Tuesday, April 23, 2024
Homeስፖንሰር የተደረጉስለ አዲሱ ሱዙኪ ዲዛየር (New Suzuki Dzire) ተሽከርካሪ እውነታዎች።

ስለ አዲሱ ሱዙኪ ዲዛየር (New Suzuki Dzire) ተሽከርካሪ እውነታዎች።

Published on

- Advertisment -

ከዛሬ መቶ ዓመት በፊት የወላጅ እናቱን የልብስ ስፌት ሽመና ስራ ለማቅለል የተጀመረው የሚስተር ሱዙኪ የፈጠራ ሥራ ዛሬ ላይ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆኑት እና ግዙፍ የሞተር ኩባንያ አንዱ የሆነውን ሱዙኪ ሞተር ኮርፖሬሽንን ለዓለም አብርክቶልናል። ከዚህም በላይ የሱዙኪ ኮርፖሬሽን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰው ልጆችን ድካም ለማቀለል በሞተር ሳይክል፣ ለባህር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ የተላያዩ ጀቶችን እንዲሁም የተለያዩ አውቶሞቢሎችን ለዓለም አቀፍ ገበያ በማቅረብ ለአውቶ ኢንደስትሪው ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። የሱዙኪ ሞተር ኮርፖሬሽን በተለይም የኮምፓካት ካር ሀሳብን ለአውቶ ኢንደስትሪው በማስተዋወቅ ግንባር ቀደም ሲሆን በየትኛውም ዓለም የሚገኝ ሰው በቀላሉ የተሽከርካሪ ባለቤት በማድረግ ከየተኛውም የተሽከርካሪ አምራቾች ታዋቂ ለመሆን ችሏል።

ከዛሬ አርባ ዓመት በፊትም የህንድን አውቶ ኢንደስትሪ በማሩቲ ኢንተርናሽናል ኩባንያ በኩል ከተቀላቀለ በኃላ ሱዙኪ ተሽከርካሪዎች በህንድ የተሽከርካሪዎች ገበያ ውስጥ በእያንዳንዱ ቤት ውስጥ ከዕለት ተዕለት አላቂ አስቤዛ ሲቀጥል ሱዙኪ ማለት የተለመደ በመሆኑ ሱዙኪ ከተሽከርካሪ ሌላ የሚያመርተው ሸቀጥ ሊኖር ይችላል የሚል ጥርጣሬን ማጫሩ አይቀርም።ሱዙኪ ማሩቲ በህንድ ሀገር ተሽከርካሪዎችን በማምረት የህንድ የተሽከርካሪን ገበያ ከመቆጣጠሩም በላይ ተሽከርካሪዎችን ለተለያዩ ሀገሮች ኤክስፖርት በማድረግ በዓለም ዓቀፍ የተሽከርከሪ ገበያ በቁጥር ግንባር ቀደም ከሆኑ የተሽከርካሪ ብራንዶች ዋነኛ ለመሆን ችሏል። ሱዙኪ ማሩቲ ለዓለም ዓቀፍ ገበያ ከሚያቀርባቸው ንዑስ ሳሎን (Compact Sedan) ከሆኑት የሱዙኪ ምርቶች ዋነኛ የሆነውን ሱዙኪ ስዊፍት ተሽከርካሪ ለህንድ ገበያ ማምረት የጀመረው እ.ኤ.አ በ2008 ዓ.ም. ሲሆን ኋላ ላይም ሱዙኪ ስዊፍት ተሸከርካሪን የስም ማስተካከያ በማድረግ ሱዙኪ ዲዛየር በሚል ስያሜ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ችሏል።

ሱዙኪ ዲዛየር ተመርቶ ለህንድ ገበያ መቅረብ ከጀመረበት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ከ 2.5 ሚሊዮን በላይ ተሽከርካሪዎች የተሸጡ ሲሆን በህንድ ገበያም በንዑስ ሳሎን ሞዴል ክፍል በኩል አንደኛ ተመራጭ ሞዴል ለመሆን ችሏል።

