢያቸውን የምግብ ባህል ጨምሮ ከመጠበቅና ከማክበር አንፃር የቱሪዝምን ሚናን ለማጉላት ነው፡፡

መንደሮቹ በገለልተኛ የአማካሪ ቦርድ በዘጠኝ መሥፈርያ የተመዘኑባቸው ዘርፎች ባህላዊና ተፈጥሯዊ ሀብት፣ ባህላዊ ሀብት እንክብካቤና ማስተዋወቅ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ አካባቢያዊ ዘላቂነት፣ የቱሪዝም ዕምቅ ይዞታና ልማት የእሴት ትስስር፣ አስተዳደርና ለቱሪዝም ቅድሚያ መስጠት፣ መሠረተ ልማትና ቁርኝቱና ጤና፣ ምቹነትና ደኅንነትን ያካተቱ ናቸው፡፡

ምርጥ የቱሪዝም መንደሮች ተነሳሽነት (Best Tourism Villages initiative) ቱሪዝምን እንደ አንድ መዘውር ለዕድገትና ብልፅግና በመጠቀም ለተጉ ጠንካራ መንደሮች ዕውቅና የሚሰጥበት ነው፡፡

የምርጥ የቱሪዝም መንደሮች ምርጫውን በደስታ የተቀበሉት የዓለም የቱሪዝም ድርጅት ዋና ጸሐፊ ዙራብ ፖሎሊካሽቪሊ፣ ‹‹በሁሉም ቦታዎች ለሚገኙ የገጠር ማኅበረሰቦች፣ ቱሪዝም ሥራ በመስጠት፣ የሀገር ውስጥ ንግዶችን በመደገፍ እና ወግና ልምዶችን በመጠበቅ ረገድ እውነተኛ  ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። በዓለም ቱሪዝም ድርጅት ምርጥ የቱሪዝም መንደሮች የኢኮኖሚ ብዝኃነትን ለማራመድና  ከትላልቅ ከተሞች ውጭ ላሉ ወገኖች ሁሉ ዕድሎችን ለመፍጠር ያለውን የዘርፉን ኃይልነት የሚያሳይ ነው፤›› ብለዋል፡፡

32ቱ መንደሮች ‹‹ምርጥ የቱሪዝም መንደሮች በተባበሩት መንግሥታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት›› (Best Tourism Villages by UNWTO) የሚል መለያ የያዘ ሽልማት የሚቀበሉት የካቲት 20 እና 21 ቀን 2015 ዓ.ም. በሳውዲ ዓረቢያ አሉልኣ ከተማ መሆኑ ታውቋል፡፡

መረጃዎች እንደሚሳዩት፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የጮቄ ሰንሰለታማ ተራራ፣ ከባህር ወለል በላይ 4100 ከፍታ ያለውና ሰባት ሺሕ ሔክታር ቦታን እንደሚሸፍን፣ ከ270 በላይ ምንጮችና ከ50 በላይ ለሚሆኑ ወንዞች ደግሞ መፍለቂያ በመሆኑ በምሥራቅ አፍሪካ ታላቁ የውኃ ማማ በመባል ይታወቃል፡፡

ከጮቄ ተራራ ከሚፈልቁት 54 ወንዞች አብዛኛዎቹ የዓባይ ወንዝ ገባር ወንዞች ናቸው፡፡ እንዲሁም ጮቄ ተራራ የበርካታ አገር በቀል ዛፎችና ለመድኃኒትነት የሚያገለግሉ ዕፀዋት መብቀያ፣ የብዝኃ ሕይወት ማዕከል መሆኑን የዕፀዋት ምሁራን ይናገሩለታል፡፡

የዓለም የቱሪዝም ድርጅት ዓምና ባካሄደው ተመሳሳይ ምርጫ በምዕራብ ሸዋ የሚገኘውን ወንጪ ሐይቅና አካባቢውን ከዓለም ‹‹ምርጥ የቱሪዝም መንደሮች›› አንዱ አድርጎ መምረጡ ይታወሳል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...