Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኤርትራ ጦር ከትግራይ መውጣቱ የአውሮፓ ኅብረት ከኢትዮጵያ ጋር ለሚኖረው ግንኙነት ወሳኝ መሆኑን...

የኤርትራ ጦር ከትግራይ መውጣቱ የአውሮፓ ኅብረት ከኢትዮጵያ ጋር ለሚኖረው ግንኙነት ወሳኝ መሆኑን አስታወቀ

ቀን:

ሐሙስ ታኅሳስ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. በናይሮቢ የተፈረመውን፣ ‹‹ግጭትን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት›› በተመለከተ መግለጫ ያወጣው የአውሮፓ ኅብረት፣ የኤርትራ ጦር በአስቸኳይና ያለ ቅድመ ሁኔታ ከትግራይ ክልል ለቆ መውጣቱ ከኢትዮጵያ ጋር ላለው ግንኙነት ወሳኝ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኅብረቱ የውጪ ግንኙነትና የደኅንነት ፖሊሲ ቃል አቀባይ ባወጣው መግለጫ፣ ከኤርትራ ጦር መውጣት በተጨማሪ፣ የሰላም ስምምነቱ መተግበር ኅብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ለሚኖረው ግንኙነት ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

ኅብረቱ በመግለጫው ዘላቂ ሰላም የመፍጠር ስምምነቱ መፈረም እንዳስደሰተው፣ በትግራይ ክልል ሰላም እንዲፈጠር መሠረት እንደሚሆንም ተስፋውን ገልጿል፡፡ ይሁን እንጂ ዘላቂ ሰላምን የማስፈኑ ሥራ ቁርጠኛ አመራርን እንደሚጠይቅ ነው ያሳሰበው፡፡

ከኢትዮጵያ ጋር ኅብረቱ ግንኙነቱን ለማደስና መልሶ ለመጠገን ብዙ ቅድመ ሁኔታዎችን ኢትዮጵያ እንድታሟላ ጠይቋል፡፡ የሰብዓዊ ረድዔት አቅርቦት ያለገደብ መከናወን እንዳለበት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙና ሕጎችን የተላለፉ አካላት ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ሲልም ኅብረቱ ቅድመ ግዴታ ያላቸውን ዘርዝሯል፡፡

በሌላም በኩል የኤርትራን ጦር ከትግራይ ክልል መውጣት እንደ ቅድመ ሁኔታ ያቀረበው የኅብረቱ መግለጫ፣ የኤርትራ ኃይሎች ወደ ነበሩበት ይመለሱ ብሏል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2000 ዓ.ም. የተፈረመው የአልጀርሱ ስምምነት፣ እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ2019 የተፈረመው የኢትዮ ኤርትራ ስምምነት በአስቸኳይ እንዲተገበርም ነው የጠየቀው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የኤርትራ ጦር በሄግ ፍርድ ቤት የተሰጠውን የባድመ ግዛትን ይዞ እንዲቆይ የሚጠይቅ እንደሆነ በመዘገብ ላይ ነው፡፡

ኤርትራ ጦሯን ወደ ትግራይ ክልል አስገብታለች የሚለውን ክስም ሆነ ወቀሳ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቀብሎት አያውቅም፡፡ የአውሮፓ ኅብረት የኤርትራ ጦር ካልወጣ ግንኙነታችንን አናድስም ላለበት መግለጫ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚሰጠው ምላሽ እየተጠበቀ ነው፡፡

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በበኩላቸው፣ ‹‹የአውሮፓ ኅብረት ለአንድ ወገን ያደላ አቋም ማንፀባረቁን ገፍቶበታል›› በማለት መግለጫውን አጣጥለውታል፡፡

‹‹ኤርትራ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ዘላቂ ሰላም፣ ፍትሕና የሕግ የበላይነት በመስፈኑ በእጅጉ ትጠቀማለች እንጂ አትጎዳም፤›› ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ያስታወቁት አቶ የማነ፣ አገራቸው ኤርትራ ለእነዚህ እሴቶች መረጋገጥ ከመጀመርያውም መቆሟን ገልጸዋል፡፡

ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሓት መካከል የሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል፡፡ ኅዳር 3 ቀን ደግሞ ይህን ስምምነት በተግባር ለመተርጎም ያስችላል የተባለ ስምምነት በኬንያ ናይሮቢ በሁለቱ አካላት የጦር መሪዎች መካከል መፈረሙ አይዘነጋም፡፡

ሁለቱ የሰላም ስምምነቶች ከተፈረሙ በኋላ የሕወሓት አማፂያን ትጥቅ ፈተው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ክልሉን ይቆጣጠራል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ይህ ሳይሆን መዘግየቱ ይነገራል፡፡

የኤርትራ ጦርና ከመከላከያ ውጪ ያሉ የታጠቁ ኃይሎች ከትግራይ ክልል ባለመውጣታቸው ነው የሰላም ስምምነቱ በተባለው ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ያልተተገበረው የሚለውን የሕወሓቶች ክስ ደግሞ፣ የአውሮፓ ኅብረትና አሜሪካ በተደጋጋሚ እያስተጋቡት ነው፡፡

ዘላቂ ሰላም በትግራይ ክልል ለማስፈን ያግዛል የተባለው የሰሞኑ የናይሮቢ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ፣ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያና በኤርትራ ላይ ጫናውን መግፋቱ የዚሁ ውጤት መሆኑ እየተዘገበ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...