በሀገራችንም ምንም እንኳን የሱዙኪ ተሽከርካሪ ምርቶች በተለያየ ሞዴል እ.ኤ.አ ከ 2017 ዓ.ም በፊት በገበያ ውስጥ ለረዥም ዘመን የሚታወቁ ቢሆንም ሱዙኪ ዲዛየር እና ሌሎችም ሞዴሎች በስፋት መግባት እና ገበያውን መቆጣጠር የቻሉት እ.ኤ.አ ከ 2017 ዓ.ም. ወዲህ መሆኑን ልብ ይሏል። እንደ ኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮምሽን መረጃ መሰረት ከ 2017 ዓ.ም. ወዲህ በአጠቀላይ ከ 25000 በላይ የተለያዩ ሱዙኪ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ሲሆን በመንግስት በኩል አሮጌ ተሽከርካሪዎችን በአዲስ ለመተካት ከወጣው የጉምሩክ ታክስ ለውጥ ወዲህ ቀላል ቁጥር የሌላቸው ሱዙኪ ዲዛየር ተሽከርካሪዎች ከሌሎች ተወዳዳሪ ተሽከርካሪዎች በመሻል ለተጠቃሚዎች ደርሰዋል።  የተሽከርካሪዎቹ መነሻ መግዢያ ዋጋ ምክንያታዊ መሆን፣ ከግዢ በኋላ ለተሽከርካዎች የሚወጡ የመደበኛ ሰርቪስ ወጪ ምክንያታዊ መሆን ፣ በአደጋ ጊዜ የተሽከርካሪዎች የመለዋወጫ ዋጋ ምክንያታዊ መሆን እና የነዳጅ ፍጆታቸው ኢኮኖሚያዊ መሆን የተሽከሪዎቹ የገበያ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንዲመጣ አድርጎታል።

የሱዙኪ ዲዛየር ተሽከርካሪ አራት ሲሊንደር የተገጠመለት ሞተር የሚጠቀም ሲሆን የሻንሲ መዋቅሩም ሀርትቴክት ፕላትፎርም ሲሆን ይህም ቀላል ነገር ግን ጠንካራ ከሆነ ቴንሳይል ስቲል ግብዓት ከመሰራቱም በላይ፣ የሻንሲ መዋቅሩ ያልተቀጣጠለ ወጥ ቀላል ብረት በመሰራቱ በአደጋ ወቅት በቀላሉ የአደጋውን ተጽዕኖ ወደ በእኩል እና በተመጣጠነ ሁኔታ ሻንሲው ብረት እንዲዘዋወር በማድረግ በአውቶሞቢል ኢንደስትሪው ከፍተኛ ተቀባይነትን ለማትረፍ አስችሎታል።

በተለይም በአደጋ ምክንያት በተሳፋሪዎች ላይ የሚደረስን ጉዳት ከመቀነስ እና የተሳፋሪዎችን ደህንነት ከመጠበቅ አንጻር የሱዙኪ ዲዛየር ተሽከርካሪዎች በአጠቃላይ የሻንሲ መዋቅራቸው ከፍተኛ ተቀባይነትን ለማግኝት አስቸሎታል። ሱዙኪ ዲዛየር አራት በአንድ መስመር የተደረደሩ አራት ሲሊንደር እና 1200 ኩቢክ ካፓሲቲ የሞተር መጠን የተገጠመለት ሲሆን 66 ኪሎዋት ጉልበት ያለው ሲሆን ይህም በዝቅተኛ የነዳጅ ፍጆታ ከፍተኛ ጉልበት እንዲያመነጭ አስችሎታል። አዎቶሜትድ ማኑዋል የጉልበት ማስተላለፊያ የተገጠመለት ተሽከርካሪ በመሆኑ፤ ከማኑዋል እና ከአውቶማቲክ የጉልበት አስተላላፊ ተሽከርካሪዎች የሚገኙ አዎንታዊ ጥቅሞችን አጣምሮ በመያዙ ማኑዋል ተሽከርካሪዎቸን ለመንዳት የሚያጋጥሙ ውጣ ውረዶችን በማስቀረት ነገር ግን ከማኑዋል ተሽከርካሪዎችን በቀላሉ ከመጠገን እና የነዳጅ ፍጆታን በመቆጠብ የሚገኙ ጥቅሞችን ተጠቃሚዎች እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

