Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊማንኛውም አለመግባባት በሰላማዊ መንገድና በውይይት ብቻ እንዲፈታ  ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን አቀረበች

ማንኛውም አለመግባባት በሰላማዊ መንገድና በውይይት ብቻ እንዲፈታ  ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን አቀረበች

ቀን:

  • የሃይማኖት ትንኮሳ ሕግና ሥርዓት እንዲበጅለትም አሳስባለች

በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች የዜጎች ሞት፤ መፈናቀል፤ ስደትና የንብረት መውደም እጅጉን ያሳዝነናል፣ ያሳስበናል ያለችው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ማንኛውንም አለመግባባት በሰላማዊ መንገድና በውይይት ብቻ እንዲፈታ ጥሪዋን አቀረበች፡፡

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት 54ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማጠናቀቁን አስመልክቶ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ታኅሣሥ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ ከሁሉም በላይ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ የሰው ልጅ ክቡር ሕይወት እንዳይጠፋ፣ ማንኛውንም አለመግባባት በሰላማዊ መንገድና በውይይት ብቻ እንዲፈታ ጥሪያችንን እናቀርባለን ያሉ ሲሆን፣ ጉዳት የደረሰባቸውንም ሁሉ ሰብዓዊ ዕርዳታ ሊቀርብላቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ሁሉም በጎ ፈቃድ ያላቸው ተቋማት በኢትዮጵያ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ሁሉ መድረስ እንዲቻል የተለመደውን ድጋፋቸው እንዲቀጥል ጥሪ ያደረጉት ካርዲናል ብርሃነየሱስ፣ በተለይም በደቡብና በምሥራቅ አካባቢ በድርቅ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ያሉትን ወገኖች እንዲታገዙ ያሳሰቡ ሲሆን፣ ቤተ ክርስቲያኒቱም የበኩሏን ድጋፍ ማድረጓን ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

በተያያዘም በአገሪቱ የሚታየው የኑሮ ውድነት ጫና በርካታ ወጣቶችና ዜጎች ሥራ አጥ እንዲሆኑ፣ ለስደትና ለኢፍትሐዊ የሥራ ስምምነቶች እንዲዳረጉ እያስገደዳቸው መሆኑን ለማስተዋል መቻሏን የገለጸችው ቤተ ክርስቲያኗ፣ መንግሥትና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ፍትሐዊ የሆነ የገበያ ሥርዓት በማስፈን ዜጎች በአገራቸው በተመጣጠነ የኑሮ ሥርዓት መኖር እንዲችሉና ሠርተው ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን የመደገፍ ሰብዓዊ መብታቸው እንዲጠበቅ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርባለች።

እንዲሁም በአገሪቱ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ የመጣውን ሌብነትና ሙሰኝነት በዚህም ምክንያት እየተስፋፋ የመጣውን አግባብነት የሌለውና ሕዝብን የሚያጉላላና መንግሥታዊ አገልግሎቶችን በጉቦ የማስፈፀምን አካሄድ አጥብቆ እንደሚያወግዝ ያስታወቀው የጳጳሳቱ ጉባዔ፣ ኢትዮጵያ በሥነ ምግባር የታነፁ፣ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላቸውና የራሳቸው ያልሆነውን ለመውሰድ ከማሰብ ይልቅ በተሰጣቸው ነገር የሚያመሰግኑ እንዲሁም ከወገኖቻቸው ጋር ተካፍለው ማደር የሚችሉ ዜጎች የሚፈሩባት እንድትሆን የሁልጊዜም ጸሎቱ መሆኑን ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ በተከታታይ እንዲሁም በተለይ ደግሞ ሰሞኑን እየተደረገ ያለው የሃይማኖት ትንኮሳ በእጅጉ የሚያሳዝን መሆኑን የገለጸችው ቤተ ክርስቲያኒቷ፣ የሚመለከተው ሥልጣን ያለው አካል ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ ሕግና ሥርዓት እንዲያበጅለት አሳስባለች፡፡

የሃይማኖት መሪዎች፣ አስተማሪዎችና ሰባኪዎች የሃይማኖት ግጭትን የሚያነሳሱ፣ አማኞችን የሚያሳዝኑና የእምነት ተቋማትን ክብር የሚነኩ አስተምሮቶችን ከማስተማር እንዲቆጠቡም ተማፅናለች፡፡

ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በሃይማኖቶች መካከል በመቻቻልና በመከባበር ያቆያቸውን እሴቶች በመጠበቅ፣ ለግጭት መንስዔ ሊሆኑ ከሚችሉ ቃላትና ንግግሮችም በመቆጠብ በጋራ ለሰላም እንቁምም ብላለች፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...