Tuesday, April 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየቀድሞ መከላከያ ሠራዊት አባላት ተሻሽሎ በቀረበው የአገር መከላከያ ሠራዊት አዋጅ ላይ ቅሬታ...

የቀድሞ መከላከያ ሠራዊት አባላት ተሻሽሎ በቀረበው የአገር መከላከያ ሠራዊት አዋጅ ላይ ቅሬታ አቀረቡ

ቀን:

የቀድሞ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ተሻሽሎ በቀረበው የአገር መከላከያ ሠራዊት ረቂቅ አዋጅ የትግል ተሳትፎ ሜዳይ አሰጣጥና የጡረታ አጠባበቅን በተመለከተ ቅሬታ አቀረቡ፡፡

በ2011 ዓ.ም. የወጣውን የመከላከያ አዋጅ ቁጥር 1100 እና በ2013 ዓ.ም የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1232 አንድ በማድረግ የተዘጋጀው የአገር መከላከያ ረቂቅ አዋጅ፣ ኅዳር 13 ቀን 2015 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት የተደረገበት መሆኑ ይታወሳል፡፡

 በረቂቅ አዋጁ ላይ ታኅሳስ 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የሕዝብ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፣ በውይይቱ ከቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላትና ሌሎች አካላት መስተካከል አለባቸው ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ተሻሽሎ በቀረበው የመከላከያ ረቂቅ አዋጅ አንቀጽ 60 አና 61 የትግል ተሳትፎ ሜደይን የሚያብራሩ ናቸው፡፡ በአንቀጽ 60 የተቀመጠው የትግል ተሳትፎ ሜደይ ባለዘንባባ ሽልማት በኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲን ለማስፈን ከደርግ ወይንም የኢትዮጵያ ሠራተኞች መንግሥት ጋር ከ1967 እስከ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. በነበሩት ጊዜያት በትጥቅ ትግሉ ከአሥር ዓመት ያላነሰ ተሳትፎ ያለው ታጋይ የሚሰጥ ስለመሆኑ ያብራራል፡፡

የትግል ተሳትፎ ሜደይ ያለዘንባባ በሚያብራራው አንቀጽ 61 ላይ ደግሞ የትግል ተሳትፎ ሜደይ ያለዘንባባ የሚሰጥ ሽልማት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲን ለማስፈን ከደርግ (የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ መንግሥት) ጋር ከ1967 እስከ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ድረስ በትጥቅ ትግሉ ከአሥር ዓመት በታች ተሳትፎ ላለው ታጋይ የሚሰጥ ሽልማት መሆኑ ተብራርቷል፡፡

በሁለቱም ዓይነት ሽልማቶች የሚሸለም ሰው በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የተፈረመ ልዩ የመታወቂያ ወረቀት እንደሚሰጠው ያብራራል፡፡

ይሁን እንጂ በውይይቱ የተገኙ ተሳታፊዎች በዚህ ረቂቅ አዋጅ ውስጥ ከደርግ/የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ መንግሥት ጋር ከ1967 እስከ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. አሥር ዓመትና ከአሥር ዓመት በታች ላገለገሉ ተብሎ የቀረበው፣ በቀደመው የኢአዴግ ሥርዓተ መንግሥት የወጣ የቀድሞው ሠራዊትን ያላከበረ አለፍ ሲልም የአገር መከላከያ ሰሜን ዕዝን በጦር ለወጉ አካላት ለይቶ ሽልማት ለመስጠት የታሰበ ይመስላል የሚል ቅሬታ አሰምተዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ በረቂቁ የተካተቱት አንቀጽ 60 እና 61 የትጥቅ ትግልን የሚያበረታታ ስለመሆኑ ጠቅሰዋል፡፡ የሽልማቱ መነሻ የደርግ መንግሥትን ለመጣል የተደረገው ትግል ላይ የተሳተፉትን አካላት ያካተተ ብቻ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ አክለውም ‹‹የደርግ መንግሥትን እኛ ተቀበልነውም አልተቀበልነውም በዓለም አቀፍ ደረጃ መንግሥት ተብሎ ቅቡልነት እንደነበረው›› በዚህ ውስጥ የአገርን ድንበርን ያሰከበሩ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት እንደነበሩ ጠቅሰዋል፡፡ ነገር ግን በዚህ ወቅት ዜጎች የመብትና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ቢኖሯቸው እንኳ እነዚህን ጥያቄዎች እንደ መሣሪያ በማድረግ የአገር መከላከያ ሠራዊትን እንዲወጉ ሲያደርጉ የነበሩ አካላትን የሚሸልም አንቀጽ የተካተተበት ረቂቀቅ መሆኑን አቶ ክርስቲያን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በአገር መከላከያ ላይ ጥቃት የሰነዘረ አካልን ለመሸለም ትልም የለው ነው ብለዋል፡፡

ከቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት ድጋፍና ልማት ማኅበር የመጡት ኡርጌሳ ፊጣ ከ1967 እስከ 1983 በነበሩት ጊዜያት ለታገሉ ሰዎች ሽልማት ለመስጠት ተብሎ አንቀጽ ሲቀመጥ፣ ከ1900 ዓ.ም. እስከ 1967 ዓ.ም. ድረስ ‹‹በጦርነት የተሳተፈን ለአገር ደምና አጥንታችን ያፈሰስንላት አገራችን፣ ብረት በሰውነታችን ውስጥ ተሸክመን የምንሄድ ሰዎች እያለን፣ የሰሜን ዕዝ የአገር መከላከያ ሠራዊትን ለወጋ አካል ሽልማት ለመስጠት በአዋጁ ላይ ከ1967 እስክ 1983 የነበሩትን ብቻ ሊሸልም መነሳቱ ጠላትን የሚያጀግን ነው ብለዋል፡፡ ‹‹ይህንን ማየታችንም ስሜታዊ ያደርገናል፤›› ሲሉ አክለው ገልጸዋል፡፡

የቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት ብሔራዊ ማኅበር ጸኃፊ የሆኑት መቶ አለቃ ተስፋዬ አየለ፣ የቀድሞ ለአሁኑ መሠረት ስለሆነ፣ የልጅነት ተስፋችን ለዚህች አገር ስንሰጥ እንደ ማንኛውም ዕቃ ተጠቅመው የሚጥሉን ሰዎች ሆነናል በማለት ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በእኛ ላይ የደረሰው አሁን ባሉት ላይ እንዳይደርስ መስተካከል ያለበት ጉዳይ ከወዲሁ መስተካከል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ለኢትዮጵያ ሲሉ አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍሰው በየዱሩ የወደቁትን ሰዎች ማስታወስ የሁሉም ግዴታ ስለመሆኑ የሚናገሩት መቶ አለቃ ተስፋዬ፣ ቢያንስ በአዋጁ ውስጥ የቀድሞ ሠራዊትን የሚጠቅምና የሚያስታውስ አንቀጽ እንዲካተት ጠይቀዋል፡፡

መቶ አለቃ አየለ አክለውም የቀድሞ ሠራዊት አባላት ሕክምና እንደሌላቸው፣ ጡረታ እንደማይከፈላቸው፣ በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ እንደታገደባቸው፣ በገንዘባቸውም አዋጥተው የሠሯቸው ክበባት እንደተወሰዱባቸው በመግለጽ በአዋጁ እንካተት የሚል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አሥራት ንጉሤ የቀድሞ ሠራዊት አባል ሲሆኑ እንደ እሳቸው ጥያቄ ሠራዊት አገር እንጂ ብሔር የለውም፣ በመሆኑም ይህ የአንድ አገር ሠራዊት በየመንግሥታቱ ስም እየተሰጠው መከፋፈሉን እንደሚያሳዝናቸው ጠቅሰው፣ አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ከ1967 ወዲህ በሚል ብቻ መያዙ ተገቢ አለመሆኑን በመጠቆም በረቂቁ የቀድሞ የሠራዊት አባላት እንዲካተቱ ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሠራዊት ድጋፍና ልማት ማኅበር አባል የሆኑት ሃምሳ አለቃ ቁምቢ ጌቱ የቀድሞ ሰራዊት አባላት ጉዳይ በአዋጅ አለመካተቱ እንዳሳሰባቸው በመጥቀስ በኦጋዴን አጥንታቸውና ደማቸውን አፍስሰው ዛሬ በዚህ ረቂቅ አዋጅ አለመካተት እንዳስከፋቸው ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከመንግሥት አፈንግጦ ጫካ የገባን አካል ታጋይ ተብሎ ለመሸሸለም አዋጅ ሲወጣለት፣ ለኢትዮጵያ የታጋሉትን ደግሞ ያገሸሸ አዋጅ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡ አክለውም ረቂቅ አዋጁ የቀድሞው ሠራዊትን አሳንሶ ያየበት መንገድ አልገባኝም ‹‹ታጋዮች አይደለንም?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ነገር ግን በአሻጥር ተበተንን እንጂ ተሸንፈን ያልወጣን በመሆኑም ይህ ካልተስተካከለ እጅግ አሳዛኝ ውሳኔ ነው ሲሉ ጠንከር አድርገው ተናግረዋል፡፡

አክለውም የቀድሞው ሠራዊት በቤተ ክርስቲያንና መስጊድ ዙሪያ ተኝቶ ነው ያለው ብለዋል፡፡ የመከላከያ ሚኒስቴር ዴኤታዋ ወ/ሮ ማርታ ሉጂ በተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችና የማሻሻያ አስተያየቶች ተገምግመው እንደሚካተቱ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሯ እንደተናገሩት ከ1967 እስከ 1983 በሚል ብቻ የአንድ የመንግሥት ሥርዓትን ብቻ ያካተተ ሆኖ የቀረበው ረቂቅ በድጋሚ ታይቶ የተሻሻለ የመነሻ ጊዜ ይበጅለታል ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ የአዋጁ ዋነኛ ይዞታ በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ያለን ሠራዊትና ከመከላከያ እስኪሰናበት ባለው ጊዜ ውስጥ በመሆኑ፣ የተሰናበቱ የመከላከያ ሠራዊት አባላትን ያካተተ አዋጅ ቢቀመጥ፣ የመከላከያ ተቋሙ ከሚሰጠው በጀትና ከተሰጠው ኃላፊነት ጋር የሚጋጭ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የቀድሞ ሠራዊት አባላትን ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያየ አማራጮችን መዘርጋት አስፈላጊ ስለመሆኑ ከመከላከያ ሚኒስትር የመጡ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...