Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲን  በፓስተር ዮናታን አክሊሉና በነቢይ ኢዩ ጩፋ ላይ የወንጀል ምርመራ...

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲን  በፓስተር ዮናታን አክሊሉና በነቢይ ኢዩ ጩፋ ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲደረግ  ለፌደራል ፖሊስ አቤቱታ አቀረበች

ቀን:

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ ያነጣጠረ፣ አደገኛ የሆነና የሃይማኖትን ክብር የሚነካ፣ የአምልኮ ሥርዓትና እምነትን የሚያንቋሽሽ፣ ዘለፋና ሓሰተኛ ንግግር፣ ለሁከትና ብጥብጥ መነሻ የሚሆን ድርጊት ፈጽመውብኛል ባለቻቸው ፓስተር ዮናታን አክሊሉ፣የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተ ክርስቲያን እና ነቢይ እዩ ጩፋ፣ ክራይስት አርሚ ኢነተርናሽናለ ቤተ ክርስቲያን ላይ የወንጀል መርመራ አጣርቶ ለሚመለከተው አካል እንዲያቀርብ ለፌደራል ፖሊስ አቤቱታ አቀረበች፡

የቤተ ክርስቲያኗ ሕግ አገልግሎት መምሪያ  ለፌደራል ፖሊስ በፃፈው አቤቱታ እንደገለጸው፣ ፓስተር ዮናታን የአዲስ ኪዳን ካህናት በተ ክርስቲያን መስራች ሲሆን፣ በዘሁ ቤተ እምነት ውሰጥ ኅዳር 22 እና ኅሣሥ 4 ቀን 2015 ዓ.ም ማርሴል ቲቪ ወርልድ ዋይድ (MARCEL TV WORLEDWIDE) በተሰኘው ሃይማኖታዊ ፕሮግራም ማሰራጭያ ሚዲያ፣ ባለቤትነቱና አምልኮ መፈጸሚያነቱ የኢተዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በተክርስቲያን የሆነንና ተአምረ ማርያም የተሰኘ የእምነት መጽሐፍ በመየዝ፣ ቤተክርስቲያኒቱ የማታምንባቸውን የተሳሳቱ ዶግማዊ አስተምህሮቶችን “ማርያምን ማምለክ፣ ገብርኤልን ማምለክ፣ መርቆሬዎስን ማምለክ ጣዖት አምላኪነት ነው” በማለት ሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር አስተላልፏል፡፡ በተጨማሪም ገድለ ተክለሃይማኖትና ገድለ ዘርዐ ብሩክ የሚባሉ የከበሩ ቅዱሳን መጽሐትን በመያዝና የገድላቱን ይዘት በማንኳሰስና“አገሪቱን የማትወጣው ድንቁርና ውስጥ የከተታት እንዲህ ዓይነቱ ጣዖት አምላኪነት ነው ” በማለት ተደራራቢ ወንጀል መፈጸሙን በአቤቱታው ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡የእምነት ተቋሙም ማለትም የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያንም ሕዝብን በመሰብሰብና በማመቻቸት የወንጀሉ ድርጊት እንዲፈጸም በማድረግ በወንጀሉ ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆኑንም በማመልከቸው ጠቁሟል፡፡

ሌላው የወንጀል ምርመራ እንዲጣራበት የተጠየቀው የክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን መስራች ነው በተባለው ነቢይ ኢዩ ጩፋ ላይ ሲሆን፣ግለሰቡ በዚሁ በተ እምነት ውስጥ ባለፈው ዓመት ነሀሴ 9 ቀን 2014 ዓ.ም ሕዝብ በተሰበሰበበት መድረክ ላይ፣ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የምታከብረውንና የምትከበርበትን የእግዚአብሔር ታቦት ከቁምሳጥን ጋር በማነጻጸር፣ የአሁኑ ታቦት በአራቱም አቅጣጫ መንገድ የሚዘጋ ነው ለእኛ ምን  ያደርግልናል በማለት፣ የአምልኮ ስርዓትንና የሃየማኖት ክብርን የመንካት ወንጀል መፈጸሙን በአቤቱታው አብራርቷል፡፡የእምነት ተቋሙ ተባባሪና ቀጥተኛ የወንጀሉ ተሳታፊ መሆኑን አክሏል፡፡

ግለሰቦቹ የግላቸውን የተዛባ አመለካከትና ሃየማኖታዊ አስተምህሮን ተገን በማድረግ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ በተክርስቲያን ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ ንግግርን በመሰንዘር፣ የቤተክርስቲያኗ አስተምህሮ ያልሆነውን አስተምህሮዋ በማስመሰል፣የተሳሳተ መረጃ ለሕዝቡ በማድረስ፣ በዜጎች መካከል የሃይማኖት ግጭት እንዲፈጠር ሆን ብለው በመስራት ላይ መሆናቸውንም መምሪያው በአቤቱታው አብራርቷል፡፡ በሕገመንግስቱ ተደንግጎ የሚገኘውን የእምነትና የሃይማኖት ነጻነትን በመጣስ በተለያዩ ሚዲያዎች በማሰራጨትና ተንኳሽ ድርጊቶችን በመፈጸም፣ የእምነቱ ተከታይ የሆኑትን ምዕመናንን ትዕግስት በሚፈታተንና ሕዝብን ላልተፈለገ ሁከት በሚያነሳሳ መልኩ የወንጀል ድርጊቱን ቀጥለውበት እንደሚገኙም አስታውቋል፡፡

ግለሰቦቹ በተደጋጋሚ ሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር በቀጥታ ከመናገር በተጨማሪ ከ5000 በላይ ተከታዮች ባሏቸው በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች በማሰራጨት፣ በመቶ ሲዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲታይና እነዲከታተሉት ማድርጋቸውን ጠቁሞ፣ ግለሰቦቹና ተቋማቱ በእግዚዘብሄር የሚያምነውን ምእመናን በሃይማኖቱ የሌለውን አስተምህሮ ጣዖት አምላኪ በማስመሰል፣ በመላው አገሪቱ ሕዝብ መካከል ሁከትና ብጥብጥ የሚፈጥር የጥላቻ ንግግር ማስራጨታቸውንም መምሪያው በአቤቱታው ዘርዝሮ አቅርቧል፡፡

የቤተ ክርስቲያኗ ሕግ መምሪያ ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ  ባቀረበው አቤቱታ በግለሰቦቹና ተቋማቱ ላይ ተገቢውን ምርመራ በማድረግና የወንጀል ምርመራ መዛግብትን በማጣራት፣ ለሚመለከተው ውሳኔ ሰጭ የፍትሕ አካል እንዲያቀርብለት ጠይቋል፡፡ ሁለቱም አካላት በአንድነትና በተናጠል እጠፈጸሙ ላሉት ወንጀል ኃላፊነት እንዲወስዱ፣ እነዲሁም በኃይማኖቱ ተከታዮች መካከል እየተፈጠረ ላለው ከባድ ችግር ኃላፊነት እንዲወስዱ እንዲደረግ ጠይቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...