Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበጃንሜዳ አገር አቋራጭ ውድድር በርካታ ዕውቅ አትሌቶች ይጠበቃሉ

በጃንሜዳ አገር አቋራጭ ውድድር በርካታ ዕውቅ አትሌቶች ይጠበቃሉ

ቀን:

  • አምስት የምሥራቅ አፍሪካ አገር አትሌቶች ይሳተፋሉ

ዓመታዊው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር የፊታችን እሑድ ታኅሣሥ 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡ ለ40ኛ ጊዜ በጃንሜዳ በሚካሄደው አገር አቋራጭ ውድድር በርካታ ዕውቅ አትሌቶች እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡ በሁለቱም ጾታዎች ከወጣት ጀምሮ አዋቂ አትሌቶች በ6 ኪሎ ሜትር፣ በ8 ኪሎ ሜትርና 10 ሺሕ ኪሎ ሜትር እንዲሁም በድብልቅ ቅብብሎሽ ሩጫ ይወዳደራሉ፡፡

ከአገር ውስጥ አትሌቶች ባሻገር የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ታዋቂ አትሌቶችንም ጨምሮ ከ1,200 በላይ አትሌቶች እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገልጿል፡፡

ውድድሩ እ.ኤ.አ. በ2023 በአውስትራሊያ ባቱረስት በሚከናወነው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች የሚመረጡበት ነው፡፡

ከዓምና ጀምሮ ‹‹የምሥራቅ አፍሪካ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና›› የሚል ተጨማሪ ስያሜ ባገኘው ውድድሩ፣ አምስት አገሮች ኬንያ፣ ኤርትራ፣ ዑጋንዳ፣ ጂቡቲ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን እንዲሳተፉ  መጋበዛቸውን ፈዴሬሽኑ ገልጿል፡፡

በብሔራዊ ፌዴሬሽን ከሚዘጋጁት ውድድሮች አንዱ በሆነው ውድድር ላይ በ6 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚያሸንፉ 6 አትሌቶች፣ በ8 ኪሎ ሜትር ወጣቶች 6 አትሌቶች፣ በ10 ኪሎ ሜትር የሚያሸንፉ በሁለቱም ጾታ 6 ልጆች፣ እንዲሁም በድብልቅ ዱላ ቅብብል 4 አትሌቶች በድምሩ 22 አትሌቶችና አራት ተጠባባቂ አትሌቶች ኢትዮጵያን ወክለው በዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ይካፈላሉ፡፡

ዓመታዊው ሻምፒዮና ለአትሌቶች የውድድር ዕድል ከመፍጠሩም በላይ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ አገራቸውን ወክለው የሚወዳደሩ ተተኪ አትሌቶችን ማግኛ መድረክ ነው፡፡

በዘንድሮ ሻምፒዮና ላይ እንደሚሳተፉ ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል ለተሰንበት ግደይ አንዷ ነች፡፡ ሦስት የዓለም ክብረ ወሰኖችንና የቤት ውስጥ እንዲሁም የጎዳና ሩጫዎች ላይ ድንቅ ብቃቷን ማሳየት የቻለችው አትሌቷ  ተጠቃሽ ነች፡፡

እ.ኤ.አ. በ2015 በጃንሜዳ ዓለም አቀፍ አገር አቋራጭ መሳተፍ የጀመረችው ለተሰንበት፣ በወጣቶች 6 ኪሎ ሜትር ውድድር በማሸነፏ፣ በቻይና ጉያንግ በተካሄደው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ለመወዳደር አስችሏታል፡፡ ለተሰንበት እ.ኤ.አ. በ2017 በጃንሜዳ አገር አቋራጭ ውድድር ላይ በማሸነፏም በዚያው ዓመት በዑጋንዳ ካምፓላ የወጣቶች ውድድር ላይ ተሳትፋ በበላይነት ማጠናቀቅ ችላለች፡፡

በሌላ በኩል የቶኪዮ የ2020 ኦሊምፒክ ጨዋታ የ10 ሺሕ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው ሰሎሞን ባረጋ፣ በዘንድሮው ውድድር ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል። ሌላው የዓለም ሻምፒዮን 5,000 ሜትር ባለድሉ ሙክታር እድሪስ፣ ጌታነህ ሞላ፣ አንዱአምላክ በልሁና ተስፋዬ አካልነውም ከሚካፈሉ አዋቂ አትሌቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተከትሎ አውስትራሊያ የጉዞ ገደቦች በማድረጓ ሃቻምና ያልተካሄደው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮናን የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም. በባቱረስት ከተማ እንደምታካሂድ ይጠበቃል፡፡

በመካከለኛና በረዥም ርቀት በመፎካከር የሚታወቁት የኢትዮጵያና የኬንያ አትሌቶች ከ1981 እስከ 2017 የተደረጉትን የአገር አቋራጭ ውድድሮች በበላይነት ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡

በወንዶች 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ኬንያ ከ1986 እስከ 2013 ዓ.ም. ባደረጉት ተሳትፎ ለ18 ዓመታት ውድድሩን በበላይነት በማሸነፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሌለው ስኬት ማስመዝገብ ችሏል፡፡ በአንፃሩ በሌሎች ርቀቶች ላይ ሁለቱ አገሮች በተፎካካሪነት እንደቀጠሉ ናቸው፡፡

ከሁለቱ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች በዘለለ፣ ፖርቱጋል በቡድን እ.ኤ.አ ከ1991 እስከ 1994 ያሉትን ውድድሮች ማሸነፍ ሲችሉ፣ በታዳጊ ሴቶች ውድድር ከምሥረታው 1989 ጀምሮ ከኬንያና ከኢትዮጵያዊያን አትሌቶች እጅ ወጥቶ አያውቅም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...