ሱዙኪ ዲዛየር ተሽከርካሪዎች የቀጣይ ትውልድ ኬ ሲሪየስ ሞተር የተገጠመለት ሲሆን በተጨናነቀ የትራፊክ እንቅስቃሴ ውስጥ በራሱ ሞተር የሚያጠፋ እና የሚያስነሳ ቴክኖሎጂን (Engine Idle start-stop technolongy) ለመጀመሪያ ጊዜ በህንድ አውቶ ኢንደስትሪ በማስተዋወቅ ይታወቃል። በአሁኑ ወቅት ገበያ ላይ እየተሸጡ የሚገኙት ዲዛየር ተሽከርካሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ ማሻሻያ የተደረገባቸው እ.ኤ.አ በ 2020 ዓ.ም. ሲሆን ሞተራቸውም VVT BS6 ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው ሲሆን ይህም ሞተራቸው የተሻለ ዕመቃ (Higher Compression Ratio) ፣የተሻሻለ የሞተር ፒስተን ማቀዝቀዣ እና የሞተር ዕፍግታ (Enhanced Engine friction) በመቀነስ የተሻለ ጉልበት ማመንጭት እንዲችል ተደርጎ ተሻሽሎ የቀረበ መሆኑ ይታወቃል።

አዲሱ 2020 Dzire ሰፊ አቋሙ ሰፊ ቦታ እና የላቀ ደህንነት እንዲኖረው ተደርገው የተፈበረኩ ናቸው። አዲሱ Dzire 2020 ሞዴል Electronic Stability Program እና የ Hill-hold አማራጭ የተገጠመላቸው በመሆኑ ተሽከርካሪዎች ፍሬን በሚያዝበት ወቅት ወደ ኋላ እንዳይንሸራተት ይረዳል። በተጨናነቀ የትራፊክ ሁኔታ ውስጥ ተሽከርካሪው ቆሞ በሚነሳበት ወቅት ተዳፋት ላይ እንዳይንከባለል Hill-hold አማራጭ የተገጠመለት ሲሆን፣ ይህም አሽከርካሪው ሁል ጊዜ ተሽከርካሪውን በቁጥጥር ስር ማቆየቱን ያረጋግጣል። የ2020 ዲዛየር አስተማማኝ የፊት እና የኋላ ፍጥነት መቆጣጠሪያ ያላቸው ሲሆን ፣ ይህም የተሻለ የብሬኪንግ አፈጻጸም እና የፍሬን ህይወትን ይሰጣል። በተጨማሪም፣ ሁሉም ተለዋዋጮች ባለሁለት ኤርባግ፣ ቅድመ-ውጥረትን የሚገድብ የመቀመጫ ቀበቶዎች፣ ISOFIX (የልጆች መቀመጫ ማቆያ ስርዓት) እና ኤቢኤስ ከ EBD ጋር የተገጠሙ ናቸው።

በአምስተኛው ትውልድ HEARTECT መድረክ ላይ የተገነባው አዲሱ 2020 Dzire የፊት ለፊት ማካካሻ፣ የጎን ተፅዕኖ እና የእግረኛ ደንቦችን ያከብራል።

በሀገራችን ብቻ ሳይሆን ሱዙኪ ዲዛየር በህንድ ሀገር ውስጥ ዓመታዊ ሽያጫቸው ከሁሉም ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ በማግኘት በተጋጋሚ ዓመታት አንደኛ ደረጃን ያገኘ መሆኑ ይታወቃል።

ሱዙኪ ዲዛየር ተሽከርካሪዎችን ከህጋዊ ወኪል ለሚገዙ ተጠቃሚዎች የሱዙኪ ኮርፖሬሽን 3 ዓመት ወይም 100,000 ኪ.ሜ ድረስ የሚደረስ ዋስትና የሚሰጥ መሆኑ በተለይም በሞዴሎቹ ላይ ያለውን የጥራት ደረጃ ለመረዳት ይቻላል።

በታምሪን ሞተርስ የቀረበ

የቅርብ ጊዜ መጣጥፎች

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን ስለሕዝቦቻችን የተሻሉና ዘለቄታዊ ሕይወቶች ስንል...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው ከሃያ በላይ የሚሆኑ ዋና ዋና...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ ላይ የጣለው ልዩ ልዩነታችን በጭራሽ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች ቡድን በቅርቡ ባቀረበው ረቂቅ ፖሊሲ...

ተመሳሳይ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም በቶነር አሴምብሊንግ ስራ የተሰማራ ድርጅት...

ኦርቶፔዲክስ

በጡንቻ መገጣጠሚያ እና የአጥንት ህመሞች ላይ የላቀ ጥበብ፡- የአጥንት ጉዳትን ችግር ከመመርመርም ያለፈ የአጥንትና መገጣጠሚያ...

የአየርላንድ እና የኢትዮጵያ የ30 ዓመታት ግንኙነት ስናከብር

ዘንድሮ አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት የጀመረችበት 30ኛ ዓመት ቢሆንም ግንኙነቱ ግን ከዚያም በበለጠ...